Friday, November 6, 2015

‪#‎በላይ‬ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ዙሪያ፣ ሌሎች ከተሞችና ቀበሌዎች ውስጥ በርካታ ትምህርት ቤቶች ማስተማር አቁመው እየተዘጉ መሆናቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገለፁ፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
‪#‎በላይ‬ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ዙሪያ፣ ሌሎች ከተሞችና ቀበሌዎች ውስጥ በርካታ ትምህርት ቤቶች ማስተማር አቁመው እየተዘጉ መሆናቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገለፁ፡፡
‪#‎የወላይታ‬ ህዝብ የህወሓት አገዛዝ በሚያደርስበት የከፋ አስተዳደራዊ ግፍና በደል በእጅጉ ተማሮ የጭቆና ቀንበሩን ባንድነት ተባብሮ ለመስበር ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ማስታወቁ ተዘገበ፡፡
‪#‎በጎንደር‬-አዘዞ፣ ጠዳ፣ ማክሰኝነት፣ ቆላ ድባ፣ ደልጊ፣ ጭልጋና ሌሎች የወረዳ ከተሞች ላይ የመጠጥ ውሃና መብራት አግልግሎት በመቋረጡ ነዋሪዎች ችግር ላይ ናቸው፡፡


====================================================
በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ዙሪያ፣ ሌሎች ከተሞችና ቀበሌዎች ውስጥ በርካታ ትምህርት ቤቶች ማስተማር አቁመው እየተዘጉ መሆናቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገለፁ፡፡
ምንጮቻችን እንደገለፁት በላይ አርማጭሆ በትክል ድንጋይ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ ት/ቤቶች ማስተማር አቁመው ለመዘጋት የበቁት መምህራኑ "ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ" በሚል ሰበብ በህወሓት ደህንነቶችና ፌደራል ፖሊሶች እየታፈኑ ወደ ወህኒ ስለሚጋዙ እና ተማሪዎች ደግሞ በበኩላቸው ከእነሱ የቀደሙትን ወንድምና አህቶቻቸውን በማየት "ብንማርም ምንም ለውጥ አናመጣም" ከሚል በመነጨ ተስፋ ቆርጠው ለመማር ፈቃደኛ ባለመሆን ከትምህርት ገበታቸው መቅረት ምክንያት ነው፡፡
በላይ አርማጭሆ በአነስተኛ ደሞዝ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ እስሩና ወከባው እያየለ በመምጣቱ ቀላል የማይባሉ መምህራን ሳይወዱ በግድ ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እየለቀቁ በመሰደድ ላይ ናቸው፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ በትክል ድንጋይና አካባቢው ለገበሬው ህዝብ የመጓጓዣ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ባጃጆችና ሞተር ሳይክሎች በጠቅላላ በህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ኃይሎች ታግደው ስራ አቁመዋል፡፡
ባጃጆችና ሞተር ሳይክሎች በጠቅላላ በትክል ድንጋይና በዙሪያው እንዳይንቀሳቀሱ በጥብቅ የተከለከሉበት ዋነኛ ምክንያት በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ ለሚገመቱት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች አገልግሎት ሊሰጡና የጦር መሳሪያ ሊያጓጉዙ ይችላሉ ከሚል ስጋት በመነጨ ነው፡፡
ይህንን አግባብነት የሌለው እገዳ የተቃወሙ በርካታ የባጃጅና የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ለእስር ተዳርገዋል፡፡
የወላይታ ህዝብ የህወሓት አገዛዝ በሚያደርስበት የከፋ አስተዳደራዊ ግፍና በደል በእጅጉ ተማሮ የጭቆና ቀንበሩን ባንድነት ተባብሮ ለመስበር ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ማስታወቁ ተዘገበ፡፡
ህወሓት ጉዳዩን እንዲያስፈፅሙለት የወከላቸው የአካባቢው አሻንጉሊት ባለስልጣናት በህዝቡ ላይ ገደብ የሌላቸው ቆራጭ ፈላጮች ሆነው በከፍተኛ የአፈና እና ዝርፊያ ተግባሮች ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
