ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቁትና የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ባደረባቸው ድንገተኛ ህምም ማክሰኞ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
ላለፉት 23 አመታት በዚህ በአሜሪካ በስደት ይኖሩ የነበሩት አቶ ፈቃደ የኢህአዴግን ስልጣን መያዝ ተከትሎ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከተባረሩ 42 መምህራን አንዱ እንደነበሩ የህይወት ታሪካቸው ያመለክታል። በዚህ በአሜሪካ በነበሩበት ረጅም ጊዚያቶች አቶ ፈቀደ ሸዋቀና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን፣ ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በንጹሃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተለያዩ መድረኮች ለህዝብ በማሳወቅም ይታወቃሉ።
በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነታቸው ጭምር የሚታወቁት አቶ ፈቃደ በወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ላይ በመቀረብ ሙያዊ ትንታኔን ሲያቀርቡ እንደነበርም የሚታወስ ነው።
ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በንጹህ ሰዎች ላይ የሚፈፅመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተለያዩ መድረኮች ለህዝብ በማሳወቅም ይታወቃል።
በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነታቸው ጭምር የሚታወቁት አቶ ፈቃደ በወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በመቅረብ ሙያዊ ትንታኔን ሲያቀርቡ እንደነበርም የሚታወስ ነው።
በዚህ በአሜሪካ በሜሪላንድ ግዛት ይኖሩ የነበሩት የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር አቶ ፈቃደ በ1985 አም ከዩኒቨርስቲው ከመባረራቸው በፊት ለ10 አመት ያህል በመምህርነት አገልግለው እንደነበርም ለመረዳት ተችሏል።
አቶ ፈቃደ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና የሰብዓዊ መብታቸው እንዲከበርም ሰፊ የማስተባበር ስራን ሲሰሩ መቆየታቸው አይዘነጋም።

No comments:
Post a Comment