Friday, April 29, 2016

የስራ ማቆም አድማና የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የጠየቁ የደሴ መምህራን እየተዋከቡ ነው ።


ሚያዚያ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሚያዚያ 14፣ 2008 ዓም የደሴ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር አጠቃላይ 3ኛ ጉባኤ ተደርጓል። በስብሰባው ላይ የ33 ትምህርት ቤቶች የመሰረታዊ መምህራን ማህበር አመራሮች፣ የደሴ ከተማ ብአዴን ተወካይ፣ የትምህርት መምሪያ ሃላፊና የደህንነት ሰዎች ተገኝተዋል። የስብሰባው አጀንዳ የመምህራን ማህበር አመራሮችን ምርጫ ለማካሄድ ቢሆንም፣ ስብሰባው እንደተጀመረ መምህራን አሁን ስብሰባ ለማካሄድ አንችልም የሚል ተቃውሞ አሰምተዋል።
የመምህራን መሰረታዊ ማህበራት አመራሮች ፣ “እኛ ከዚህ በሁዋላ ምርጫ አንፈልግም፣ ኢህአዴግ 25 አመታትን ገዝቷል፣ በቃው፣ ለውጥ አላየንም፣ ልማትና እድገት የለም፣ እኛ በረሃብ እየተሰቃየን ነው ፣ ማህበራችንን ማዋቀር አንፈልግም፣ ከፖለቲካ ነጻ አይደለም” ያሉ ሲሆን፣በተለይ መምህራን የትምህርት ጥራት እናስጠብቃለን እያልን ባለንበት ወቅት ትምህራታቸውን ያላጠናቀቁ መምህራን እየተመደቡ ዜጎቻችንን እያበላሹ በመሆኑ፣ ይህንንም እየተቃወምን ስለሆነ ህገመንግስታዊ መብታችንን ለማስጠበቅ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደምናደርግ እናሳውቃለን ብለዋል።
መምህራኑ ተቃውሞአቸውን ካቀረቡ በሁዋላ፣ በታዛቢነት የተገኙት የብአዴን ተወካይ፣ የትምህርት መምሪያ፣ የትምህርት መምሪያ ምክትል ሃላፊና ካድሬዎች የመምህሩን መብት በማፈንና በማስፈራራት ስብሰባውን እነሱ በሚፈልጉት መልኩ ለማስኬድ ጥረዋል። ባለስልጣናቱ ከፉከራ የዘለለ የምታመጡት የለም እንዳሉዋቸው የሚናገሩት መምህራን፣ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ የስራ ማቆም አድማ ማድረግ እንደማይችሉ ተናግረዋል። ከስብሰባው በሁዋላ አንድ የሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤት የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርግ በመግለጽ ጽሁፍ ማቅረቡንም መምህራን ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም በደሴ የጸጥታ ሃይሎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተመድበው ቅኝት በማድረግ ላይ ናቸው ፡፡ መምህራን ከኑኖረና ከአስተዳደር በደል ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ሲሆኑ፣ መንግስት የጥያቄው መግፋት እያሳሰበው መምጣቱን ተከትሎ በቅርቡ ለመምህራን የቤትና የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚያመቻች ገልጿል።

መንግስት ከጋምቤላ የተጠለፉ ዜጎችን ለማስለቀቅ ድርድር መጀመሩን አስታወቀ


ሚያዚያ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ200 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን እና ከ108 በላይ ህጻናትና ሴቶች በደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት የተጠለፉበትን አስደንጋጭ ዜና ተከትሎ መንግስት በሰጠው መግለጫ፣ የተጠለፉ ሰዎችን ለማስመለስ መከላከያ ሰራዊቱ ወደ ሱዳን ድንበር ዘልቆ መግባቱንና ከበባ ማካሄዱን በተለያዩ አለማቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሲገልጽ ቢቆይም፣ ሰዎቹ ከተጠለፉ ከሁለት ሳምንት በሁዋላ፣ ከጠላፊዎቹ ጋር ድርድር በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል። የኢህአዴግ መንግስት ከደቡብ ሱዳን መንግስት፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከነዋሪዎች ጋር እየተደራደረ መሆኑን ለኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ ሳያስታውቅ፣ ለውጭ አገር መንግስታት ገለጻ መስጠቱ፣ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ወይስ ለውጭ መንግስታት ነው የሚል ጥያቄ አስነስቶበታል። ከሚያዚያ 7 በሁዋላ ባሉት ሁለት ቀናት ከተሰጠው መግለጫ ውጭ፣ ሰዎቹን የማስለቀቅ ጥረቱ ስለተደረሰበት ሁኔታ ለኢትዮጵያ ህዝብ መረጃ ያልተሰጠ ሲሆን፣ አዳዲስ መረጃ የሚጠይቁ የውጭ አገርና የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች መለስ የሚሰጣቸው የመንግስት ባለስልጣናት ማጣታቸውን ተከትሎ እለታዊ መረጃዎችን ለህዝብ ለማቅረብ ሳይችሉ ቀርተዋል።
የኢህአዴግ መንግስት ሰዎቹን ወታደራዊ ሃይል በመጠቀም ለማስለቀቅ የነበረውን እቅድ ለምን እንደሰረዘ የገለጸው ነገር የለም። ምንም እንኳ ሰዎቹ በድርድር መለቀቃቸው የተሻለው አማራጭ መሆኑ ቢታወቅም፣ ድርድሩ ረጅም ጊዜ መውሰዱ በታጋቾችና በቤተሰቦቻቸው ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ፣ መንግስት የራሱን ምስል ለመገንባት “ለአለማቀፉ ማህበረሰብ ስራዬን አድንቁልኝ” የሚል ስብሰባ ማዘጋጃቱ፣ በሰዎች ስቃይ፣ የራስን ገጽታ ለመገንባት የሚደረግ ጥረት ይመስላል” ሲል ዘጋቢያችን አስተያየቱን አሰፍሯል።

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የፍርድ ቤት ዋስትና መብታቸው ተገፎ ድጋሚ አዲስ ክስ ተመሰረተባቸው


ሚያዚያ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአክሰስ ሪልስቴት መስራችና ባለቤት የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በፍርድ ቤት በዋስ እንዲወጡ ቢፈረድላቸውም ፓሊስ ተጨማሪ ክስ በማቅረብ የዋስትና መብታቸው ተገፎ ሌላ ክስ መስርቶባቸዋል።
ባለሃብቱ ባለፈው ሳምንት ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቢበይንም ፣ፓሊስ ግለሰቡን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። አቶ ኤርሚያስ አመልጋን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸውና ጠበቃቸው ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱን ከሕግ አግባብ ውጪ ድጋሚ መከሰሳቸውን ተከትሎ እገዳ ተጥሎባቸዋል። ይህም ከፍተኛ ስነ ልቦናዊ ጫና እንደፈጠረባቸው የአቶ ኤርሚያስ ቤተሰቦች በተለይ ለፎርቹን ጋዜጣ ገልፀዋል።

Thursday, April 28, 2016

በትንሳኤ በአል ዋዜማ የሚታየው የዋጋ ንረት ሸማቾችን አስደንግጧል

ሚያዚያ ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ክርስቲያኖች ዘንድ ከሚከበረውን የፋሲካ በአል ጋር ተያይዞ የቅቤ እና የዶሮ ዋጋ የተጋነነ ጭማሪ ሲያሳዩ፣ በብዙ የክልል ከተሞች ደግሞ ዘይት እስከናካቴው ጠፍቷል። በአማራ ክልለ በሚገኙ ከተሞች ደግሞ፣ ከዘይት በላይ ውሃ ማግኘትም እየቸገረ ነው።

