(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
በጎንደር-ላይ አርማጭሆ ማውራ፣ ገንበራ፣ ጎንደሮች ማርያም፣ ሮቢት፣ ጋባ እና በሌሎች ቦታዎች በገበሬዎችና በህወሓት ጦር መካከል ሲካሄድ በሰነበተው ውጊያ አስካሁን በትንሹ ከ90 በላይ የልዩ ኃይል ጦር አባላት ሲገደሉ ከ150 በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡ ከገበሬዎች በኩል የተሰዋ አንድ አለበል የተባለ ወጣት ብቻ ሲሆን የህወሓት ፌደራል ፖሊሶች 19 ህፃናትና ሴቶችን በጩቤ አርደው በመግደል የአካባቢውን ህዝብ ተበቅለዋል፡፡
ከጎንደር ከተማ 20 ኪ.ሜ በማይበልጥ ርቀት ውስጥ ማውራ መንደር ላይ በገበሬዎችና በህወሓት ልዩ ኃይል ጦር መካከል የተጀመረው ጦርነት በላይ አርማጭሆ የሚገኙ ቀየዎችን ከማዳረስ አልፎ ወደ ታች አርማጭሆና ጭልጋ ጭምር ተስፋፍቷል፡፡ ከትናንት በፊት በጭልጋ ጮንጮቅ በተካሄደው ውጊያ ከ4 በላይ ፌደራል ፖሊሶች ተገድለዋል፡፡ ባጠቃላይ የጎንደር ገበሬዎች ማለት በሚቻል ሁኔታ ህወሓትን ለመውጋት ተባብረው በአንድነት ታጥቀው ተነስተዋል፡፡
በማውራና በሌሎች የላይ አርማጭሆ ወረዳ ቀበሌዎች ሲካሄድ በሰነበተው ውጊያ ገበሬዎች 4 ፒ.ኬ መትረየሶችን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ ከነተተኳሹ ማርከዋል፡፡ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ የህወሓት መራሹ ልዩ ኃይል፣ ፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት አባላት ስርዓቱን እየከዱ ከነትጥቃቸው ገበሬዎቹን በመቀላቀል ላይ ናቸው፡፡ ሁለት የልዩ ኃይል አባላት መትረየስ ይዘው ከገበሬዎቹ ጎን በመሰለፍ አፈሙዛቸውን ወደ ህወሓት ማዞራቸው ታውቋል፡፡
በህወሓት አገዛዝ ላይ ያመፁት የላይ አርማጭሆ ገበሬዎች በየቀዬዎቻቸው የሚገኙ ገዥ መሬቶችንና ጫካዎችን ይዘው ምሽግ በመቆፈር የህወሓትን ጦር ባጠገባቸው ፈፅሞ ድርሽ ሊያሰኙት ባለመቻላቸው የህወሓት ፌደራል ፖሊሶች ባዶ የሆኑ መንደሮችን ወረው በተለይም በማውራ ከ19 የሚልቁ ህፃናትና ሴቶችን በጩቤ አርደው በመግደል አረመኔያዊነት የተላበሰ የበቀል እርምጃ ወስደው የሊቢያውን የ"ISIS" ድርጊት ደግመውታል፡፡ ከታረዱት ሴቶች ውስጥ ሁለት እህትማማቾች ይገኙበታል፡፡
ህወሓት ከልዩ ኃይሉና ከፌደራል ፖሊስ ጦሩ በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መከላከያ ሰራዊትም በአካባቢው አስፍሯል፡፡
በአርማጭሆ ገበሬና በህወሓት ጦር መካከል ፍጥጫው አይሏል...
No comments:
Post a Comment