Friday, July 4, 2014
ጨቋኙ የወያኔ ቡድን የተመሰረተው ብዙሀኑን የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ነው። (የአብስራ ዳኛቸው)
ዛሬ የወያኔ መንግስት በውድ ሀገራችን ኢትዬጵያ ላይ እያደረሰ ያለውን ታላቅ በደል እና ክህደት በታየኝ እና ግልፅ በሆነልኝ መልኩ ላቀርብላችሁ እወዳላው
የወያኔ መንግስት ኢትዬጵያን ከተቆጣጠረ ድፍን 23 አመት አድርጎዋል። ግን ያሉ እውነታዎች እንደሚያሳዩት በነዚህ 2 አስርት አመታት ትግል ሀ ብሎ ከጀመረበት ከትግራይ ክልል እና ህዝብ ሌላ ሌላውን ሙሉ በሙሉ በመርሳት እና ለሚያቀርቡት ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ብዙሀኑን የትግራይን ክልል እና ህዝብ ብቻ በአስፈላጊው መንገድ በኢኮኖሚ በማህበራዊ በፖለቲካ በባህል ዘርፎች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለማገልገል ቆርጦ መነሳቱን ያሳየበት አጋጣሚ እንደሆነ ታይቷል።
በሌላው የኢትዮጵያ ክልል እና ህዝብ ላይ ግን በእጅ አዙር ቀኝ ግዛት እየገዛት ይገኛል። ባህልን ታሪክን አብሮ መኖርን ፍቅርን መተማመንን መተጋገዝን በጣም ግልፅ እና በሚታይ መልኵ ለማጥፍት ደፍ ቀና እያለ እነዚ ሁሉ አመታትን አሳልፏል።ታላቋን ትግራይ ለመገንባት ያላደረጉት ጥረት የልፈነቀሉት ድንጋይ ያልቆረጡት ዛፍ የለም። በአሁኑ ሰአቱ ከሌላው የኢትዬጵያ ክልል በጣም ሰፊ በሆነ የእድገት ልዩነት የትግራይ ክልል እየለማች ትገኛለች። ለዚሁም ምስክር የሚሆነው በአሁኑ ሰአት በትግራይ ክልል ውስጥ ተቋቁመው የሚገኙ የተለያዩ መጠነ ሰፊ እና ትላልቅ ፍብሪካዎች እና ተቋማት ምስክሮች ናቸው።
በተለያየ ዘርፍ ለምሳሌ በመሰረተ ልማት በህክምና በትምህርት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ያለው ልዩነት ከሌላው ክልል ጋር በማወዳደር ለማወቅ በጣም ቀላል ነው። በተመሳሳይ መልኩ ብዙሀኑ የትግራይ ህዝብ ከዚህ ነገር የጥቅም ተቋዳሽ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ የሎላው ክልል እና ህዝብ በጣም በከፍ የኑሮ አዝቅጥ ውስጥ ገብቶ መኖር ከጀመረ እነዚህ ሁላ አመታት ተቆጥረዋል።
ጨቋኙ የወያኔ ቡድን ካፒታሉ ከፍተኛ በሆነ ወጪ ከ66 በላይ የንግድ ተቋማት መስርቶ በትልቅ የሀገር ምዝበራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል። ለዚህም ተቋም effort የሚባል የንግድ ስም ሰቶታል። effort ያልተሰማራበት የንግድ መስክ በሀገሪቷ ላይ ተፈልጎ ሊገኝ አይችልም። ይህ ድርጅት በመላው የኢትዮጽያ ክልሎች ላይ ተንሰራፍቶ የየክልሎችን አንጡሬ ሀብት እንደ መዥገር ተጣብቆ እየመጠጣት ይገኛል። ከዚህ ድርጅት የሚገኘው ትርፍ በተዋረድ ከወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንሥቶ እሥከ ዝቅተኛ የስራ እርከን ላሉት የወያኔ ግልገሎች ኪስ ማዳለቢያ ሆኗል ለዚህም ተጨባጭ ማስረጃ ካስፈለገን sunday time በ2011 ባወጣው ሪፖርት ላይ በኢትዮጵያ ካሉ ከፍተኛ 20 ባለሀብቶች መካከል ከ90% በላይ ያሉ የዚሁ ጨቋኝ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል ከወያኔ እኩይ ተግባር መካከል