እነ አቶ መላኩ ፈንታ ተከላከሉ ተባሉ ሚያዚያ ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል የፀረ ሙስና

ኮሚሽን በቀድሞ የጉምሩክ ኃላፊ በነበሩት አንደኛ ተከሳሽ አቶ መላኩ ፈንታውና ግብረ አበሮቻቸው ላይ ከተከሰሱባቸው አስራ ሰባት ክሶች በተወሰኑት የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፎባቸዋል።

1ኛ ተከሳሽ አቶ መላኩ ፈንታ የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር፣ 2ኛው ተከሳሽ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ የባለስልጣኑ የህግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ 3ኛው ተከሳሽ አቶ በላቸው በየነ የኦዲት ዳይሬክተር፣ እንዲሁም አቶ ማሞ አብዲ የታክስ አማካሪ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አባል እና ጸሃፊ ሆነው ስርተዋል።

ዱባይ 6ቱን የኢትዮጵያ ነጋዴዎች ክስ አነሳች

ሚያዚያ ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው የካቲት ወር በዱባይ የተደረገውን የምግብ ኤግዚቢሽን ለመካፈል ያቀኑ 6 የኢትዮጵያ ነጋዴዎች፣ የተበላሸ ስጋ አቅርበዋል በሚል ለሁለት ወራት ያክል ከአገር እንዳይወጡ ታግተውና ሁለቱ ነጋዴዎች ደግሞ በተደጋጋሚ ሲታሰሩ መቆየታቸውን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው ጭንቅት ውስጥ መግባታቸውን በተደጋጋሚ ከገለጹ በሁዋላ፣በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስና በኢህአዴግ መንግስት መካከል በተደረገ ስምምነት፣ ክሳቸው መነሳቱ ወደ አገራቸው መሄድ እንደሚችሉ እንደተፈቀደላቸው ታውቋል።

ነጋዴዎቹ ከዚህ ቀደም በአለማቀፍ የንግድ ስርአት ውስጥ ባልተለመደ መልኩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው፣ የመነጋጋሪያ አጀንዳ ሆኖ ከርሟል።

አቶ ኦኬሎ አኳይ ለፍርድ ቤት ማብራሪያ ሰጡ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2008)

የቀድሞ የጋምቤላ ፕሬዚደንት አቶ ኦኬሎ አኳይ የጋምቤላ ጭፍጨፋን በተመለከተ ለፍርድ ቤት ማብራሪያ ሰጡ። የጭፍጨፋውን ሂደት በማዛባት፣ የተሳሳተ መረጃ ለህዝብ እንዲያቀርቡ በመገደዳቸውና ጭፍጨፋው የህሊና ሰላም ሰለነሳቸው ፕሬዚደንትነታቸውን ጥለው ድንበር አቋርጠው መሸሻቸውን በጽሁፍ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።

በጋምቤላ ክልል አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2008)

ከ200ሺ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በሚገኙበት የጋምቤላ ክልል የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ግጭት በአዲስ መልክ መቀጣጠሉ ተገለጸ። ይኸው ግጭት በርካታ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን አስጠልሎ በሚገኝበት የጃዊ መጠለያ ጣቢያ መቀጠሉንና በድርጊቱ ተጨማሪ ሰዎች ይሞታሉ የሚል ስጋት መኖሩን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ከ10 ለሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ግድያ ተጠያቂ ናቸው ያሏቸውን 45 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ሃሙስ አስታውቀዋል።

በሰቆጣ ወረዳ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ነዋሪዎች ወደ ደብረ-ብርሃን ከተማ በመሰደድ ላይ ናቸው

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2008)

በአማራ ክልል በሚገኘው የሰቆጣ ወረዳ የተከሰተው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ ተጨማሪ ነዋሪዎች ወደ ደብረብርሃን ከተማ በመሰደድ ላይ መሆናቸውን ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ።
በቅርቡ ወደ ከተማዋ ተሰደው የነበሩት ከ30 በላይ የወረዳው ነዋሪዎችም ወደ ቀያችሁ ካልተመለሳችሁ ተብለው እርዳታ እንዳያገኙ እየተደረገ መሆኑን ነዋሪዎች አስረድተዋል።

የኢንተርኔት አጠቃቀም ረቂቅ ህግ እንዲወጣ የተደረገው ተቃዋዎችንና ጋዜጠኞችን ለመቆጣጠር ነው ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2008)

በቅርቡ በኢትዮጵያ ረቅቆ ለምክር ቤት የቀረበው የኢንተርኔት አጠቃቀም ህግ በአገሪቱ ያሉትን የመንግስት ተቃዋሚዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና የድረ-ገጽ ተጠቃሚዎችን ድምፅ ለማፈን ሆን ተብሎ የታቀደ ህግ እንደሆነ በኬንያ የሚታተመው ኦኬ አፍሪካ የተባለው ጋዜጣ ዘገበ። በኢትዮጵያ የቀረበው አዲስ የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ ተብሎ የሚጠራው ረቂቅ ህግ በብዛት የሚሰራጩ የጹሁፍ መልዕክቶችን ተቀብሎ ማሰራጨት በወንጀል እንደሚያቀጣ ያትታል።

ተመድ በቅርቡ በጋምቤላ የተፈጸመውን ግድያና አፈና አወገዘ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2008)

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን በቅርቡ በጋምቤላ የተፈጸመውን ግድያና አፈና አወገዘ ፥ በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍንም ጥሪ አቅርቧል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ረቡዕ ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ፣ በጋምቤላ የተከሰተ ድንበር ዘለል ግጭት ከ21ሺህ በላይ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዳፈናቀለ ገልጿል።

የውጭ ምንዛሪ ያስገኛሉ ተብለው በመንግስት ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ ኩባንያዎች ውጤታማ አይደሉም ተባሉ

ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008)

የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኙ ታስበው በመንግስት ልዩ የማበረታቻ ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ ከ30 በላይ ኩባንያዎች በየወሩ ስድስት ሚሊዮን ዶላር እንዲያስገኙ ቢጠበቅባቸውም ከ90 ሺ ዶላር በታች ማስመዝገባቸው ተገለጠ።
በጉዳዩ ቅሬታ የተሰማቸው የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ድርጅቶቹ ሲደረግላቸው የቆየ ልዩ ልዩ ድጋፍ ተቋርጦ በኩባንያዎቹ ላይ ምርመራ እንደሚካሄድ አሳስበዋል።
እነዚሁ በብረታ-ብረትና በኤሌክትሮኒክስ ማምረት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙት ድርጅቶች ለምርት ግብዓት የሚሆናቸውን ጥሬ እቃ ያለቀረጥ ወደሃገር ውስጥ እንዲያስገቡና ሌሎችም ድጋፎች ሲደረጉላቸው መቆየቱን የብረታብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል።

በአፍሪካ ሃገራት የመገናኛ ብዙህን ነጻነት እያሽቆለቆለ መምጣቱን አንድ ጥናት አመለከተ

ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008)

ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ሃገራት የመገናኛ ብዙህን ነጻነት እያሽቆለቆለ መምጣቱን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናትን ያደረገ አንድ አለም አቀፍ ተቋም ረቡዕ ይፋ አደረገ።
መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገውና የ2015 ሪፖርቱን ለህዝብ ይፋ ያደረገው ፍሪደም ሃውስ (Freedom House) እኤአ አቆጣጠር በ2015 የአለም የመገናኛ ብዙሃን ባለፉት 12 አመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አሽቆልቁሎ መገኘቱን አስታውቋል።
ከአፍሪካ ቡሩንዲ፣ በመገናኛ ብዙሃን ላይ በምትወስደው የከፋ እርምጃ ግንባር ቀደም ተደርጋ የተቀመጠች ሲሆን በቅርቡ የውጭ መገናኛ ተቋማት ወደሃገሩ እንዲገቡ የፈቀደችው ጎረቤት ኤርትራም ጋዜጠኞችን በማሰር የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን ተግባራዊ እንዳላደረገች ፍሪደም ሃውስ ባወጣው ሪፖርት አስፍሯል።
ተደጋጋሚ ትችት የሚቀርብበት የኢትዮጵያ መንግስት፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በመንፈግ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን አፍኖ መቀጠሉን ድርጅቱ ገልጿል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አዲሱ ትውልድ የኢትዮጵያን አንድነት እንዲጠብቅና የታሪክ ህፀፆችን እንዲያርም ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008)

የኢትዮጵያ አንድነት የመጠበቅና የታሪክ ህፀፆችን ማረም ከአዲሱ ዘመንት ዲሞራቶች ይጠበቃል ሲል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ገለጸ። ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ “ የዘንድሮ ግንቦት 20” በሚል ርዕስ ሰሞኑን ከወህኒ ቤት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው ፅሁፍ ኢህአዴግ ወደስልጣን የመጣበትን 25ኛ አመት በማስመልከት ያለፉትን 50 አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ በመገምገም ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል።

አቶ ኦኬሎ አኳይን ጨምሮ ሰባት ተከሳሾች እስከ ዘጠኝ አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው

ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008)

የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይን ጨምሮ ሰባት ተከሳሾች በተመሰረተባቸው የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ከሰባት እስከ ዘጠኝ አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ።
ተከሳሾች የቀረበባቸውን ወንጀል እንዳልፈጸሙ በመግለጽ የመከላከያ ማስረጃን በማቅረብ ሲከራከሩ ቢቆዩም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ያቀረቡት ማስረጃ የሚያስተባብል አይደለም ሲሉ ውድቅ ማድረጉም ታውቋል።
የተከሳሾች ጉዳይ ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤቱ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ሰባቱ ተከሳሾችን ጋምቤላን ለመበተንና ከፌዴሬሽን ለመገንጠል ሞክረዋል ሲል በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ሲል ወስኖባቸዋል።

ተመድና የኢትዮጵያ መንግስት በጋራ ለምግብ እርዳታ ገቢ የማሰባሰብ ዘመቻ ጀመሩ

ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008)

በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ሰዎች የሚያስፈልገው ድጋፍ በበቂ ሁኔታ አለመገኘቱን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶችና መንግስት በለጋሽ ሃገራት በመዘዋወር ገቢ የማሰባሰብ ዘመቻ ጀመሩ።

ይኸው ማክሰኞ በኖርዌይ መዲና ኦስሎ ከተማ የተጀመረው ድጋፍን የማሰባሰብ ዘመቻው በስዊዘርላንድ ጄኔቫና በዚህ በአሜሪካ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መቀመጫ በሆነችው የኒውዮርክ ከተማ እንደሚካሄድም ታውቋል።
ከ10 ሚሊዮን ለሚበልጡ ተረጂዎች ወደ 1.4 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ቢያስፈልግም፣ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት መኖሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

A former administrator of Gambella sentenced to nine years in prison

ESAT News (April 27, 2016)
Okello Aquay, the former administrator of the Gambella region who was abducted from South Sudan two years ago by operatives of the TPLF regime was sentenced on Wednesday to nine years in prison on trumped up terrorism charges.
Okello was in office in the 2003 genocide against the Anyuak of Gambella perpetrated by the TPLF army. He left his office when coerced by top officials of the TPLF, including the then Prime Minister Meles Zenawi, to blame the killings of the Anyuak on an ethnic conflict with the Nuers.

A human rights council in Ethiopia says government responsible for the loss of lives in the Gambella region.

ESAT News (April 27, 2016)
The Human Rights Council said on Wednesday that the Ethiopian government was responsible for the recent killing of over 200 people and the abduction of women and children in the Gambella region of Ethiopia.
The Council said the government did not protect its citizens knowing very well that armed tribes from South Sudan have repeatedly carried out killings and cattle raids. The Council said the government instead disarmed the people and the local police, leaving them with nothing to defend themselves. It said the local people and officials have requested help from the government before the killings but the government chose to ignore them.
Over 200 people were killed last week in the Gambella region by the Murle tribe men from South Sudan, who also abducted over 100 women and children. The Murles also raided thousands of cattle. The fate of the abductees is yet not known.

Tuesday, April 26, 2016

ሃረር ከቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ ተወጥራ ዋለች

ሚያዚያ ፲፰(አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ 2 ሺ በላይ ቤቶችን ለማፍረስ በዝግጅት ጋር ያለው የክልሉ መንግስት፣ ዛሬ ከህዝብ ጋር ተፋጦ መዋሉን ወኪላችን ገልጿል። ህዝቡ “ከ10 አመታት በፊት ቤቶችን ስንሰራ ዝም ብላችሁ አሁን ለምን እርምጃ ለመውሰድ ተነሳችሁ? በክረምት ቤተሰቦቻችንን ሜዳ ላይ መበተን ሰብአዊነት ነው ወይ? ለምን ቤቶቹን ህጋዊ አታደርጉልንም?” የሚሉ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ የቆዬ ቢሆንም፣ መልስ ሊያገኝ አልቻለም።

በሸንኮር መስተዳደር ስር በሚገኙ አካባቢዎች 1 ሺ ያላነሱ ቤቶች እንደሚፈርሱ የገለጸው ወኪላችን ፣ ዛሬ ሸንኮር መስተዳድራና በድሬ ጥያራ መለያ ቦታ ላይ በሚገኘው ድልድይ ላይ ነዋሪዎች ቋጥኝ ድንጋይ እያንከባለሉ መንገዶችን የዘጉ ሲሆን፣ ይህን አልፎ በሚመጣ ላይ እርምጃ እንወስዳለን በማለት በመናገር ላይ ናቸው።
ቤቶቹ የሚፈርሱት በሸንኮር ወረዳ፣ ከአቡበክር ወረዳ፣ ከሃኪም ወረዳ እንዲሁም ከሶፊ ወረዳ ናቸው። ጊዮርጊስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ቤት አፍራሽ ግብረሃይል ቤት ማፍረስ የጀመረ ሲሆን፣ ህዝቡ ቀኑን ሙሉ በጩከት ተቃውሞውን ሲገልጽ ውሎአል። አንድ አዛውንት የጎረቤታቸው ቤት ሲፈርስ አይተው በድንጋጤ ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።
ቤቶቻቸው የሚፈርሱባቸው ሰዎች በየአመቱ ግብር ይገብሩ እንደነበር ነዋሪዎች በማነጋገር ወኪላችን ከላከው መረጃ ለመረዳት ይቻላል።

