Monday, November 9, 2015

የሶማሊያ የፓርላማ አባል የኢትዮጵያ ጦር መኖር ግጭቶችን እንዳባባሰው ተናገሩ

ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጦር ስር ካሉት ሰራዊቶች ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሚገኝበት ጌዶ አውራጃ ውስጥ በሚፈጽማቸው ዘግናኝ ግፎች ምክንያት በአካባቢው ነዋሪዎች እንደማይፈለግና ለአገራቸው ሰላም ማጣት የኢትዮጵያ ጦር ተጠያቂ ነው ሲሉ የሶማሊያ ፌዴራል ፓርላማ አባል ማህመድ አሊ መጋን አስታወቁ።

የኢትዮጵያ ጦር ድብቅ ዓላማ ይዞ በጌዶ ግዛት የፖለቲካ ልዩነቶችን በማስፋት ነዋሪዎቹ እርስበርስ እንዲጋደሉ በማሴር የአካባቢውን ሰላም እያናጋ ያለ በመሆኑ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የደም መቃባቱን ለማስቆም ጥረት እንዲያደርጉና የኢትዮጵያ ጦር ካለምንም ቅድመ ሁኔታ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ተማጽኗቸውን አቅርበዋል ሲል ዲፕሎማት ኒውስ ኔትወርክ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment