ሚስጥራዊ መረጃው እንደሚያመለክተው ከሆነ በዛሬው እለት የተቋሙ ጀነራል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጎን በሚገኘው ቢሮአቸው የተቋሙን ከፍተኛ አመራሮችን ትዕዛዝ ለመስጠት መሰብሰባቸውንና በስብሰባውም ዳይሬክተሩ ተቋሙ ከጥቂት ወራቶች በፊት ብዛት ያላቸው አዳዲስ አባላትን መቅጠሩን እና ወደ ስራ ማሰማራቱን አስታውሰው ነገር ግን በውስጣቸው ሴራ ይዘዉ በተቋማችን ለበርካታ አመታት ተሰግስገው ሲሰሩ የነበሩ 6 አመራሮች እነዚህን አዳዲስ አባላትን በተለያየ ጊዜ በሥውር በመሰብሰብና አቅጣጫዎችን በመስጠት መንግስት የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርግ እና የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን እንዲጨመርላቸው ጥያቄ እንዲያነሱና ጫና እንዲያደርጉ አነሳስተዋል ያሉ ሲሆን አባላቱም እሔን ጥያቄና አቅጣጫ በመያዝ በየተመደቡበት መምሪያ እና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጋ በመሔድ አቅርበው ነበር::
ባሁን ሰአት መንግሥት ምንም አይነት የደሞዝም ይሁን ጥቅማጥቅሞች ለዉጥ እንደማያደርግ ምላሽ እንደተሰጣቸው እና ገና ከመግባታቸው እንደዚህ አይነት ጥያቄ ለማቅረብ መደራጀታቸው ወንጀል መሆኑን እና ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት ጥያቄ ቢጠይቁ ሊታሰሩ እንደሚችሉ ተገልፆላቸው ነበር ብለዋል ዳይሬክተሩ ። አቶ ጌታቸው አክለውም የነሱን ጥያቄ በነዚህ አዳዲስ ልጆች ለማንፀባረቅ መሞከራቸው እና 6ቱም አመራሮች የትግራይ ክልል ተወላጆች መሆናቸው ለኛ ከፍተኛ ውርደት ነው ማለታቸውን ሚስጥራዊው መረጃ ይገልፃል።
በመቀጠልም ዳይሬክተሩ እንደገለፁት ከሆነ እነዚህ 6 አመራሮች ለአባላቱ እንደዚህ አይነት ምላሽ እንደተሰጣቸው ሲያቁ 2ወር የፈጀ ስልጠና በሚስጥር እንደሰጡአቸው እና የስልጠናው ዋና አላማም መንግስት የደሞወዝ ጭማሪ የማያደርግ ከሆነ ከተቋሙ መውጣት እንዳለባቸው እና ከዛም በሁዋላ እንዴት መንግስትን ሊታገሉ እንደሚችሉና እነሱም ምን ምን አይነት ድጋፍ ሊያደርጉላቸው እንደሚችሉ የሚገልፅ ነበር ብለዋል ይህን ሥራ በስውር ከስራቸው ሆነው እንዲያስተባብሩም 10 አባላትን መርጠዋል ።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ከሆነ እነዚህ 6 የተቋሙ የክፍል አመራሮች በ ኤርፖርት ጥበቃ መምሪያ ፣ በ ውስጥ ክትትል መምሪያ እና በአዲስ አበባ ደህንነት ቢሮ የሚገኙ ናቸው ብለዋል ። በስተመጨረሻም ዳይሬክተሩ ለሰበሰቡዋቸው ጥቂት የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እነዚህን 16 አባላትና አመራሮችን በዚህ ሣምንት ውስጥ ከ ፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ሀይል ጋር በመሆን በቁጥጥር ሥር እንዲያስዉሉአቸዉና ለክስ መዝገብ የሚሆን ሌላ ምክንያት እንዲፈጥሩ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ሚስጥራዊ መረጃው እንደሚገልፀው ከሆነ በአሁን ሠአት ትዕዛዝ የተሠጣቸው ከፍተኛ የተቋሙ አመራሮች ሥራውን ጀምረዋል ።
No comments:
Post a Comment