ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) መንግስት በኢንተርኔት አማካኝነት የሚደረጉ የድምፅና የምስል አገልግሎቶች ላይ አዲስ መመሪያን እንደሚተገብር ማስታወቁን ተከትሎ አገልግሎቱ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተቋረጠ።
በተለይ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተቃውሞ በተቀሰቀሰበት የኦሮሚያ ክልል የትዊተርና የWhatsAPP አገልግሎቶች ከተቋረጡ አንድ ወር አካባቢ እንደሆናቸው ብሉምበርግ የዜና ወኪል የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል።
በኦሮሚያ ክልል በተጨማሪ አገልግሎቶቹ በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማና በተለያዩ አካባቢዎች ተቋርጦ እንደሚገኝም የተለያዩ አካላት ለዜና ወኪሉ ያስታወቁ ሲሆን፣ በምስራቅ ለንደን ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት አቶ ስዩም ሃሜሶ ሃገር ቤት ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንኳን መገናኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ አገልግሎቱ ሊስተጓጎል የቻለው በቴክኒክ ችግር ሊሆን እንደሚችል ገልፀው፣ መንግስት የማገድ ፖሊሲ እንደሌለው ለዜና አውታሩ አስተባብለዋል።
ይሁንና የስልክ አገልግሎት ተጠቃውሚዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መንግስት ተግባራዊ ሊያደርግ ያሰበው አዳዲስ መመሪያዎች በኢንተርኔት እና በስልክ የመልዕክት ልውውጦች ላይ ቁጥጥርን እንዲሁም የስነ-ልቦና ተፅዕኖን ለመፍጠር እንደሆነ አስታውቀዋል።
በአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ ስዩም ተሾመ በተቀንሳቃሽ የእጅ ስልክ የሚደረጉ የተለያዩ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተቋርጠው እንደሚገኙ ለብሉምበርግ የዜና አውታር አስረድቷል።
በቅርቡ የWhatsAPP ኩባንያን የገዛው ፌስቡክና ትዊተር ድርጅቶች በኢትዮጵያ እገዳ ተጥሎበት ስላለው አገልግሎት ተጠይቀው ምላሽ ከመስጠት መቆጠባቸው በዘገባው ያወሳው የዜና ወኪሉ እገዳው በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ እንደሚገኝም አስነብቧል።
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ የመብት አያያዝና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ዙሪያ የሰላ ትችትን የሚያቀርበው ሂውማን ራይትስ ዎች በበኩሉ ድርጊቱ ቀድሞ የተተነበየ እንደሆነና መንግስት የመረጃ ልውውጦች ላይ ቁጥጥሩን እንዳጠናከረ ገልጿል።
መቀመጫውን በሰርቢያ ያደረገውን በቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚሰራው ኩባንያ በየጊዜው የሚያወጣቸው መረጃዎች በቢቢሲ እና በሌሎች አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘንድ በመረጃነት እንደሚቀርቡም ለመረዳት ተችሏል።
ቤርሙዳ ኢዝቤኪስታን እና ሚያንማር ከኢትዮጵያ በመቀጠል ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ከሚያደርገው ቁጥጥር በተጨማሪ የሚጠይቀው ክፍያም ውድ መሆኑን የተለያዩ አካላት ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወሳል።
መንግስት በገጠመው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ፣ በውጭ ሃገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በህዳሴ ግድብ እንዲሁም በመኖሪያ ቤት ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ አዲስ ዘመቻ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment