የፓርላማ አባልና የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የኢሕአዴግ መንግስት በሰላም የሚታገሉ ወጣት ፖለቲከኞችን የማሰሩን ጉዳይ እብድነት ብለዉታል።
«እነዚህ ሰዎች አብደው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሀብታሙ አያሌውን ፖሊሶች ይዘውት እንደሄዱ ሰማው፡፡ ስልኩ ይጠራል ግን አይመልስም፡፡ የእነርሱን ሃሳብ የሚቃወም ሁሉ አሸባሪ እየመሰላቸው በሽብር እራሳቸውን እያናወዛቸው ያለ ይመሰለኛል፡፡ ሀብታሙን ሊያስሩት ይችላሉ በህዝብ ውስጥ ያለውን የነፃነት መንፈስ ግን ማስረ አይቻላቸውም፡፡ እልፍ አህላፍ የነፃነት ሰዎች ይፈጠራሉ፡፡ ለነገሩ የሚታሰሩ ንፁሃን ታሳሪዎች ሳይሆን አሳሪዎ በከፍተኛ የህሊና ስቃይ ውስጥ መሆናቸውን መረዳት አሰቸጋሪ አይደለም፡፡» ሲሉ ነበር አቶ ግርማ በፌስ ቡክ አስተያየታቸውን የሰጡት።«የዚህ ልጅ ነገር ሳያበሳጫቸው አይቀርም፡፡ ሰለማዊ ሰልፍ ላይ በባትሪ አንደሚሰራ ሳያርፍ ያጋልጣቸዋል፡፡ በየሳምንቱ ገበናቸውን በመፅኄት በጋዜጣ ያወጣል፡፡ በዓመት መጨረሻ ደግሞ ትምህርት ተምሮ በክብር በማዕረግ ይመረቃል፡፡ ኢዚህም እዚያም ያገኙታል ሁሉም ጋ ሲያወግዛቸው፤ በቃችሁ ሲላቸው ይሰማሉ፡፡ በቃቸው የሚላቸው ደግሞ እንደበቃቸው ስራቸው ሆኖ ያያቸው እርሱ መሆኑ ያበሳጫቸዋል፡፡ ሌላው በግምት አትችሉም ሲላቸው ሀብታሙ ግን አውቃችሀኋለሁ አትችሉም ይላቸዋል፡፡ በእውነት ነርቫቸውን ነው የነካው፡፡ የሚያጓጓው ግን ምን ብለው 28 ቀን የምርመራ ጊዜ ለመጠየቅ አሸባሪ እንደሚሉት ነው፡፡ ዛሬ ቄሱን አሸባሪ አሉ የሚለው ዜና አብርሃ ደሰታ ከመቀሌ ሹክ ብሎናል፡፡ ሀብታሙን ቢሉት አይገርምም፡፡ እንሰማለን፡፡ ተረኞች መዘጋጀት ነው፡፡» ብለው የጻፉት አቶ ግርማ የኢሕአዴግን የፖለቲክ ክስረትና የአቶ ሃብታሙን ታታሪነት የገለጹ ሲሆን፣ እርሳቸዉን ጨምሮ ሌሎች በሰላም የሚታገሉ ሁሉ፣ የሰላማዊ ትግል ለሚያስከፍለው እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀርበዋል።የሰላማዊ ትግል አልጋ በአልጋ እንደሆነ ለሚመስላቸውና በቀላሉ ተስፋ ለሚቆርጡ ወገኖች አቶ ግርማ ሰይፉን ጠንካራ ምክር ለግሰዋል። « ሰላማዊ ታጋዮች መንገላታት እና እስር አሰበውበት የገቡበት ነው፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ያማል ግን ይህን እመም ለመቻል ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡ የሀብታሙ አያሌው ባለቤት ባለፈው ሳምንት አባቷን በድንገት በሞት ተነጥቃለች አሁን ደግሞ ባለቤቷ በግፍ ወህኒ ወርዶዋል ኮልታፋ ህፃን ልጅ ይዛ መከራዋን እንደምትገፋ ሀብታሙ ያውቀዋል፡፡ ሊያሞላቅቃቸው ቢፈልግ ግን ከኢህአዴ ደጅ ፍርፋሪ መልቀም የሚከለክለው አልነበረም፡፡ » ሲሉ ነበር በሰላምዊ ትግል ከአምባገነኖች ጋር ትንቅንቅ የየዙ ወገኖችን ጀግንነት ያስረዱት።አቶ ግርማ ሲያጠቃልሉ « ውድ የትግል ጓዶች ከዞን ዘጠኝ ወደ ሌላ ዞን መሸጋገራችሁ ቢያሳዝነንም ፅናታችሁ ያበረታናል፡፡ ፅኑ፡፡ ለካ እነርሱ ይህን የማንበብ መብት የላቸው፡፡ በዞን ዘጠኝ የምትገኙ ሁሉ በርቱ ፅናቱን ይስጣችሁ ማለት የግድ ይላል» በማለት ትግሉን ከማፋፋም ዉጭ ሌላ አማራጭ እንደሌልም ለማሳየት ሞክረዋል።
No comments:
Post a Comment