መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጸጥታ እና ከደህንነት ዋስትና ማጣት ጋር በተያያዘ፣ ስራ ያቋረጡት የመንግስት ሰራተኞች፣ ከወረዳው ባለስልጣናት ጋር ተናንት የተወያዩ ቢሆንም፣ መተማመን ላይ ባለመድረሳቸው አብዛኞቹ ዛሬም ስራ ሳይጀምሩ ቀርተዋል።
አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች በግዴታ ስራ እንዲጀምሩ ቢደረግም፣ ብዙዎቹ በአድማው ቀጥለውበታል።
የሀመር ወረዳ አርብቶአደሮች በየጊዜው በሚሰነዝሩት ጥቃት የፖሊስ፣ የመከላከያና የልዩ ሃይል አባላትን ጨምሮ ነዋሪዎች ተገድለዋል። በየጊዜው የሚፈጸመው ግድያ መጨመር፣ ሰራተኞች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ስራቸውን ያለስጋት ለማከናወን አላስቻላቸውም።
የሰሞኑን የስራ ማቆም አድማ እንደገና የተቀሰቀሰው ባለፈው ማክሰኞ ወንድምነህ እሸቴ የተባለ የኩርሜ ማዘጋጃ ሰራተኛ በአርብቶ አደሮች መገደሉን ተከትሎ ነው። የሟቹን አስከሬን ለማንሳት ወደ ቀበሌው በመጓዝ ላይ የነበሩት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አይቼም በአርብቶ አደሮች የመገገል ሙከራ ተደርጎባቸዋል።

No comments:
Post a Comment