ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተካሄደውን የግንቦት ወር ምርጫ 1997 ዓመተ ምህረት ተከትሎ “ድምጻችን ይከበር!” በማለት ሰልፍ በመውጣታቸው ሳቢያ በመንግስት ታጣቂዎች የተገደሉት የሰኔ 1 ሰ ማዕታት 11ኛ ዓመት ዛሬ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ታስቦ ውሏል።
በመንግስት ደረጃ በወጣው ሪፖርት ሰኔ 1 ቀን የተገደሉት ሰማዕታት 42 እንደሆኑ ቢነገርም፤ በወቅቱ የሀዘነኞችን ቁጥር ዋቢ በቅርበት የተከታተሉ ገለልተኛ ወገኖች ግን የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ሲናገሩ ቆይተዋል። “የሰጠነው ድምጽ ይከበር!” በማለታቸው ከተገደሉት ከነዚህ ሰማ ዕታት መካከል፣ መንትያ ወንድማማቾች፣ አዛውንቶች፣ እናቶችና የ15 ዓመት ታዳጊ ህጻናት ይገኙበታል።
በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማምጣት በተደረገው ሰላማዊ ትግል ህይወታቸውን የሰጡት የእነዚህ ሰማዕታት 11ኛ ዓመት እንደ ፌስቡክና ትዊተር በመሣሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ሲዘከር ውሏል።
No comments:
Post a Comment