Friday, June 17, 2016

እነ አቶ አባይ ወልዱ ከአውስትራሊያዋ ታስማኒያ ግዛት ለቀው እንዲወጡ ተደረገ

ሰኔ ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለገንዘብ ማሰባሰብና ለቅስቀሳ ስራ በአውስትራሊያ የተገኙት የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ሙክታር ከድር እና ሶማሊ ክልል

ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሃመድ በአካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያን ያጋጣመቻውን ተቃውሞ ተከትሎ የአገሪቱ ፖሊስ ዋና ከተማዋን ሆባርትን ለቀው እንዲወጡ በማዘዝ፣  በመጡበት አውሮፕላን ተመልሰዋል።
ሶስቱ ባለስልጣኖች ቀደም ብሎ በካምቤራና በሜልበርን የደረሰባቸውን ተቃውሞ ተከትሎ ደጋፊዎቻቸውን ኢትዮጵያውያን በብዛት አይገኙበትም ተብሎ በሚታሰበው የታስማኒያ ግዛት ለመሰብሰብ አስቀድመው ቢገኝም፣ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሰባስበው ተቃውሞ በማሰማታቸው ፖሊስ ለጸጥታ አስቸገሪ ነው ከተማዋውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል።

በታስማኒያ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ሰብሳቢ አቶ ደሴ አሰፋ ሰዎቹ እንዲወጡ ለፖሊስ ማመልከታቸውንና ፖሊስም ሁኔታውን በመረዳት እንዲወጡ አድርጓል ብለዋል። የኦሮሞ ኮሚኒቲ ሰብሳቢ አቶ ዘይድ ሙሃመድም በበኩላቸው በአውስትራሊያ በሶስት ግዛቶች ለማድረግ ያቀዱት ስብሰባ ከተጨናገፈ በሁዋላ ወደ አካባቢያቸው እንደሚመጡ መረጃ ሲደርሳቸው ሌሊቱን በሙሉ በአየር ማረፊያ ሲጠብቁዋቸው ማደራቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻም ያረፉበትን ሁቴል እንዳገኙ የኦሮሞ ኮሚኒቴ አመራሮችና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት በጋራ በመጠራራት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ኢትዮጵያውያን ስራቸውን እየተው በመምጣት ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ ፖሊስ የህዝቡን ጥያቄ በመስማት ከከተማዋ እንዲወጡ አድርጓል። በከፍተኛ ድንጋጤና ፍርሃት በፖሊስ ታጅበው ወደ አየር ማርፊያ ከሄዱም በሁዋላ ተከታትለው ተቃውሞአቸውን መግለጻቸውን ተናግረዋል
በሌላ በኩል በቤልጂየም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ትናንት በአውሮፓ ህብረት ፊት ለፊት ተቃውሞ አሰምተዋል።  አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የልማት ትብብር ለመፈራረም በቤልጂየም መገኘታቸውን የተቃወሙት ኢትዮጵያውያኑ ፣ ወያኔ ከኦሮምያ፣ አማራ፣ አፋር፣ ኦጋዴን፣ ጋምቤላ ለቀህ ውጣ፣ ሰላማዊ ዜጎችን መግደል አቁም ፣ የአውሮፓ ህብረት የወያኔን ገዳዮችና ወንጀለኞችን መደገፍ አቁም የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል።

No comments:

Post a Comment