Wednesday, July 16, 2014

ኣቶ ዳኘው ይገዙ የሞት ፍርደኛው የዓረና ኣባል…!

ዓረና-መድረኽ “ዘመቻ ኣብራሃ ደስታ” ብሎ ህዝባዊ ስብሰባ በመኾኒ ከተማ በተሳካ ሁኔታ ሲያካሂድ የእንዳሞኮኒ ወረዳ ኣስተዳዳሪ የሆነው ኣቶ ሃፍቱ ወላሞ በወረዳ የምትገኝ ታሕታይ ሓያ የምትባል ቀበሌ(ጣብያ) በመሄድ “የዚህ ቀበሌ ዓረና ኣባላት ሞተር ዳኘው ይገዙ ነው ስለዚ በኣከባቢው የዓረና እንቅስቃሴ ለመግታት ዋና መፍተሄ እሱን መግደል ነው።” በማለት ለኣከባቢው ታጣቂዎች ዳኘው ከገድልነው ሌሎቹ ኣባላት ቦታቸው ይይዛሉ በማለት እንዲገድሉት ትእዛዝ ኣስተላልፏል።

ኣቶ ዳኘው ይገዙ የ 65 ዓመት ኣዛውንት ሲሆኑ በጀግነታቸው የወረዳዋ ህዝብ የሚያውቃቸውና ታላቅ ተሰሚነት ያላቸው ናቸው።

ኣቶ ዳኘው የሞት ፍርድ የሰጣቸው ፍርድ ቤት ኣይደለም የወረዳዋ ኣስተዳዳሪ የሆነው ኣቶ ሃፍቱ ወላሞ እንጂ…! ይህ የተናገረው ህዝብ ሰብስቦ በሓምሌ 6 /2006 ዓ/ም ነው።

የዓረና ኣባላት የዓላማቸው ፅናት ሁሉም ዓየነት መስዋእትነት እስከመክፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ኣድርጓቸዋል።

ኣቶ ዳኘው ፍርዳቸው ለመቀበል ዝግጁ ሁነዋል።

የህወሓት መንግስት ግን ወደ ጥፋት መንገድ እየተራመደ ነውና ቆም ብሎ እንዲያስብበት እናሳስባለን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው…!


No comments:

Post a Comment