መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እድለኞቹ በአስተዳደሩ አታላይ ፕሮፖጋንዳ ማዘናቸውን ገልጰዋል።አስተዳደሩ ምርጫ 2007 ተከትሎ ከ32ሺ በላይ ቤቶች ላይ እጣ በመጋቢት ወር 2007 ያወጣ ሲሆን ቤቶቹንም በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ከማስረከብ አልፎ ቀጣዩን እጣ በሰኔ ወር 2007 እንደሚያወጣ ቃል ቢገባም አንዱንም መፈጰም ሳይችል ቀርቶአል። አስተዳደሩ የካርታ ስራ እንዳዘገየው ቢናገርም እውነቱ ግን ቤቶቹ ባለመጠናቀቃቸው መሆኑን የአስተዳደሩ ምንጮች አጋልጠዋል።
አንድ እጣ የደረሳቸው ነዋሪ በሰጡት አስተያየት ከምርጫው በፊት በሳምንት ግዜ እናስረክባለን ሲባል ከርሞ ከምርጫው በሀላ ሁሉም ነገር ተረሳ። አንድ መንግስት እንደየመንደር ደርዪ ለቃሉ እንኩዋን መታመን አለመቻሉ ያሳዝናል ብለዋል።
በሰኔ ወር 2007 ይወጣል የተባለውና በርካታ የዲያስፖራ አባላት የቀፈው የ40 በ60 ቤቶች እጣ እና ከ36ሺ በላይ ኮንዶሞኒየም ቤቶች ቀጣይ እጣ መቼ እንደሚወጣ እስካሁን አለመታወቁም ብዙዎችን ያሳዘነ ሆኖአል።
በአሁኑ ወቅት በአዲስአበባ ብቻ ከ700ሺ በላይ ቤት ፈላጊዎች ተመዝግበው ከዛሬ ነገ እጣ ይወጣልኛል በሚል በተስፋ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ይታወቃል። በመንግስት ዘገምተኛ የ ቤት ግንባታ አካሄድ ግን ይህን ተመዝጋቢ ብቻ የቤት ባለቤት ለማድረግ በትንሹ የ30 አመታት ጊዜን እንደሚፈልግ ጉዳዩን ያጠኑ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ በመግለጵ አስተዳደሩ ሌላ መፍትሄ እንዲፈልግ ቢመክሩም ሰሚ አላገኙም።

No comments:
Post a Comment