የደቡብ ኦሞ መምህራን ያነሱዋቸው አገራዊ ጥያቄዎች ባለስልጣናቱን አስቆጡ

ሚያዚያ ፲፰(አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓም የጸረ ሙስና ጥምረት በሚል ፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ቦዲ ፣ የ8 ወረዳዎች ጸረ-ሙስና ኮሚሺነሮች፣ የሃይማሮት ተቋማት ተወካዮች፣ የእድር አመራሮች፣ የመምህራን ማህበራት፣ የንግድ ማህበረሰብ ማህበር ተወካዮች፣ የሴቶችና ወጣቶች ፎረም እንዲሁም የደኢህዴን ተወካዮች በተገኙበት በተካሄደው ስብሰባ መምህራንና የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች በርካታ አገራዊ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

በጋምቤላ የቤት ለቤት ፍተሻ በመካሄድ ላይ ነው

ሚያዚያ ፲፰(አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደዘገቡት በጃዊ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የተደረገውን ግድያ ተከትሎ በከተማው የሚታየው ውጥረት እንዳጨመረ ሲሆን፣ ዛሬ ፖሊስ አውራ ጎዳናዎችን በመዝጋት እንዲሁም በሰዎች መኖሪያ ቤቶች በመግባት ፍተሻ ሲያደርግ ውሎአል።

የኑዌር ሱዳናውያን ከአንድ የመኪና አደጋ ጋር በተያያዘ የወሰዱት አሰቃቂ እርምጃ የ21 ኢትዮጵያውያንን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን ለምን ተጠቃን በሚል ስሜት የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ያደረጉት ጥረት በፖሊሶችና መካለከያ ጣልቃ ገብነት እንዲቆም ተደርጓል። ይሁን እንጅ ጥቃቱ በኢትዮጵያ ኑዌሮችም ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ገልለተኛ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ሁኔታው እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ የኢትዮጵያ ኑዌሮች ከደቡብ ሱዳን ኑዌሮች ጋር የሚያገናኛቸው አንዳች ነገር እንደሌለና በከተማዋ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ይህን እንዲረዱላቸው በመጠየቅ ላይ ናቸው።

Monday, April 25, 2016

ከጋምቤላ ተጠልፈው የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን የደህንነት ሁኔታ አልታወቀም

ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሙርሌ ጎሳ አባላት ተጠልፈው የተወሰዱት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን፣ አስረኛ ቀናቸውን ቢያስቀጥሩም እስካሁን ሰዎቹ ስላሉበት ሁኔታ በቂ መረጃ ሊገኝ አልቻለም።

ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓም የሙርሌ ጎሳ አባላት በኑዌር ኢትዮጵያውያን ላይ በሰነዘሩት ጥቃት፣ ከ143 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩት መቁሰላቸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶችና ህጻናት እንዲሁም ከ2 ሺ በላይ የቀንድ ከብቶች ደግሞ መዘረፋቸው መዘገቡ ይታወቃል። ድርጊቱን የፈጸሙት ሃይሎች የሚገኙበትን ቦታ ለማወቅ መቻሉንና ከበባም መደረጉን መንግስትን በመጥቀስ የአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ጨምሮ ዜናውን ቢዘግቡም፣ እስካሁን ድረስ በኢህአዴግ መንግስት በኩል የተወሰደ እርምጃ የለም።

በድሬዳዋ በርካታ ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ

ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚያዚያ 17 ንጋት ላይ በድሬዳዋ የጣለው ከባድ ዝናብ እስካሁን ድረስ በትንሹ 15 ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ወደ መልካ ጀብዱ የሚወስደው ድልድይ የተሰበረ ሲሆን አንድ ገልባጭ የጪነት መኪናም በጎርፍ ተወስዷል። ወደ መልካ ጀብዱ በሚያሻግረው ወንዝ አንድ ድልድይ ተሰብሮ በህዝብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ የነበሩ 18 ሰዎች መወሰዳቸውን እንዲሁም 1 ዩዲ ገልባጭ መኪና ረዳትና ሹፌር በጎርፍ መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በደብረዘይት የመከላከያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) የተሰሩ የእርሻ መኪኖች ጥራት የሌላቸው መሆኑ ቅሬታ መፍጠሩ ተነገረ፡፡

ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የገዢው መንግስት በእርሻ ስራ ያደራጃቸው ወጣቶች እንዲሰሩበት የተሰጣቸው የእርሻ መኪና ጥራት ዝቅተኛ በመሆኑ ስራቸውን አቁመው ማህበራቸወን ለመበተን መገደዳቸውን ተናገሩ፡፡

በክልሉ ልዩ ልዩ ዞኖች የሚገኙት ቅሬታ አቅራቢ ወጣቶች ከዩኒቨርስቲና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ትምህርታችውን በመጀመሪያ ዲግሪና በዲፐሎማ ያጠናቀቁ ናቸው፡፡ ወጣቶቹ በእርሻ ስራው ለመሰማራት የሚያስችል ፕሮፖዛል አቅርበው ተቀባይነትን በማግኘቱ ገንዘብ በመቆጠብ ብድር ቢፈቀደላቸውም፤ባቀረቡት የሃሳብ እቅድ ዝርዝር (ፕሮፖዛል) ሳይሆን ንብረቱን ከመከላከያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) እንዲቀርብላቸው መደረጉ ለችግሩ ዋና ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ፡፡

አልሸባብ አንድ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ ስድስት የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ

ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡባዊ ሶማሊያ ግዛት አወዲን ከተማ አቅራቢያ አውራጎዳና ላይ በተጠመደ ቦንብ አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ ስድስት ወታደሮችን መግደሉን ድርጅቱ አስታውቋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በአካባቢው ወደ ነበረው የወታደራዊ ካንፕ ሲያመሩ በነበሩት ወታደሮች ላይ ጥቃቱ መፈጸሙን ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረትም ሆነ የኢህአዴግ መንግስት ስለደረሰው ጥቃት የሰጡት መግለጫ የለም።

Saturday, April 23, 2016

በወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ፤ ሞትና ስደት ለማስቆም ሁላችንም ጠንክረን እንታገል!!!

የአርበኞ ግንቦት 7 ሳምንታዊ ርዕስ አንቀጽ

አፕሪል 22 2016
ህወሃት ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በህዝባችንና በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ወንጀል ቁጥር ስፍር የለውም። እስከ አምናና ካቻምና የሆነውን እንኳ ትተን በዚህ በያዝነው አመት ብቻ በወገኖቻችንና በአገራችን ላይ ከተፈጸሙት ወንጀሎች ጥቂቶቹን ብናስታውስ የሚከተሉትን እናገኛለን ፤
በጎንደር በኩል አገራችንን ከሱዳን ጋር የሚያዋሰነውን ለምና ድንግል መሬት ቆርሶ ለርካሽ የፖለቲካ ጥቅም ማራመጃ ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተፈጸመውን ስውር ስምምነት የተቃወሙ በርካታ ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ ስቃይና እንግልት ተፈጽሞአል።
ለዘማናት ተዋህዶ የኖረውን የቅማንትና የአማራ ህዝብ በማንነት ጥያቄ ለመከፋፈልና ለማጋጨት በተደረገው ደባ በርካታ ንጹሃን ዜጎች ህይወት እንዲቀጠፍ ተደርጎአል።

Ethiopian government charges opposition politician, protesters with terrorism

ESAT News (April 22, 2016)

The Ethiopian government on Friday charged a leading member of an opposition party, Bekele Gerba and 21 others with terrorism, quoting its anti-terrorism proclamation that the regime uses to silence dissent.

