ሚያዚያ ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው የካቲት ወር በዱባይ የተደረገውን የምግብ ኤግዚቢሽን ለመካፈል ያቀኑ 6 የኢትዮጵያ ነጋዴዎች፣ የተበላሸ ስጋ አቅርበዋል በሚል ለሁለት ወራት ያክል ከአገር እንዳይወጡ ታግተውና ሁለቱ ነጋዴዎች ደግሞ በተደጋጋሚ ሲታሰሩ መቆየታቸውን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው ጭንቅት ውስጥ መግባታቸውን በተደጋጋሚ ከገለጹ በሁዋላ፣በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስና በኢህአዴግ መንግስት መካከል በተደረገ ስምምነት፣ ክሳቸው መነሳቱ ወደ አገራቸው መሄድ እንደሚችሉ እንደተፈቀደላቸው ታውቋል።
ነጋዴዎቹ ከዚህ ቀደም በአለማቀፍ የንግድ ስርአት ውስጥ ባልተለመደ መልኩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው፣ የመነጋጋሪያ አጀንዳ ሆኖ ከርሟል።
No comments:
Post a Comment