Sunday, July 13, 2014
የአቶ አዳርጋቸዉ መያዝና እንድምታዉ
የአቶ አንዳርጋቸዉ መያዝ በተሰማ-በ16ኛዉ ቀን ባለፈዉ ማክስኞ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቆጣጠረዉ ቴሊቪዥን ጣቢያ ባሠራጨዉ መግለጫ ግን «የአሸባሪ ድርጅት አመራርና በጥብቅ የሚፈለጉ » ያላቸዉ አቶ አንዳርጋቸዉ እና ሌሎች ሰዎች መታሰራቸዉን አረጋግጧል::ጤና ይስጥልኝ እንደምን አመሻችዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚሕ ቀደም ባሸባሪነት ወንጅሎ በሌሉበት ሞት ያስፈረደባቸዉ፤ የግቦት ሰባት የፍትሕ፤ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ሰነዓ-የመን ተይዘዉ ወደ ኢትዮጵያ መጋዛቸዉ ብዙ እያነጋገረ ነዉ።አቶ አንዳርጋቸዉ የብሪታንያ ዜጋ ናቸዉ።ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያንና የየመን መንግሥታትን እርምጃ አዉግዟል።የብሪታንያ መንግሥት በበኩሉ የየመን መንግሥት አቶ አዳርጋቸዉን ለኢትዮጵያ አሳልፎ መስጠቱን የጄኔቫ-ሥምምነትን የጣሰ ብሎታል።በአቶ አንዳርጋቸዉ ላይ ግርፋት ወይም ሌላ በደል እንዳይፈፀምባቸዉ፤ ከኤምባሲና ከሕግ ባለሙያዎች ጋር የመነጋገር መብታቸዉ እንዲጠበቅ ጠይቋል።በተለይ በሌሉበት የተወሰነባቸዉ የሞት ቅጣት እንዳይፀና አሳስቧል።አምንስቲ ኢንተርናሽናል፤ ሑዩማን ራይትስ ዋች እና ሌሎች የተለያዩ የመብት ተሟጋች ድርጅቶችም አቶ አንዳርጋቸዉ መጋዛቸዉን ተቃዉመዉ፤ «ሰብአዊ ምብት ይጥሳል» የሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸዉን ያሰቃያል ብለዉ እንደሚሰጉ እያስታወቁ ነዉ።Die Gesellschaft für bedrohte Völker(ለተበደለ ሕዝብ ተሟጋች ማሕበር እንደማለት ነዉ) የተሰኝዉ የጀርመን የመብት ተሟጋች ድርጅት ደግሞ አቶ አንዳርጋቸዉን ለማስፈታት የአዉሮጳ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቋል።አዉሮጳ እና ሰሜን አሜሪካ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ በየከተማዉ ባደረገዉ የተቃዉሞ ሠልፍ የአቶ አንዳርጋቸዉን መያዝና መጋዝ አዉግዟል።የኢትዮጵያ መንግሥትን ባለሥልጣናትን ሥለ ጉዳዩ ለማነጋገር፤ ቢቻል በዚሕ ዉይይት እንዲሳተፉ ለመጋበዝ ለተከታታይ ቀናት ሞክረን ነበር-ያገኘናቸዉ እስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም።ሌሎቹ ን ልናገኛቸዉ አልቻልንም።የአቶ አንዳርጋቸዉ መያዝ በተሰማ-በ16ኛዉ ቀን ባለፈዉ ማክስኞ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቆጣጠረዉ ቴሊቪዥን ጣቢያ ባሠራጨዉ መግለጫ ግን «የአሸባሪ ድርጅት አመራርና በጥብቅ የሚፈለጉ » ያላቸዉ አቶ አንዳርጋቸዉ እና ሌሎች ሰዎች መታሰራቸዉን አረጋግጧል።በአምደ መረብ የሚፃፈዉ ዉግዘት፤ ክርክርም፤ እንደቀጠለ ነዉ።የእርምጃዉ ሕጋዊ፤ ሠብኣዊና ፖለቲካዊ እድምታ የዛሬ ዉይይታችን ትኩረት ነዉ።ነጋሽ መሐመድአርያም ተክሌ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment