ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በማላ ዊ የድንበር ጠባቂዎች የተያዙ ከ317 በላይ ኢትጵያዊያን ስደተኞች በተለያዩ እስርቤቶች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው መሆኑን አጃን ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
የማላዊ ፍርድ ቤት በስደተኞች ላይ የእስር ቅጣትና ስድሳ አምስት የአሜሪካን ዶላር መቀጮ የጣለባቸው ሲሆን ፣ አብዛሃኞቹ ከስድስት ወራት በላይ በእስር ያሳለፉ አሳልፈዋል። ወደ አገራቸው ለመመለስ ቢፈልጉም ከ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል ጉዳያቸውን የሚከታተልላቸው አካል ባለመኖሩ የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት ስደተኞች እስር ቤት ውስጥ ለመቆየት ተገደዋል።
የማላዊ መንግስት የበጀት እጥረት ስላለብን እስረኞቹን ለማጓጓዝ አንችልም የሚል ምክንያት ያቀረበ ሲሆን፣ ከረድኤት ድርጅቶች እገዛ እፈልጋለሁም ብሏል።ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም በበኩሉ ስደተኞቹን ለመመለስ ከ200,000 የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚያስፈልገው ገልጿል።
በተጨማሪም ዓለማቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን እንዳስታወቀው እስርቤቱ የተጨናነቀና ንፅሕና የጎደለው በመሆኑ ስደተኞቹ ለምግብ እጥረት ፣ ለወባ፣ለሳንባና ለቆዳ በሽታዎች መጋለጣቸውን ጠቅሷል።
ብዙ ተስፋ ሰንቀው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናትና የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ከመንገድ ከቀሩት ወጣቶች አንዱ የሆነው የ15 ዓመቱ ወጣት እያሱ ታዲያ ”ይህ እስርቤት የምድር ላይ ሲኦል ነው! የምከፍለው ገንዘብ ስለሌለኝ እዚህ መቀመጥ ግድ ሆኖብኛል!” ሲል ምሬቱን ለጋዜጠኞች ተናግሯል።
የኢህአዴግ መንግስት ወደ አገራቸው መመለስ የሚፈልጉትን ስደተኞች ለማገዝ አለመሞከሩና በየአገሩ ለሚንገላቱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አፋጣኝ እገዛ ከማድረግ ይልቅ ዝምታን መርጧል። ኢትዮጵያ በስደተኞች ቁጥር በአለም ቀዳሜ አገራት ተርታ ተሰልፋለች
No comments:
Post a Comment