በቂሊንጦ ወህኒ ቤት የሚገኙት የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እሳቸውንና አቶ በቀለ ገርባን ለማስገደል ትዕዛዝ ተላልፎ እንደነበር አስታወቁ። የቂሊንጦ እስርቤት የደህንነትና ጥበቃ ሃላፊ በነበሩት ዋና ኦፊሰር ገብረማርያም ወልዳይ ተላልፎ የነበረው ትዕዛዝ በእስር ቤቱ ፖሊሶች እምቢተኝነት ሳይሳካ መቅረቱንም አስታውቀዋል። ይሄ መረጃ የወጣው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በእነ መቶ አለቃ ማስረሽ ሰጤ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ሰዎች ላይ የሚሰጠው ምስክርነት በተሰማበት ወቅት ነበር። ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የነበረውን የትናንት ታህሳስ 24 /2017 ውሎ በመረጃ መረቡ ላይ አስፍሮታል። በዋናነት በችሎቱ ይታይ የነበረው በእነ የመቶ አለቃ ማስረሽ ሰጤ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ሰዎች ላይ የሚሰጠው ምስክርነት ነበር። በችሎቱ ቀረበው የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጡ የነበሩት ደግሞ የቂሊንጦ እስርቤት የደህንነትና ጥበቃ ሃላፊ የነበሩት ዋና ኦፊሰር ገብረማርያም ወልዳይ ናቸው። የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ጠያቂ ዋና ኦፊሰር ገብረማርያም ደግሞ ተጠያቂ በሆኑበት በዚህ መድረክ ላይ ፍርድ ቤቱም ጣልቃ እየገባ አስታራቂ የሚመስሉ ሀሳቦችን ለመሰንዘር ሲሞክር ተስተውሏል። ተከሳሹ የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ በዋናነት
እሳቸውንና አቶ በቀለ ገርባን ለማስገደል ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን፣ በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት የተገደሉ እስረኞች በጅምላ ተቀብረው ቀብሩ ላይ እስር ቤት እንደተሰራ፣ የተገደሉ እስረኞች አስከሬንን ለቤተሰብ አለመሰጠታቸውንና ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። ጠያቂው በመጀመሪያ በችሎቱ ላይ ለምስክሩ ያቀረቡት ጥያቄና ያረጋገጡት እውነታ ቢኖር በእስር ቤት ያሉ ግፎች ሁሉ ሲፈጸሙ የእስር ቤት ሃላፊነቱን ቦታ ሲቆጣጠሩ የነበሩት ሁሉም የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መሆናቸውን ነው። የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እኔንና አቶ በቀለ ገርባን በጥይት ተመተን እንድንገደል ትዕዛዝ አስተላልፈው ፖሊሶች ግን አንገድልም አላሉዎትም ወይ ሲሉ ላቀረቡላቸውጥያቄም ትዕዛዝ አላስተላልፍኩም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ጠያቂው ግን በወቅቱ ትዕዛዝ መስጠታቸውን የሚያረጋግጡና ከዛም ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጥያቄዎችን ማንሳታቸው ተመልክቷል። በቂሊንጦ እስር ቤት ስለተነሳው የእሳት ቃጠሎና ከዛም ጋር በተያያዘ ሕየወታቸው ስላለፈው እስረኞች ጉዳይም የመቶ አለቃ ማስረሻ ላቀረቡት ጥያቄ የሞተ ሰው ስለመኖሩ አላየሁም የሚል ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል። በወቅቱ እሳቸው የቂሊንጦ እስርቤት የደህንነትና ጥበቃ ሃላፊ በሆኑበት ሁኔታና በማረሚያ ቤቱ በኃላፊነት 2ኛ ሰው መሆናቸው እየታወቀ የሟቾቹን ቁጥር አላውቅም ማለታቸው በብዙዎች ዘንድ ትዝብትን ፈጥሯል። ነገር ግን የመቶ አለቃ ማስረሻ አንተ ይህን ትላለህ እንጂ ካንተ መረጃ የተቀበሉት የህወሃት መገናኛ ብዙሃን የሟቾቹን ቁጥር 23 ብለው መረጃ ሰተዋል ሲሉ ምላሻቸው የማይገናኝና ሀሰተኛ መሆኑን አሳይተዋቸዋል። በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት የተገደሉ እስረኞች በጅምላ ተቀብረው ቀብሩ ላይ እስር ቤት ተሰርቷል ለሚለው ጥያቄም ምንም አላየሁም በሚል መልኩ ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል። በአጠቃላይ በችሎቱ ለተነሱትና በርካታ ወንጀሎች በሳቸው ዙሪያ መፈጸማቸውን በሚያሳይ መልኩ ጥያቄ የቀረበላቸው መስካሪው በስተመጨረሻ በሁሉም ጉዳይ ላይ ተጠያቂ አይደለሁም ሲሉ ደምደመዋል። ትክክለኛው የፍትህ ምላሽ ምን እንደሚሆን ባይታወቅም እንኳ።

No comments:
Post a Comment