Friday, October 2, 2015

ሱዳን ከኤርትራ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋገጠች።

መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቢዪን እንደዘገበው ፕሬዚዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር ይህን ያረጋገጡት፤ ዛሬ ሀሙስ ከኤርትራው የፋይናንስ ሚኒስቴር ከአቶ ብርሀኔ ሀብተማርያም ጋር ካርቱም ውስጥ ባደረጉት ውይይት ነው።

ሰሞኑን ካርቱም በኤርትራ የነበሩ የኢትዮጰያ አማጽያንን ወደ ኢትዮጵያ አሸጋግራለች የሚል መረጃ መውጣቱን ተከትሎ በኤርትራና በሱዳን መካከል ያለው ግንኙነት ሊሻክር እንደሚችል እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ፤ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የኤርትራውን ባለስልጣን ተቀብለው ሲያነጋግሩ ” ወዳጅነታችን ይቅደም!” ማለታቸው ተሰምቷል።

ከዚህም ባሻገር በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት በሚጨምርበትና ሀገራቱን በአውራ ጎዳና መንገዶች ማገናኘት በሚቻልበት ሁኔታ አልበሽርና የኤርትራው የፋይናንስ ሚኒስተር ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ሱዳን ትሪቢዩን አመልክቷል።
ሀገራቱ አሁን ያደረጉት ወይይት -በመስከረም አጋማሽ በኤርትራና በሱዳን ወታደሮች መካከል ድንበር ላይ ግጭት እንደተከሰተ ከተነገረ ውዲህ በዓይነቱ ለየት ያለ ነውም በሏል-ጋዜጣው።
ፕሬዚዳንት አልበሽር በዚሁ ውይይት ላይ በተደጋጋሚ ፦”ከኤርትራ ጋር የነበረን ጠንካራ ግንኙነትና ወዳጅነት ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የሁለቱ ሀገራት የፋይናናስና የኢኮኖሚ ሚኒስትሮች ሀገራቱ ነጻ የንግድ ቀጣና በሚመሰርቱበት መንገድ መወያየታቸው ተመልክቷል።

No comments:

Post a Comment