South Sudan refugees in Gambella kill 13 Ethiopians

ESAT News (April 22, 2016)

South Sudan refugees in Gambella, Ethiopia killed at least 13 Ethiopians on Thursday after a car accident claimed the lives of two of their own. The refugees at the Jawi camp in Gambella went on a killing spree, apparently motivated by revenge, after an Ethiopian driver struck and killed two refugees.

Friday, April 22, 2016

በጋምቤላ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገደሉ

ሚያዚያ ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት ፣ ሚያዚያ13፣ 2008 ዓም አንድ ኢትዮጵያዊ ሹፌር፣ ከጋምቤላ ከተማ በ 13 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በጃዊ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ሁለት የደቡብ ሱዳን የኑዌር ተወላጆችን ገጭቶ መግደሉን ተከትሎ፣ ስደተኞቹ በቀን ስራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ እስካሁን በትንሹ 13 ሰዎች ተገድለዋል፤ ነዋሪዎች በበኩላቸው የሟቾች ቁጥር ከ20 በላይ ነው ይላሉ። 10 ሰዎች ክፉኛ መቁሰላቸው የታወቀ ሲሆን፣ በተለይ ወደ ጫካ የተሰደዱት ዜጎች ሁኔታ ሲታወቅ፣ የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊደርስ ይችላል ተብሎ ተፈርቷል። ከተገደሉት መካከል በየተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችም ይገኙበታል። መንግስትም ሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን የሰጡት መግለጫ የለም።

ከሟቾቹ መካከል 4 አስከሬን ወደ ወልቂጤ እና ወሊሶ ሲጓጓዝ፣ የሌሎቹን ማንነት እስካሁን ለመለየት አለመቻሉን ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል።ካለው ጥበቃ አንጻር ወደ ሆስፒታል ገብቶ ለማጣራት መኩራ ቢያደርግም እንዳልተሳካለት የገለጸው ወኪላችን፣ በሆስፒታሉ አካባቢ ዘመዶቻቸውን ፍለጋ ላይ ታች የሚሉ ሰዎችን መመልከቱን ገልጿል።
በካምፑ ውስጥ የሚገኙት የደቡብ ሱዳን የኑዌር ተወላጆች፣ በኢትዮጵያ ኑዌሮች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ሲያወግዙ መሰንበታቸውን የሚገልጸው ወኪላችን፣ መንግስት የኑዌር ጎሳ አባላትን የጦር መሳሪያ ባይቀማ ኖሮ ይህ ሁሉ ጉዳት ሊደርስ አይችልም ነበር ብለው እንደሚያምኑ እና አሁን የመኪና አደጋውን ሰበብ አድርገው የወሰዱት እርምጃ ፣ በቀላቸውን በኢህአዴግ መንግስት ላይ የተወጡ ስለመሰላቸው ሊሆን ይችላል ብሎአል፡፡
በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በክልሉ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የደህንነት ጥበቃ እንዲደረግላቸው ቢጠይቁም፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት ራሳችሁን ተከላከሉ፣ የሚል መልስ እንደሰጡዋቸው ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት በኑዌር ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግድያ እና ጠለፋ ተከትሎ፣ የህወሃት ልሳን የሆነው ሬዲዮ ፋና ፣ መንግስት ደቡብ ሱዳን ውስጥ በመግባት የጎሳውን አባላት መክበቡንና ህጻናቱና ሴቶች ያለቡት ቦታም መታወቁን መዘገቡን ተከትሎ የአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዜናውን ተቀባብለው ቢያሰራጩትም፣ እስካሁን ድረስ የተወሰደ እርምጃ አለመኖሩ “ ለምን?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል። በተለይ የኢህአዴግ መንግስት ተሽቀዳድሞ የደቡብ ሱዳን መንግስትም ሆነ አማጺዎች ከጥቃቱ ጀርባ እጃቸው የለበትም በማለት የሰጠው መግለጫ ፣ ዘግይቶ የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ከሚሰጡት መግለጫ ጋር የመጣረስ ሆኗል።
በደቡብ ሱዳን መንግስት ጦር ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ የሆኑት የሙርሌ ጎሳ ተወላጅ የሆኑት ሌተናንት ጄኔራል ዳቪድ ያው ያው እንደተናገሩት ፣ ጥቃቱን የፈጸሙት ሃይሎች በቦማ ግዛት አስተዳዳሪ በሆኑት ባማ ሜዳን የተደራጁና የታጠቁ ናቸው። ጄኔራሉ ከጥቃቱ ጀርባ የግዛቱ አስተዳዳሪ እጅ እንዳለበት ተጨባጭ መረጃ እንደደረሳቸው ገልጸው፣ ጥቃቱን የፈጸሙት ልካንጎሌ ግዛት ውስጥ የሚገኙ የእርሳቸው የጎሳ አባላት መሆናቸውንና አካባቢው የአሁኑ የጎማ አስተዳዳሪ የትውልድ ቦታ መሆኑን አስረድተዋል።
እርሳቸው የሚመሩት ኮብራ የሚባለው ጦር እጁ እንደሌለበት የገለጹት ጄኔራሉ፣ በተቃራኒው የደቡብ ሱዳንን መንግስትን መወንጀላቸውን ሱዳን ትሪቢውን ዘግቧል። ቀደም ብሎ በተሰራጨ ዘገባ የቦማ ግዛት አስተዳዳሪ ጥቃቱን በጄ/ል ያው ያው የሚመራው ጦር ፈጽሞታል ብለው እንደሚያስቡ ገለጸው ነበር።
የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት እርስ በርስ መወነጃጀላቸው ከጥቃቱ ጀርባ ፖለቲካዊ ይዘት ሊኖረው እንደሚችል ተገምቷል።

የአዲስ አበባ ታክሲ እና የረጅም ርቀት ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶች ስራ ለማቆም እንደሚገደዱ አስጠነቀቁ

ሚያዚያ ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ታክሲ እና የረጅም ርቀት ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶች ከመለዋወጫ እቃዎች ዋጋ ንረት ጋር በተያያዘ የታሪፍ ማስተካከያ እንዲደረግላቸው ለአዲስ አበባ እና ለፌደራል የትራንስፖርት ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ያቀረቡት አቤቱታ ተግባራዊ ምላሽ ባለማግኘቱ ስራ ለማቆም እንደሚገደዱ አስታወቁ።

ዛምቢያ 16 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ማሰሩዋን አስታወቀች

ሚያዚያ ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች በዝምባብዌ አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ሲሞክሩ መያዛቸውን የአገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል። ስደተኞቹን ያመላልሳሉ ተብለው የተጠረጠሩ 2 ሰዎች መያዛቸውንም ፖሊስ አስታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ 30 ሺ ሽልንግ ለፖሊሶች ጉቦ ለመስጠት መሞከራቸውን ሉሳካ ታይምስ ዘግቧል።

በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ አቶ አለማየሁ መኮንን በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ

