ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በፍቼ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት መስሪያ ቤትስራችንን በአግባቡ ሊያሰራን አልቻለም በሚል ምክንያት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከትናንት ጀምረው የስራማቆም አድማ አድርገዋል።
የከተማው መንገድ ትራንስፖርት ባጃጅ ለመንዳት የታክሲ አንድ ፈቃድ መያዝ ያስፈልጋል የሚል መመሪያ ያወጣ ሲሆን፣ በሶስተኛ መንጃ ፈቃድ ሲያሽከረክር የተገኘ ሹፌር 2 ሺ 500 ብር ይቀጣል። የቅጣቱን መጠንና መመሪያውን የተቃወሙት ሹፌሮች አድማቸውን ለምን ያክል ጊዜ እንደሚቀጥሉበት የታወቀ ነገር የለም።
No comments:
Post a Comment