ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ያለው የዘይት አቅርቦት ከጊዜ ወደ ጊዜ በ ነዋሪዎች ህይወት ላይ ችግር ሲፈጥር ቢቆይም፣ በአማራ ክልል ግን የከፋ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ገዢው ፓርቲ በፋሲካ ሰሞን በነፍስ ወከፍ አንድ ሊትር ዘይት ካከፋፋለ በሁዋላ እስካሁን ዘይት የሚባል ነገር አልቀረበም። ክፍፍሉን ፍትሃዊ እናደርጋለን በማለት ለነዋሪዎች የዘይት የሬሽን ካርድ ያደለው አስተዳደሩ፣ ቃል በገባው ጊዜ ማቅረብ ባለመቻሉ ፣ አብዛኛው ህዝብ ምግቡን ያለዘይት እየሰራ ነው። መክፈል የሚችሉ ዜጎች አንድ ሊትር የኑግ ዘይት በ56 ብር በመክፈል ለመጠቀም ተገደዋል።
የቅባት እህል ወደ ወጭ የምትልክ ሃገር ዜጎች ዘይት በማጣት መቸገራቸው እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ፡ሁሉን አሰራር በመጠቅለል የህብረተሰቡን ፍላጎት አሟላለሁ የሚለው ‹‹ አለ በጅምላ ›› የተባለው መንግስታዊ ድርጅት ምን ይሰራ ነው ሲሉ ይጠይቃሉ።
No comments:
Post a Comment