ሚያዚያ ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው መጋቢት 17/08 ተይዘው እስከ ትናንት በሃዋሳ ታስረው የነበሩት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞን ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን፣ የኦህዲኅ አባል የሆኑት አቶ አብረሃም ብዙነህና የቀድሞው አንድነት የዞኑ አስተባባሪ የነበሩት አቶ ስለሺ ጌታቸው ሚያዚያ 13-08-08 ዓም ፍርድ ቤት ቀርበው ምንም አይነት ማስረጃም ሆነ መረጃ ያልቀረበባቸው በመሆኑ ፣ ፍርድ ቤቱ በአስር ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ እንዲፈቱ እንደወሰነላቸው ተከሳሾች ባልቀረቡበት ሁኔታ ተነግሯቸዋል።

Wednesday, April 20, 2016

Ethiopian civic and political organizations call on the WHO to reject the candidacy of Dr. Tedros Adhanom for the position of Director General

ESAT News (April 19, 2016)
Twenty civic and political organizations wrote a letter to the Chairman of the Executive Board of the World Health Organization (WHO) calling for the rejection of Dr. Tedros Adhanom’s candidacy for the position of the Director General of the WHO.
In a letter to Ms. Malebona Precious Matsoso Chairman of the Executive Board of WHO, the 20 Ethiopian organizations said “Dr. Adhanom’s nomination as the sole candidate representing Africa is not only an insult to Ethiopia but to all Africans. His candidature must be read in the context of the political, social and economic policies of the government of Ethiopia that he represents.”

Over 20,000 people displaced in Gambella following attack by armed group from South Sudan, death toll reaches 230

ESAT News (April 19, 2016)
Over 20,000 people have been displaced in Gambella following Friday’s attack by armed men from South Sudan’s Murle tribe that killed 230 and abducted 140 women and children.
Head of the Gambella Regional State, Gatluwick Tut told local reporters that the displaced were from three Woredas of the Nuer Zone – Malawe, Jikao and Lare.
Officials of the Gambella region have said the Murle tribe in South Sudan have attacked the Nuer and Anyuaks in Ethiopia several times before. The federal government meanwhile said it was waiting on permission from the South Sudan government to cross the border and launch an attack on the Murles.
Regional experts said the South Sudan government has tried several times to disarm the Murles with no luck. The experts added the Murles who reside in Jogle province were well armed and control a vast area under their stronghold.

Tuesday, April 19, 2016

በጋሚቤላ ወገኖቻችን ላይ ለደረሰው ጭፍጨፋ ተጠያቂው ወያኔ ነው!!!

ባለፈው ዓርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው በመግባት በላሬና ጃካዋ ወረዳዎች በሚኖሩ የኑዌር ወገኖቻችን ላይ ጭፍጨፋ ማካሄዳቸውን በአገዛዙ ቁጥጥር ሥር ያሉ ሚዲያዎች ጭምር ዘግበዋል። 
ህወሃት ሥልጣን ከተቆጣጠረ ወዲህ በጋምቤላ ክልል ነዋሪ በሆኑ ወገኖቻችን ላይ እንዲህ አይነት የጅምላ ጭፍጨፋ ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በ1996 የህወሃት ልዩ ጦር የተሳተፈበት የዘር ማጥፋት ወንጀል በአኝዋክ ተወላጆች ላይ ተካሂዶ ከ400 በላይ ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸው ተቀጥፎአል። በወቅቱ የፈደራል ጉዳዮች ሃላፊ የነበረው አባ ጸሃይና ሌሎች ቱባ ቱባ የመከላኪያና የደህንነት ባለሥልጣናት እጃቸው እንደነበረበት ቢታወቅም እስከዛሬ ድረስ አንዳቸውም ለፍርድ አልቀረቡም። ከ1996ቱ ጭፍጨፋ በተጨማሪም በክልሉ የሚካሄደውን የመሬት ቅሚያ የተቃወሙ፤ ከአያት ቅድሜ አያቶቻችው የወረሱትንና እትብታቸው ከተቀበረበት በሃይል አንፈናቀልም ያሉ በርካቶች ተገድለዋል ፤ ተደብድበዋል፤ ለእስርና ለስደት ተዳርገዋል። ከእስርና ከስደት ያመለጡ በርካቶችም በገዛ መሬታቸው ለአዳዲሶቹ ባለሃብቶች ጭሰኛ ሆነዋል አለያም ለጎዳና ተዳዳሪነት ተዳረገዋል። ይህ ሁሉ ግፍና መከራ አልበቃ ብሎ ከሰሞኑ ደግሞ "ማንነታቸው ያልታወቁ" የተባሉ ታጣቂዎች ከጎሬቤት ደቡብ ሱዳን ድንበር ተሻግረው ከ208 በላይ የኑዌር ተወላጅ ወገኖቻችንን ጨፍጭፈው ወደመጡበት ተመልሰዋል። ከተጨፈጨፉት ወገኖቻችን ከሃምሳ በላይ የሆኑት ህጻናት ሲሆኑ ሴቶችና አቅመ ደካማ የሆኑ ሽማግለዎች ቁጥርም ቀላል አይደለም።
ለመሆኑ ወያኔ "ማንነታቸው ያልታወቀ" የሚላቸው እነዚህ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው 40 እና 50 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገብተው ምንም መሣሪያ ባልታጠቁ ወገኖቻችን ላይ እንዲህ አይነት ጭፍጨፋ ሲፈጽሙ የአገር ዳር ድንበር ለመጠበቅ የተቀጠረው መከላኪያ ሠራዊት አንዳችም የአጸፋ እርምጃ እንዳይወስድ ካምፕ ውስት ተዘግቶ እንዲቀመጠ የተደረገው ለምንድነው?የጥቃት ፈጻሚዎቹ ማንነትና የመጡበት ቦታ እንኳ በትክክል እንዳይታወቅና ተድበስብሶ እንድቀርስ የተፈለገው በምን ምክንያት ነው?

በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር 230 መድረሱንና ከ140 በላይ ህጻናትና ሴቶች መወሰዳቸውን የአካባቢው ምንጮች ገለጹ

ባለፈው አርብ፣ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓም በጋምቤላ በከፍተኛ ሁኔታ የተጣቁ ወታደሮች በኑዌር ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸሙት ጥቃት፣ መንግስት እንኳን ባመነው፣ 208 ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ100 በላይ ቆስለዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ተወስደዋል፣ ከ2 ሺ ያላነሱ የቀንድ ከብቶችም ተወስደዋል።የአካባቢው አስተማማኝ ምንጮች እንደሚሉት ዋናው ጥቃት በተፈጸመበት በጅካዎ እና በላሬ መስመር ብቻ እስከዛሬ ቀን ድረስ የ230 ሰዎች አስከሬን ተገኝቶአል። ተጠልፈው የተወሰዱት ህጻናት ቁጥር ደግሞ 143 ደርሶአል። በማኩዌ አካባቢ በተፈጸመው ጥቃት ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ ገና እየተጠራ በመሆኑ፣ የማቾች ቁጥር ከተጠቀሰው በላይ ይሆናል ሲሉ እነዚሁ ምንጮች ተናግረዋል። ጥቃቱ በተፈጸመበት አካባቢ ሰፍረው የሚገኙ ዜጎችን መንግስት ወደ ጋምቤላ ከተማ እየወሰዳቸው መሆኑንም ምንጮች አክለዋል። በመከለከያ ቦታ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአንዳንድ አካባቢዎች ዛሬ ቅኝት ሲያደርጉ ታይተዋል። 

