ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ተሜ) በዝዋይ ማጎሪያ ቤት ውስጥ በጣም መታመሙን ወንድሙ
ተመስገን እጅጉን በጣም ታሞል። ለተመስገን በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ህክምና የለም።
ከ24 ቀናት በኃላ በዐይናችን እንድናይው “ሲፈርዱ” ሲፈልጋቸው ከልክለው ሲያሰኛቸው ስለሚፈቅዱ ፈቀዱ ከማለት ፈረዱ ማለት ይሻላል ብዬ ነው። ዛሬ ህዳር 8/2008ዓ.ም ዝዋይ እስር ቤት ተመስገንን ዐይቼዋለሁ። “እጅጉን በጣም ታሟል” ከወገቡ ህመም በሻገር “የግራው ጆሮ መድማት” ጀምሮል። የሚደማውን ጆሮ ቶሎ ቶሎ እየጠረገ በመከራ ነው የሚያናግረኝ። ሊያናግረኝ አፉን ማንቀሳቀስ ሲጀምር የጆሮው ህመም ንግግሩን ያቆርጠዋል። እኔ ህመሙን ላለማየት አይኔን የማሳርፈበት ቦታ አጣለሁ። ከበውን የቆሙት ወታደሮች እና ሀላፊዎች ህመሙን አይተዋል። በተመስገን ላይ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ሌላ እስር ቤት ሰርተውለታል ከስረኞች የሚገለልበት፣ ምንም አይነት ህክምና የማያገኝበት እስር ቤት።
No comments:
Post a Comment