ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብር ወንጀል ተከሰው በፌደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ የተለቀቁት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች አቶ ሃብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባል አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ የአረና አባልና ጸሃፊ መምህር አብርሃ ደስታ እንዲሁም አቶ አብራሃም ሰሎሞን አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ሳይቀርቡ በሌሉበት በድጋሜ ለጥቅምት 29/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷቸዋል፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ ጥቅምት 17/2008 ዓ.ም ከአርባ ምንጭ ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት እስረኞች ቅዳሜ እለት አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል አቶ ሉሉ መሰለ፣ አለም ክንፉ፣ ደረጀ አደመ፣ አየለች አበበ፣ አስማው የሚገኙበት ሲሆን በማግስቱ እሁድ 21 እስረኞች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት ተዛውረዋል።
አብዛኞቹ እስረኞች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው። ብዙዎቹ በከተማው ከተበተነው የአርበኞች ግንቦት7 የቅስቀሳ ጽሁፍ ጋር በተያያዘ የተያዙ ናቸው።
አብዛኞቹ እስረኞች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው። ብዙዎቹ በከተማው ከተበተነው የአርበኞች ግንቦት7 የቅስቀሳ ጽሁፍ ጋር በተያያዘ የተያዙ ናቸው።
No comments:
Post a Comment