ሰኔ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አብዛኛው መምህራን ከድርቁ ጋር ተያይዞ በነበረው የውሃ እጥረት ስጋት ምክንያት በየጊዜው ስራቸውን እየለቀቁ መሄዳቸውን የተናገሩት የትምህርት ባለሙያ በሚለቁ መምህራን ትክ የሚመጡትም ብዙ ሳይሰሩ በመልቀቃቸው የመማር ማስተማሩ ሂደት ተስተጓጉሎ የትምህርቱ ጥራት እየወደቀ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ሰው ከድርቁ ስጋት የተነሳ አካባቢውን በመልቀቁ መምህራንም እንደ ነዋሪው ቀየውን እየለቀቁ ለመሄድ መገደዳቸውን ተናግረው፤ በዚህ ምክንያት የትምህርቱ ስራ እየወደቀ በመሄዱ በቀጣዩ ዓመት ችግሩ ተባብሶ እንዳይቀጥል ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትን መንገድ መንግስት እንዲያፈላልግ ጠይቀዋል፡፡ በተመሳሳይ ዜና በአካባቢው እስካሁን ቀያቸውን ያለቀቁ የድርቁ ተጎጂዎች እንደተናገሩት ህዝቡ ተገቢውን ድጋፍ ባለማግኘቱ ረሃብ ላይ መሆኑን ገልጸው ከጊዜ ወደጊዜ የዝናቡን ሁኔታ በመመልከት ወደ ስደት መጓዝ መጀመሩን ይገልጻሉ፡፡
ድርቁ እንደጀመረም ተጎጂዎች ለቀን ስራ እያሉ በመሄድ ሞተው የቀሩበት ሁኔታ መኖሩን እና አሁንም ህብረተሰቡ ወደተለያዩ ሃገራት መሰደዳቸውን መቀጠላቸውን ተናግረው ከተሰደዱት ተጎጂዎች ከአስር አንዱ ብቻ እየተመለሱ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አሁንም ከመንግስት ለተጎጂዎች ሚቀርበው የእርዳታ እህል እየቀነሰ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን የሚናገሩት ተጎጂ በስተመጨረሻ እየቀረበ ያለው የእርዳታ እህል “ጸበል የመርጨት ያህል ትንሽ ነው!” በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል፡፡
የገዢው መንግስት በተለያዩ ፖለቲካዊ የበዓል ዝግጅቶች ከፍተኛ ወጪዎችን በመመደብ መጠመዱ የድርቁን ጉዳይ ችላ እንዲል እንዳደረገው የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎች “ለዜጎቼ እጨነቃለሁ!” ከሚል መንግስት የማይጠበቅ ስራ መሆኑን ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ለሪፖርተራችን ሰጥተዋል፡፡ ከሰሜን ወሎ ተሰደው የመጡ ዜጎች በባህርዳር ከተማ በድባንቄ መድሃኒያለም አካባቢ በሚገኘው የአትክልት ቆሻሻ መድፊያ ላይ ከእንስሳት ጋር በመሻማት ፍራፍሬ የሚለቅሙ ዜጎች መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ፎቶዎችን በማንሳት ለኢሳት ልከዋል።በወልድያም እንዲሁ እነዚሁ ዜጎች በየቦታው በልመና ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ደግሞ አሁንም በርካታ ዜጎች እየተሰደዱ መሆኑን ወኪላችን ገልጿል።ሰኔ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አብዛኛው መምህራን ከድርቁ ጋር ተያይዞ በነበረው የውሃ እጥረት ስጋት ምክንያት በየጊዜው ስራቸውን እየለቀቁ መሄዳቸውን የተናገሩት የትምህርት ባለሙያ በሚለቁ መምህራን ትክ የሚመጡትም ብዙ ሳይሰሩ በመልቀቃቸው የመማር ማስተማሩ ሂደት ተስተጓጉሎ የትምህርቱ ጥራት እየወደቀ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ሰው ከድርቁ ስጋት የተነሳ አካባቢውን በመልቀቁ መምህራንም እንደ ነዋሪው ቀየውን እየለቀቁ ለመሄድ መገደዳቸውን ተናግረው፤ በዚህ ምክንያት የትምህርቱ ስራ እየወደቀ በመሄዱ በቀጣዩ ዓመት ችግሩ ተባብሶ እንዳይቀጥል ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትን መንገድ መንግስት እንዲያፈላልግ ጠይቀዋል፡፡ በተመሳሳይ ዜና በአካባቢው እስካሁን ቀያቸውን ያለቀቁ የድርቁ ተጎጂዎች እንደተናገሩት ህዝቡ ተገቢውን ድጋፍ ባለማግኘቱ ረሃብ ላይ መሆኑን ገልጸው ከጊዜ ወደጊዜ የዝናቡን ሁኔታ በመመልከት ወደ ስደት መጓዝ መጀመሩን ይገልጻሉ፡፡
ድርቁ እንደጀመረም ተጎጂዎች ለቀን ስራ እያሉ በመሄድ ሞተው የቀሩበት ሁኔታ መኖሩን እና አሁንም ህብረተሰቡ ወደተለያዩ ሃገራት መሰደዳቸውን መቀጠላቸውን ተናግረው ከተሰደዱት ተጎጂዎች ከአስር አንዱ ብቻ እየተመለሱ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አሁንም ከመንግስት ለተጎጂዎች ሚቀርበው የእርዳታ እህል እየቀነሰ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን የሚናገሩት ተጎጂ በስተመጨረሻ እየቀረበ ያለው የእርዳታ እህል “ጸበል የመርጨት ያህል ትንሽ ነው!” በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል፡፡
የገዢው መንግስት በተለያዩ ፖለቲካዊ የበዓል ዝግጅቶች ከፍተኛ ወጪዎችን በመመደብ መጠመዱ የድርቁን ጉዳይ ችላ እንዲል እንዳደረገው የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎች “ለዜጎቼ እጨነቃለሁ!” ከሚል መንግስት የማይጠበቅ ስራ መሆኑን ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ለሪፖርተራችን ሰጥተዋል፡፡ ከሰሜን ወሎ ተሰደው የመጡ ዜጎች በባህርዳር ከተማ በድባንቄ መድሃኒያለም አካባቢ በሚገኘው የአትክልት ቆሻሻ መድፊያ ላይ ከእንስሳት ጋር በመሻማት ፍራፍሬ የሚለቅሙ ዜጎች መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ፎቶዎችን በማንሳት ለኢሳት ልከዋል።በወልድያም እንዲሁ እነዚሁ ዜጎች በየቦታው በልመና ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ደግሞ አሁንም በርካታ ዜጎች እየተሰደዱ መሆኑን ወኪላችን ገልጿል።
No comments:
Post a Comment