ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናት ጀምሮ የአርበኞች ግንቦት7 አባሎች በሰገን ዞን ኮንሶ ወረዳ ውስጥ ገብተዋል በሚል የፖሊስ አባላት በከተማው የሚገኙ ወጣቶችን ሲያድኑ ከዋሉ በሁዋላ ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶችን ይዘው አስረዋል።
በአካባቢው ሰሞኑን በፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸመ የተባለ ጥቃትና ወጣቱን የሚያነሳሱ በራሪ ወረቀቶች መበተናቸው ለአሰሳው ተጨማሪ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ከዞን ምስረታ ጥያቄ ጋር በተያያዘ የመንግስት ስራተኞች እያደረጉት አለው የስራ ማቆም አድማ ቀጥሎአል። አድማውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እና የመንግስት ስራዎች ቆመዋል። የተቃዋሚ ሃይሎችን እያሳደዱና እያሰሩ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል
በሌላ በኩል ደግሞ በአርባምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅን ጨምሮ የታሰሩ በርካታ ወጣቶች፣ የአርበኞች ግንቦት7 ደጋፊዎች ናችሁ በሚል ከታፈሱ በሁዋላ አዲስ አበባ ማእከላዊ እስር ቤት ተወስዷል።
No comments:
Post a Comment