በሃረሪ ክልል ሃብሊና ኦህዴድ እየተወዛገቡ ነው

የክልሉ የኢሳት ወኪል እንደገለጸው፣በሃረር ከተማ የሸንኮር ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ አፈንዲ ሰሎሞን በጸረ -ሙስና ኮሚሽን አማካኝነት በከፍተኛ ሙስና ተወንጅልው እስር ቤት መግባታቸውን ተከትሎ፣ የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ( ሃብሊ) እና የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲ ድርጅት ( ኦህዴድ) እየተወዛገቡ ነው። 
አቶ አፈንዲ የሃብሊ አባል ሲሆኑ፣ ኦህዴዶች ሆን ብለውአስገምግመው እንዲታሰር አስደርገውታል በማለት ሃብሊዎች የኦህዴድ መሪዎችን እየወነጀሉ ነው። ክልሉን በዋነኘነት የሚያስተዳድሩት ሃብሊዎች ቢሆኑም፣ ከእነሱ በመቀጠል በሁለተኛ የስልጣን ደረጃ ላይ የሚገኙት ኦህዴዶች የሃብሊን ስልጣን አይቀበሉትም። ኦህዴዶች ሆን ብለው በሙስና ስም የሃብሊ አባላትን ከጭዋታ ውጭ እያደረጉዋቸው ነው በማለት ሃብሊዎች ቅሬታ ያሰማሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ የሃረር ከተማ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ ያሲን ሁሴን፣ ቀድሞ የቀበሌ ቤት፣ በሁዋላ ደግሞ ጤና ጣቢያ የሆነውን ቤት በማስለቀቅ የግል መኖሪያ ቤት ማድረጋቸውን ተከትሎ ህዝቡ ተቃውሞውን ቢገልጽም የሚሰማው ማጣቱን ወኪላችን ገልጾአል። ግለሰቡ ለቤት ማደሻ በሚል 1 ሚሊዮን ብር እንደተመደበላቸው የገለጸው ወኪላችን፣ ለህዝቡ የተዘጋጀው ተለዋጭ ጤና ጣቢያ ለትራንስፖርት አገልግሎት አመቺ አለመሆኑን ጠቅሷል።

ዝዋይ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የዝዋይ ሃይቅ በደረሰበት የኬሚካል ብክለት ሳቢያ አደጋ ውስጥ ነው ተባለ

በአካባቢው የሚገኙ የአበባ እርሻዎችና ፋብሪካዎች ወደ ሃይቁ በሚደፉት መርዛማ ኬሚካሎች ምክንያት የሃይቁ የአሳ ሃብት እየተመናመኑ መጥተዋል። በያዝነው ዓመት ብቻ ሃይቁ በአሁኑ ወቅት አንድ ሜትር ወደ ታች ወርዷል።የችግሩ አስከፊነት እያሳሰባቸውና እየተባባሰ መምጣቱን የ አካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በአካባቢው ካሉ ገሊላ፣ ደብረሲና፣ደብረፂዮን፣ጠደቻና ፉንድሮ ደሴቶች ነዋሪዎች በተጨማሪ ሌሎችም በአሳ ማምረት ስራ ላይ መሰማራታቸው ከኬሚካሉ ቀጥሎ ሃይቁ ላይ ጉዳት አስከትሏል። ሃይቁ በመበከሉ ምክንያት የዝዋይ ከተማ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ በመቸገራቸው ቡልቡላ የሚመጣን ውሃ ለአንድ ጀሪካን 15 ብር በመክፈል መጠቀም ግድ ሆኖባቸዋል። አቅም የሌላቸው ገዝተው መጠቀም ስለማይችሉ ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች መዳረጋቸውን ነዋሪዎቹ ያናገራሉ።
ሃይቁ የቱሪስት መስ ህብ በመሆኑ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ስለጉዳዩ ተጠይቀው ጉዳዩን ሰሚ አካል ማግኘት እንዳልቻሉና ጉዳዩ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን የቢሮው ሃላፊ ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ የተከለከሉ የግብርና ኬሚካሎች ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑንና ሃይቁ አደጋ ላይ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።በኢትዮጵያ የተፈጥሮና አካባቢ ጥበቃ ባለመኖሩ በሃረርጌ የአለማያ ሃይቅ መንጠፉ ይታወሳል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተቃውሞ ገጠማቸው

ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ውይይት ላይ ለመሳተፍ በድንገት ስዊድን የተገኙት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ መረጃው ደርሶአቸው በፍጥነት በተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ገጥሞአቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ፣ ደ/ር ቴዎድሮስን፣ ሌባ፣ ገዳይ በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል።
ወደ ስዊድን እንደሚመጡ አስቀድሞ ሳይነገር በመገኘታቸው ተቃውሞ ለማዘጋጀት አለመቻሉን የሚናገሩት ኢትዮጵያውያን፣ ከያሉበት በስልክ ተደዋውለው በመጠራራት፣ ተቃውሞአቸውን መግለጻቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። ዶ/ር አድሃኖም በከፍተኛ የጸጥታ ሰራተኞች ታጅበው ወደ አዳራሹ መግባታቸውን ለኢሳት ከተላው ፊልም መመልከት ይቻላል።

እኛ የወልቃይት ጠገዴ የጎንደር አማራ ህዝብ የወያኔ ሴራዋን አውቀን ብንታገስም ወደ ግጭት እንድንገባ በማድረግ ህዝባችንን ለመጨረስ ዝግጅት እያደረገች ነው

ቀን፡ ሚያዝያ 10/2008 ዓ/ም
እኛ የወልቃይት ጠገዴ የጎንደር አማራ ህዝብ የወያኔ ሴራዋን አውቀን ብንታገስም እንኳ በምታደርስብን ስቃይ ወደ ግጭት እንድንገባ በማድረግ ህዝባችንን ለመጨረስ ዝግጅት እያደረገች ነው!!!
በዚህ ሳምንት በወልቃይት ጠገዴ በዳንሻ ከተማ የሚገኙ ሁለት የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች “የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጎንደሬ አማራ ነው” ብላችሗል ተብለው ከትምህርት ገበታቸው ተባረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትምህርት ቤቱ የሚያስተምር አንድ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ መምህር ገ/ፃድቃን ከተባለ
ትግሬ የኬምስትሪ መምህር ጋር “ወልቃይት ጠገዴ አማራ ነው” ብሎ ስለ ተከራከረው ብቻ ከትግራይ አስተዳደሩ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት ይገኛል።
ሌላው አስገራሚ የሆነው ክስተት ደግሞ በትላንት እለት በቃብቲያ በጠቅላላው ደግሞ በዚህ ሳምንት በአዲረመጥ የወልቃይት ህዝብን የክልል ሃላፊዎች ስብሰባ በማካሄድ “መሬት እንስጣችሁ ፤ ተሰብሰቡ”
ሲሏቸው “ይህ የቆማችሁበት ወልቃይት የተባለ መሬትና ህዝብ እናንተ እንደምትሉት የእናንተ የትግራይ ሳይሆን የጎንደር ስለሆነ መሬቱ የኛ የራሳችን የጎንደሬዎቹ ሆኖ ሳለ ከየት ያገኛቹሁት

An Open Letter to Mr. Barack Obama – By Andualem Aragie (Prisoner of conscience)

the president of the United States of America,
Dear President Obama,
I am a son of a poor farmer who sustains his family in subsistence agriculture and still is. I am the son of that farmer, who did not try to change the life of his father, nor that of his own, believing from the outset that, it is when societal, political and economic problems are properly dealt with first that we can prosper as a nation or as a family. Mr. President, I am the son of that farmer, who tried to peruse his dream to change the conditions of his people to the better since my university campus days as a student leader and later on as an opposition politician before finally finding myself labeled a terrorist by the Ethiopian regime. I am sentenced to life imprisonment and languishing in the worst prison in Ethiopia, Kaliti Prison.

