መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት አሚሶል ስር ያለውን ንብረነታቸው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት የሆኑትን ሁለት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በደቡባዊ ምዕራብ ሶማሊያ በጌዶ ግዛት በደፈጣ ውጊያ ማውደሙን አልሸባብ አስታውቋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በአሊላን መንደር ውስጥ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ሰራዊት መሃከል ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ ነው። በአርፒጂ የጦር መሳሪያ ተሽከርካሪዎቹ መመታታቸውን የአካባቢው የዐይን እማኞች ተናግረዋል። በአልሸባብ ጥቃት ብዛት ያለቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውን ራዲዮ ሸበሌ ቢዘግብም፣ ከገለልተኛ ምንጮች አለማረጋገጡን አስታውቋል።
ባለፈው ሃምሌ ወር ላይ የአፍሪካ ሕብረት ጦር አሚሶም በምድር እና በአየር ላይ ጥቃት በመፈጸም ስትራቴጂክ ከተማ የሆነችውን ዋርዴርን ከአልሸባብ እጅ አስለቅቆ የያዘ ሲሆን ፣ በወቅቱ ብዙ ሰላማዊ ሰዎችና የሰራዊት አባላት መገደላቸው ማእረግ ድረገጽ በሰበር ዜናው ዘግቧል።
ባለፈው ሃምሌ ወር ላይ የአፍሪካ ሕብረት ጦር አሚሶም በምድር እና በአየር ላይ ጥቃት በመፈጸም ስትራቴጂክ ከተማ የሆነችውን ዋርዴርን ከአልሸባብ እጅ አስለቅቆ የያዘ ሲሆን ፣ በወቅቱ ብዙ ሰላማዊ ሰዎችና የሰራዊት አባላት መገደላቸው ማእረግ ድረገጽ በሰበር ዜናው ዘግቧል።
በሶማሊያ ከተሰማራው የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ አገራት ውስጥ አብዛኞቹ የደረሰባቸውን የሰራዊት ሞትና ቁስለኛ ለ ሕዝባቸው በየወቅቱ የሚገልፁ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት በሰራዊቱ ላይ ስለደረሰው ጉዳት ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ለአንድም ቀን ለፓርላማ አባላት እንኳ ገልጾ አያውቅም። የሟችና የጉዳተኛ ቤተሰቦችም ስለ ልጆቻቸው ምንም ዓይነት በቂ መረጃ አግኝተው አያውቁም ሲል ዘጋቢያችን አስተያየቱን ገልጿል።
No comments:
Post a Comment