መጋቢት ፳፮( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 13 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያ-ታንዛኒያ ድንበር መታሰራቸውን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል። እንደ ፖሊስ መግለጫ ኢትዮጵያውያኑ የታሰሩት በኩዋሌ ካንትሪ በምትገኘው በሉንጋ- ሉንጋ ውስጥ እሁድ ማታ ነው።
የሳብዌኒ ፖሊስ ኃላፊ ጆሴፍ ኦሚጃህ ህገወጥ የውጪ ሀገር ስደተኞቹን በህንድ ውቅያኖስ አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያስወጡ አሻጋሪዎች እየተጠየቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ባለፈው መጋቢት ወር በናይሮቢ -ምዕራብ ካሀዋ በሚገኝ ቤት ውስጥ ራሳቸውን ደብቀው የተገኙ 23 ኢትዮጵያውያን መታሰራቸው ይታወሳል።
በአንድ ሞቶ በተገኘ ሞተር ባይስክለኛ የተቆጡ ኬንያውያን 23ቱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ በጅምላ የኃይል እርምጃ ሊወስዱባቸው ሲሉ ፖሊስ እንደታደጋቸው የኪያምቡ ካንትሪ ዲስትሪክት ፖሊስ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሮቢንሰን ሊያምቢላ ገልጸዋል።
የፖሊስ ኃላፊው አክለውም ስደተኞቹ በራሳቸው መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ የተነሱ ናቸው ተብሎ ይታመናል፤ ሆኖም እንግሊዝኛ ስለማይናገሩ ፍላጎታቸው ይህ ነበር ብሎ በቶሎ ማወቅ እንደማይቻል አስረድተዋል።
No comments:
Post a Comment