ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ሰገን ዞን የኮንሶ ወረዳ ሕዝብ በዞን ደረጃ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር መጠየቁን ተከትሎ የክልሉ መንግስት ልዩ ታጣቂ ኃይል ወደአካባቢው በማስገባት ነዋሪዎችን በማሰር፣ በመደብደብ እና በማስፈራራት ላይ ይገኛል። የዞኑ ባለስልጣናት ሕዝቡ ተሰብስቦ የዞን ይሰጠን ጥያቄ አላቀረብንም በማለት እንዲያወግዝ በማስጨነቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትየመብት ጥያቄው አንቀሳቀሾች ናቸው የተባሉ የወረዳውን ፖሊስ አዛዥ ጨምሮ የተለያዩ የወረዳ አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞች መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
የአካባቢው ባህላዊ ንጉስና የኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ካላ ገዛሕኝ ፣ ህዝቡ ጥያቄዎን ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ቢያቀርብም፣ የአካባቢው ባለስልጣናት ጥያቄው የግንቦት7 እና የሰማያዊ ፓርቲ ነው በማለት የህዝቡን ጥያቄ ፖለቲካዊ ይዘት በመስጠት ለማጨናገፍ መሞከራቸው ውጥረቱን እንዳባባሰው ተናግረዋል። በተመሳሳይ ዜናም ጥቅምት27፣ 2008 ዓም በደቡብ ክልል- በከምባታ ጠምባሮ ዞን በዶንጋ ብሄረሰብ የተነሳውን የማንነት ጥያቄ ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት በሃደሮ ከተማ እስካሁን 10 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
ብሄረሰቡ ባህሉን እንዳያደብር፣ ቋንቋውን እንዳያሰድግ በየትኛውም የመንግስት መዋቅር ስያሜ ውስጥ እንዳይካተት ተደርጓል በመላት ተቃውሞ ያሰማሉ።
ብሄረሰቡ ባህሉን እንዳያደብር፣ ቋንቋውን እንዳያሰድግ በየትኛውም የመንግስት መዋቅር ስያሜ ውስጥ እንዳይካተት ተደርጓል በመላት ተቃውሞ ያሰማሉ።
No comments:
Post a Comment