Monday, November 16, 2015

እነ አቶ ሀብታሙ አያሌው አቃቤ ህግ የጠየቀው ይግባኝ ተቀባይነት አገኘ

ኀዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ተበይኖላቸው የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የጠየቀው ይግባኝ ያስቀርባል በመባሉ ክሱ እንደገና ሊታይ መሆኑን ነገረ ኢትዮጵአ ዘግቧል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ‹‹ይግባኙ ያስቀርባል ” በማለት መወሰኑን ተከትሎ ይግባኝ የተጠየቀባቸው ተከሳሾች ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃም ሰለሞን በቀረበባቸው ይግባኝ ላይ በአካል ቀርበው የቃል ክርክር ለማድረግ ለህዳር 29/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሁሉም ተከሳሾች አሁንም ድረስ በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

No comments:

Post a Comment