Sunday, July 6, 2014

በእኛ እምነት አንዳርጋቸው ቀድሞ የቤት ስራውን ጨርሶል (ወጣት ዘመነ ካሴ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሀይል ቃል አቀባይ)

ወጣት ዘመነ ካሴ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሀይል ቃል አቀባይ የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ  ስለሆኑት ስለ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታገትና ለወያኔዎች ተላልፎ መሰጠት ዙሪያ በኢሳት ሬዲዮ የተናገረው

በእኛ እምነት አንዳርጋቸው ቀድሞ የቤት ስራውን ጨርሶል እያለቀሰ ተናግሮ ፣ እያለቀሰ ሰብኮ፣ እያለቀሰ ያለፈውን ታሪክ እያነሳ ከወደፊት አቅጣጫችን ጋር እያቀናጀ በመንገር ንጹህ ኢትዮጵያዊነትን መብት እንዲፈጠር በተለይ በእኛ በአዲሱ በወጣት ትውልድ  ንጹህ የሆነ ራዕይ እንዲኖረን በማድረግ በኩል  መስራት የሚገባውን ስራ ቀድሞ አጠናቋል ::

ምን አልባት አንዳርጋቸውን የያዙትም አካላት ወይም አስያዦቹ  አልገባቸውም እንጂ የመኝታ ቤታቸው ድረስ የሚያንኮኮና የሚንሳፈፈ የትግል መንፈስ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳርጋቸው ፈጠሮል::የቤተ መንግስት አትክልቶች ጋር አትክልቶች ጋር እኩይ እየተንከባከቡ የሚያሳድጉት እሾህ የሆነ የትግል መንፈስ፣ጸረ ወያኔ የሆነ የትግል መንፈስ አንዳርጋቸው ፈጥሯል:: ከተማ ውስጥ የአንዳርጋቸው መንፈስ አለ,፣ ገጠር ውስጥ የአንዳርጋቸው መንፈስ አy ለ ፣ደቡብ ውስጥ የአንዳርጋቸው መንፈስ አለ፣አፋር ውስጥ የአንዳርጋቸው መንፈስ አለ፣አዲስ አበባ ውስጥ የአንዳርጋቸው መንፈስ አለ፣ አማራ ውስጥ፣ ጉራጌ ውስጥ፣ ጋምቤላ ውስጥ፣ኦሮሚያ፣ትግራይ  አፋር፣ሱማሌ ውስጥ፣ ባጠቃላይ መለው ኢትዮጵያዊ  ውስጥ የአንዳርጋቸው መንፈስ አለ::ያን መንፈስ ከቶ ማሰር አይቻልም::አንዳርጋቸውን በካቴና አስሮ ከሰነአ አዲስ አበባ መውሰድ ይቻላል አድርጋቸውን የፈጠረው ትጉህ ፣ ታታሪና ቀና የሆነውን ወጣት የኢትዮጵያዊ መንፈስ ማሰር ግን ፈጽሞ በጭራሽ አይቻልም:: አንዳርጋችው በየሂዱበት የሚወጋቸው፣ በተኙበት የሚቆረቁራቸውና የሚጎረብጣቸው መንፈሰ ጸረ ወያኔ የሆነ መንፈስ በመላው በኢትዮጵያ ወጣት ላይ ዘርቷል፣
አስቀምጦል::

አንዳርጋቸው ኢትዮጵያዊነትን ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ በዚህ ኢትዮጵያዊነት መነጽር ፀረ ኢትዮጵያዊነት የሆነ አቋም ሁሉ እስከመጨረሻው እንታገላለን የየመን መንግስትም ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ ነው አንዳርጋቸውን አስተላልፎ መስጠት ማለት አንድ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የተፈጠረ ንጹህ ራዕይ ያለው ኢትዮጵያዊ አሳልፎ መስጠት ብቻ አይደለም አንዳርጋቸው የፈጠራቸው መንፈሶች የሚፈጥሯቸውን ቀጣይ ትውልዶች መንፈስ ጭምር የሚጎዳ እና ነገሩን ጥሩ ባልሆነ ሁኔታ ምንአልባት በቀጣይ የወደፊት የኢትዮጵያንና የየመንን ትውልዶች ግንኙነት በሚያበላሽ ሁኔታ የምናየው መሆኑን ሊያውቁት ይገባል

No comments:

Post a Comment