Tuesday, June 28, 2016

ቤታቸው በህገወጥ መንገድ ይፈርስባችሁዋላ በመባላቸው ሰዎች ተቃውሞአቸውን ገለጹ

ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ወረዳ 11 በአካባቢው መጠሪያ ቀርሳና ኮንቱማ በሚባሉ አካባቢዎች ቤቶችን በህገወጥ መንገድ ሰርታችሁዋል የተባሉ ነዋሪዎች፣ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ካላፈረሱ ግን መንግስት እንደሚያፈርስባቸው ከተነገራቸው በሁዋላ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።

“አንድ የአራት እናት ልጆችና የአንድ ሳምንት አራስ የሆኑት እናት “ መሄጃ የለኝም፣ መሞቴ ነው ድረሱልኝ “ ብላለች። ልጆቼን የሚረከቡኝ አካል እፈልጋለሁ፣ መንግስት ሊቀብረኝ ነው ፣ በአረብ አገር ለፍቼ የሰራሁትን ቤት አፍርሺ ተብያለሁ፣ ባለቤቱ በአደጋ በቅርቡ ሞተብኝ፣ እርዱኝ “ ብላለች።

“አሁኑኑ ሰባብረን ቆራርጠን እንጥላችሁዋለን፣ እናንተ ከ 5ሺ አትበልጡም፣ እኛ ከአምስት ሺ በላይ የታጠቀ ሃይል አለን፣ ምንም አታመጡም” መባላቸውን የተናገሩት አንድ ግለሰብ ፣ በዚህ ክረምት ከምንወጣ እዚሁ ቢገድሉን እንመርጣለን ብለዋል። ሌላም ሴት እንዲሁ በአረብ አገራት ለፍታ ባገኘችው ገንዘብ የሰራችውን ቤት በሁለት ቀናት ውስጥ አፍርሺ መባሉን  ተናግራለች።
በአዲስ አበባ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ ቤቶችን ገንብታችሁዋል በሚል ቤቶቻቸው ከፈረሱባቸው በሁዋላ ለችግር ተዳርገዋል።

No comments:

Post a Comment