በጣም የሚያሳፍረው እና የሚያሳዝነው ሳይማሩ በከፍተኛ የትምህርት ደረጃ እንደተማሩ እና እንደተመረቁ ተደርጎ ከኬንያ እና ከህንድ ባስመጡት የተሳሳተ የትምህርት መረጃ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙት የስራ እና የስልጣን ቦታዎች ላይ የወያኔ ጥቅም ለማስጠበቅ ታስቦ በኃላፊነት እንዲቀመጡ ተደጓል። ለዚህም ማስረጃ ካስፈለገን ኢሳት may 9,2014 ባወጣው መረጃ ከ61ጀነራሎች 59ኙ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ እነሱም ከአራተኛ ክፍል የዘለለ እውቀት የላቸውም።
በአሁኑ ሰአት በዋናነት በአ/አ አድርጎ እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች በአማራ በኦሮሞ በጋምቤላ በአፋር ወ.ዘ.ተ...... ወያኔ በቦታቸው ላይ ለብዙ አመታት የኖሩትን ዜጎች በመማፈናቀል እና ያለምንም ካሳ አውጥቶ መሬት ላይ በመጣል በምትኩ የትግራይ ተወላጆችን እና ሌሎች ባንዳዎችን ቦታው ላይ በማስፈር ህጋዊ ካርታ እንዲኖራቸው በማድረግ ብዙሀኑን እያሰቃየ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም ደግሞ በግብርና ከሚተዳደረው አርሦ አደር ላይ መሬት በመንጠቅ ለተለያዪ የልማት ስራ ይፈለጋል በማለት የሀሰት ምክንያት በማቅረብ ደሀ አርሦ አደሩን ከቦታው በማፈናቀል የራሱን ጥቅም ለመጋበዝ ለተለያየ ተግባራት ያውለዋል። ከዚህ በተቃራኒ የተፈናቀለው አርሦ አደር ለኑሮ ምቹ ባልሆነ ዱር ውስጥ በመጣል የጅብ እና የአውሬ እራት እንዲሆኑ ማድረጋቸው የሚረሳ አይደለም።
ወያኔ ስልጣን ከተቆጣጠረ ጀምሮ ብዙ ዜጎችን ከትውልድ ቀያቸው በተለያየ ግዜ ማፈናቀሉ ይታወቃል ከብዙ በጥቂቱ እንኳን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ይኖሩ የነበሩ ሀብት ንብረት ያፈሩ ዜጎችን ከትውልድ ቀያቸው አፈናቅሎ ክስ ቢመሰርቱበትም እንኳን ቤት ንብረት አለማፍራታቸውን ጠቅሶ ምንም ለክስ የሚያበቃ ነገር ሳይኖራቸው ጉዳያቸው ለፖለቲካ ፍጆታ እየዋለ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል።
ደሀው ህዝብ ከቤቱ ተፈናቅሎ በአመታት ያፈራውን ጥቂት ጥሬት በመነጠቅ አውላላ ሜዳ ላይ ሲወድቅ የወያኔ ጀሌዎች ግን ለመዝናናት በተለያዩ ያለማችን ክፍሎች ሲዟዟሩ እና ሲገበያዩ እንዲሁም መጠኑ በዛ ያለ ብር በአለም በታወቁ ባንኮች ውስጥ ተቀማጭ ሲያደርጉ እና ልጆቻቸው ደግሞ በብዙ የውጪ ምንዛሬ በአለም ባሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እያስተማሩ ይገኛሉ
ለዚህም መፍትሄው ይህንን ሁላ ግፍ ያደረሰብንን ጨቋኝ ቡድን ዘር ጎሳ ሀይማኖት ሳንል አንድ ሆነን ከስር መሰረቱ በመንቀል ከዝች ቅድስት ሀገር ነቅለን ማስወጣት ይኖርብናል።
ያኔ!
ትግራይ የበራው መብራት ሁሉም ጋር ይበራል
ትግራይ የማይጠፍው ውሀ ሁሉም ጋር ይኖራል
ታላቋ ትyግራይ መባልዋ ቀርቶ ታላቋ ኢትዮጵያ ይባላል
የወያኔን ኪስ ያዳለበው የኢትዮጵያ አንጡራ ሀብት የሁላችንም ይሆል
ይህ ሁላ ሲሳካ ሁላችንም ሀገራችን ላይ በፍቅር በሰላም መኖር እንጀምራለን።
ድል ለኢትዬጵያ ህዝብ
የአብስራ ዳኛቸው።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment