ኢሳት ዜና :-ሳሙኤል ጋዲሳ ገለታ የተባለው የደህንነት አባል ጥቅምት 03/2008 ዓ.ም ፣ በመኪና አከራይነት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙትን አቶ ተክሉ ቀጄላን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባል እንደሆንክ ደርሸብሃለሁ በማለት አስፈራርተው 30 ሺ ብር ጽዮን ሆቴል ውስጥ ሲቀበሉ፣ ግለሰቡ አስቀድመው ለፖሊስ አመልክተው ስለነበር፣ የደህንነት አባሉ ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል። ፖሊስ በገንዘቡ ላይ ማህተም በማሰራፉ የደህንነት አባሉ ድርጊቱን ሊክድ አልቻለም።
የደህንነት አባሉን መያዝ ተከትሎ የኦሮምያ ክልል መስተዳደር ባለስልጣናት ድርጊቱ ገጽታችንን ያበላሻል በሚል ፣ ባለፈው ሳምንት በፖሊስ ፕሮግራም ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት እንዳይቀርብ አስደርገዋል። የፖሊስ ምንጮች እንደሚሉት የደህንነት አባሉ በቁጥጥር ስር እንዲውል የጠቆሙ ሰዎች፣ በደህንነቶች እየተጠሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ምንም እንኳ የደህንነት ሰራተኛው አሁንም ድረስ ማእከላዊ ታስሮ ቢገኝም፣ክስ እንዳይመሰረትበት ለማድረግ ባለስልጣናት በመሯሯጥ ላይ ናቸው።
No comments:
Post a Comment