Wednesday, January 17, 2018

በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ 31ኛ ተከሳሽ አቶ ጌታቸር እሸቴ የስርአቱ ሰዎች እየገደሉና እየረሸኑ ድሆች የእነሱን ሐጥያት እንዲሸከሙ እየተደረጉ ነው ሲሉ በጻፉት ድብዳቤ አስታወቁ።

በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ 31ኛ ተከሳሽ አቶ ጌታቸር እሸቴ የስርአቱ ሰዎች እየገደሉና እየረሸኑ ድሆች የእነሱን ሐጥያት እንዲሸከሙ እየተደረጉ ነው ሲሉ በጻፉት ድብዳቤ አስታወቁ። አቶ ጌታቸር እሸቴ በ30 ደቂቃ ውስጥም 9 ሰዎችን ግድለሀል ተብዬ በሀሰት ውንጀላ መከሰሴን ዓለም ይወቅልኝ በማለት ተናግረዋል። ነሐሴ 28/2008 የቂሊንጦ እስር ቤት በእሳት በጋየበት ወቅት በተደረገ ተኩስ 23 እስረኞች መገደላቸውን የህወሃት መንግስት በወቅቱ ያመነ ሲሆን የዓይን ምስክሮችና አንዳንድ ታሳሪዎች ቁጥሩ በሁለት እጥፍ እንደሚሆን ይናገራሉ ። ከዚህ ጋርም በተያያዘ 38 ሰዎች በሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው የፍርድ ሂደታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ። ከተከሳሾቹ መካከል 31ኛው ተከሳሽ የሆኑት አቶ ጌታቸር እሸቴ ይህንን አሰቃቂ ወንጀል የስርዓቱ ሰዎች መፈጸማቸውን ዓለም ይወቅልን ሲሉ ሁኔታውን በዝርዝር ጽፈዋል። ዜጎችን እየገደሉና እየረሸኑ ዜጎችን ያለ ስራቸው የእነሱን ወንጀል የሚያሸክሙትና የፖለቲካ መልስ የሚያደርጉትን ባለስልጣናት አንድ ቀን የሰማይና ምድር ገዥ የሆነው አምላክ እንደሚያጋልጣቸው ተስፋ አለኝ ሲሉም በምሬት ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ
አይበገሬነቱን የሚያሳየው የራሱ መንግስታትም ሆነ የውጭ ጠላት በሕዝብ ላይ የሚፈፅሙትን አረመኔያዊ ድርጊት እና በደል በመታገል እንደሆነ ከታሪክ የምንረዳው ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የቂሊንጦን የገሃነም ድርጊት ዝም ብሎ መመልከቱም የሚያሳዝን ነው። አንድ ድሃ በ30 ደቂቃ ውስጥ 9 ሰው ገድለሃል ተብሎ የፖለቲካ መልስ መስጫ እና የሀሰት ክስ ሰለባ ሲሆን ሕዝብ በተለይም ምሁራን፣ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ዝምታ እጅግ አሳዝኖኛል። ይህ እውነታ እያለና ወንጀሉን የፈጸሙት ሀላፊዎች ሆነው ሳለ በዚህ ጉዳይ የድሀ ልጆች በከባድ የሽብር ክስ እንድንከሰስ ተደርገናል ብለዋል። ወንድሞቻችን በእሳት ከስለውና ተረሽነው ዝም ማለት ሀገር አለ ወይ? ህዝብስ አለ ወይ? የሚል ጥያቄን ያስነሳል ብለዋል። አቶ ጌታቸር በደብዳቤአቸው ሲቀጥሉ የቂሊንጦ የደህንነትና ጥበቃ ሀላፊውና ኦፊሰር ገ/ማርያም ወልዳይ ጥፋቱ የራሳቸው መሆኑን የሚያሳይ ምስክርነት ሰጥተዋልም ይላሉ። ታዲያ ይህ በሆነበት ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ የተከሰስነው ስቃይና መከራውን እየተቀበልን ፍ/ቤት እየተመላልሰን እንገኛለን ሲሉ በምሬት ይገልጻሉ። የኢትዮጵያና የዓለም ህዝብ እውነታውን እንዲመረምር፣ትክክለኛ ፍርዱንም እንዲሰጥ ጥሪም ያቀርባሉ። የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች መንግስት ጥፋተኝነቱን በሙሉ እንዲያምን ከጎናቸን እንዲሆኑም እጠይቃለሁ በማለት የመገናኛ ብዙሀንና ሌሎች ግለሰቦችም በደላችንን ለዓለም እንድታደርሱልን ሲሉ ጥሪ በማቅረብ አደራ ይላሉ።

No comments:

Post a Comment