በወላይታ ፍትህ፣ ዳኝነት፣ ሰብዓዊነትና ሌሎችም እሴቶች ከአገዛዙ ሹሞች ዘንድ ትንሽ እንኳን እንጥፍጣፊ ሳይቀር ፈፅመው መጥፋታቸውን ህዝቡ በከፍተኛ ምሬት ሲገልፅ እየተደመጠ ነው፡፡
የወላይታ ትራፊክ ፖሊሶች ከአካባቢው የህወሓት ቆራጭ ፈላጭ የደህዴግ ሰዎች ጋር በመሞዳሞድ ለአሽከርካሪዎች የቀን ጅብ ሆነውባቸዋል፡፡
ባጠቃላይ የወላይታ ህዝብ ሆድ ብሶታል፡፡
በጎንደር-አዘዞ፣ ጠዳ፣ ማክሰኝነት፣ ቆላ ድባ፣ ደልጊ፣ ጭልጋና ሌሎች የወረዳ ከተሞች ላይ የመጠጥ ውሃና መብራት አግልግሎት በመቋረጡ ነዋሪዎች ችግር ላይ ናቸው፡፡
የህወሓት አገዛዝ በተለየ ሁኔታ በመሰረተ ልማት ሆነ ብሎ እያዳከማቸው ከሚገኙት የኢትዮጵያ ከተሞች ጎንደር አንዷ እና ዋነኛዋ ናት፡፡ ህወሓት ጎንደር እድገት እንዳታሳይ ብቻ ሳይሆን ባሏት የቆዩ ታሪካዊ እሴቶችና ውበቷ ከዘመን ዘመን እየቆረቆዘች እንድትመጣ ተቆጥረው የማያልቁ ሸፍጦችን ፈፅሟል፡፡ በደርግ ዘመን ጎሃ ተራራ ላይ የተተከለውን ከተማዋን በበቂ ሁኔታ ሊያዳርስ የሚችል ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለውን ግዙፍ ጀነሬተር በጉልበቱ ነቅሎ ወደ ትግራይ በማስጫን ሃውዜን ላይ መትከሉን ሁሉም የጎንደር ነዋሪ በከፍተኛ ፀፀትና ቁጭት የሚገልፀው የሀወሓት ዓይን ያወጣ የዘረፋ ተግባር ነው፡፡
በተጨማሪም በአለፋ ጣቁሳ-ደልጊ እና ደምቢያ-ቆላ ድባ ይገኙ የነበሩ ሁለት ታላላቅ የተግባረ ዕድ ት/ቤቶችን ቁሳቁሶች ሙልጭ አድርጎ በመዝረፍ ወደ ትግራይ ጭኗቸዋል፡፡ ከዕደ ጥበብ መማሪያ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ወድ ውድ ቁሳቁሶች በተጨማሪ አቢያተ መፅሐፍትም አብረው ተዘርፈው የማንበቢያ አዳራሾች መቀመጫ ወንበሮችን ብቻ ታቅፈው ኦና ሆነው ቀርተዋል፡፡
በጎንደር ከተማም ሆነ በቆላ ድባና በደልጊ የተፈፀመውን ከበቀል የመነጨ የህወሓት የማራቆት ነውረኛ ተግባር ህዝቡ ዝም ብሎ በፍርሃት እጆቹን አጣጥፎ አልተመለከተውም ነበር፤ ነገር ግን ጎጠኛው የህወሓት ቡድን ታንክ አሰልፎና መትረየስ ጠምዶ ያቃተውን ንጥቂያ አሳቻ ሰዓት ጠብቆና አዘናግቶ በደረቅ ሌሊት ህዝቡ በእንቅልፍ ላይ ሆኖ ባልሰማበትና ባላየበት ሊያከናውነው ችሏል፡፡
ሁለት ታላላቅ ጅረቶች አንደኛው ከሁለት ሰንጥቋት ሌላኛው አካሏት የሚያልፉባት ጥንታዊቷ የጎንደር ከተማ በመጠጥ ውሃ ችጋር ፍዳዋን እያየች በጨለማ ውስጥ እንድትኖር ህወሓት የተባለው የባንዳ ልጆች ቡድን ፈርዶባታል፡፡ በተለይም ደግሞ በወረዳ ከተሞቿ ችግሩ እጅግ በጣም የከፋና አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፡፡
በጣና ሐይቅ አፍንጫ ላይ የሚገኙት ደልጊ፣ ማክሰኝትና ቆላ ድባ እንዲሁም ጭልጋና ሌሎች የወረዳ ከተሞች የሚጠጣ ጠብታ ውሃ አሮባቸው ከእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ደግሞ በድቅድቅ ጨለማ ተውጠው ይገኛሉ፡፡
በእነዚሀ ጎስቋላ የጎንደር ወረዳዎች በተለይም ደግሞ በማክሰኝት ከተማ የውሃ ልማትና የመብራት ኃይል ቅርንጫፍ መ/ቤቶች የህወሓት ሎሌ የሆኑ የወረዳው ሹሞች መኖሪያ ቤቶች በሚገኙባቸው ሰፈሮች እየለዩ ውሃ በገፍ በመልቀቅና መብራት በማብራት ድሃውን ህዝብ ዘወትር ያስጠሙታል፤ በጨለማ ያሳድሩታል፡፡
በተጨማሪም የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የህወሓት አገልጋይ ካቢኔዎች ሲያሻቸው ጠዳ አሊያም ጎንደር እንዲሁም እስከ ባህር ዳር ድረስ ተጉዘው ውሃ በመቃረም የህዝቡ ንብረት በሆኑት የመስሪያ ቤት ተሽከርካሪዎች በበርሜል ጭነው እያጓጓዙ በመጠቀም ድሃውን ህዝብ እንቁልልጭ ይሉታል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በእንፍራንዝ ከተማም ነዋሪዎች የሚጠጡት ውሃ የላቸውም፡፡ የከተማዋ የህወሓት አሻንጉሊት የብአዴን አባላት የሆኑ ሹሞች የመጠጥ ውሃውን ችግር ለመፍታት በሚል ህብረተሰቡን ገንዘብ እንዲያዋጣ ካስገደዱት በኋላ በብዙህ ሺህ የሚቆጠረውን ብር ወደየ ግል ኪሳቸው አስገብተውት በህዝቡና በሹሞች መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቶ ነበር፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)

No comments:

Post a Comment