Thursday, April 14, 2016

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ ታጣቂዎች በአርማጭሆ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የግድያ ዘመቻ ከፈቱ፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ ታጣቂዎች በአርማጭሆ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የግድያ ዘመቻ ከፈቱ፡፡
‪#‎ትክል‬ ድንጋይ እና አካባቢው በህወሓት ሰራዊት ተከቦ የጦር ቀጠና እንደመሰለ እየተገለፀ ነው፡፡
‪#‎43ኛ‬ ክፍለ ጦር የአባላቱ ቁጥር ተመናምኖ በሻለቃ ደረጃ በመድረሱ በ24ኛ ክፍለ ጦር ስር እንዲሆን ተደርጎ ከሸዋ ሮቢት ወደ አዘዞ እና ዳንሻ መዛወሩ ታወቀ፡፡

የህወሓት አገዛዝ ታጣቂዎች በአርማጭሆ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የግድያ ዘመቻ ከፈቱ፡፡
በላይ አርማጭሆ ኩርቢት የተሰማሩት የህወሓት ታጣቂዎች ሚያዚያ 3 2008 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ላይ አቶ አርጋው ሲሳይ ወደተባሉት ድሃ ገበሬ ቤት በመሄድ ገድለው ንብረታቸውን ዘርፈው ተመልሰዋል፡፡

Sharing anti-government messages, audiovisuals to become unlawful in Ethiopia

ESAT News (April 13, 2016)
The Ethiopian government has drafted a law banning the sharing of anti-government protest messages and audiovisuals via phones and computers. The draft law tabled to the parliament on Tuesday make it punishable by law the act of sharing or disseminating any messages or audiovisuals that encourages people to protest against the government.
The Ethiopian government has also began registering every cellphone in the nation while shutting down social media apps for the last one month.
The stringent law and restrictions on the social media came after police brutality and deadly force against peaceful protesters in the Oromia region and elsewhere in the country were instantly shared by millions of Ethiopians worldwide, unmasking the true nature of the tyrannical regime in Addis Ababa.
The law would also allow authorities to spy on personal computers. The law stipulates that investigators, cyber security professionals and other authorities could spy on personal computers with court warrant. Police could spy and search personal computers “if they find it necessary.” Police could detain suspects of “cyber criminals” for 4 months without arraigning the suspects to court.
The Ethiopian government had spent millions of dollars to spy on computers of opposition politicians and journalists living in the US and elsewhere, as revealed by the Washington Post investigative report a year ago.

ሰበር ዜና — አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ለትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን ደህንነት ቢሮ ከፍተኛ እራስ ምታት ሆኗል

በልኡል አለም
የተከበሩት የቀድሞ የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ ለወያኔ በግፍ ተላለፈዉ ሲሰጡ የእንግሊዝ የደህንነት አካላት ያዉቁ እነደነበር እና የየመን የጸጥታ ሐይሎች እንዲሁም የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን በመተባበር እገታዉን እንዳካሄዱት ዛሬ ከብሔራዊ መረጃ ምንጭ ተገኝቷል።

Wednesday, April 13, 2016

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአቶ አባይ ወልዱ ጋር በወልቃይት ጉዳይ ጸብ ውስጥ ነኝ አሉ

ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008)

የወልቃይትን ማንነት በተመለከተ በተነሳው ጥያቄ ዙሪያ የአማራ ክልል ፕሬዚደንት፣ ከትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ጋር ፀብ ውስጥ መሆናቸው ተገለጠ። ይህንን የተናገሩት ራሳቸው የአማራ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሲሆኑ፣ የአማራ ምሁራን ከሩቅ ሆነው ከሚቃወሙ እንደ ትግራይ ተወላጆች ሃብት እንዲሰበስቡም ጥሪ ማቅረባቸው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ በህክምና ላይ የሚገኙትን ባለቤታቸውን ለመጎብኘት በአሜሪካ የሚገኙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የወልቃይት ህዝብን የማንነት ጥያቄ በተመለከተ በርሳቸውና በድርጅታቸው በኩል የተያዘው አቋም የትግራይ ክልል መንግስትንና ህወሃት እንዳላስደሰተ ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ በርሳቸውና በትግራይ ፕሬዚደንት አቶ አባይ ወልዱ መካከል በግልፅ ጸብ መኖሩንም አመልክተዋል።

የመከላከያ ሚኒስቴር ባዘጋጀው ስብሰባ የሰራዊት መክዳት አብይ ርዕስ ነበር ተባለ

ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008)

የመከላከያ ሚኒስቴር የበታች ሹሞችና መኮንኖች ባዘጋጀው የ4 ቀናት ኮንፈረንስ የሰራዊቱ መክዳት አብይ ርዕስ ሆኖ መውጣቱን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ባለፈው ሳምንት የተካሄደውና ከሰኞ እስከ ሃሙስ በቀጠለው ኮንፈረንስ ከተለያዩ የሰራዊቱ ክፍሎች የተውጣቱ የበታች ሹሞችና መኮንኖች በቪዲዮ ኮንፈረንሰ ከመከላከያ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል።
አዲስ አበባ ላይ ሆነው በቪዲዮ ኮንፈረንሰ ማብራሪያና መግለጫ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ሲሆኑ፣ ከፍተኛውን ወታደራዊ ስልጣን የያዙት ጄኔራሉ ከአጠገባቸው ቢሆኑም፣ መድረኩን ሙሉ ለሙሉ ለአቶ ሲራጅ ፈርጌሳ መልቀቃቸውንም ምንጮች አስረድተዋል።

የማህበራዊ ድምጽና ምስል አገልግሎቶች በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተቋረጡ

ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) መንግስት በኢንተርኔት አማካኝነት የሚደረጉ የድምፅና የምስል አገልግሎቶች ላይ አዲስ መመሪያን እንደሚተገብር ማስታወቁን ተከትሎ አገልግሎቱ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተቋረጠ።

በተለይ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተቃውሞ በተቀሰቀሰበት የኦሮሚያ ክልል የትዊተርና የWhatsAPP አገልግሎቶች ከተቋረጡ አንድ ወር አካባቢ እንደሆናቸው ብሉምበርግ የዜና ወኪል የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል።
በኦሮሚያ ክልል በተጨማሪ አገልግሎቶቹ በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማና በተለያዩ አካባቢዎች ተቋርጦ እንደሚገኝም የተለያዩ አካላት ለዜና ወኪሉ ያስታወቁ ሲሆን፣ በምስራቅ ለንደን ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት አቶ ስዩም ሃሜሶ ሃገር ቤት ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንኳን መገናኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በአለም ደረጃ በጣም ውድ የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደምታቀርብ ተገለጸ

ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008)

ኢትዮጵያ በአለማችን ካሉ ሃገራት መካከል የኢንተርኔት አገልግሎትን በጣም ውድ በሆነ ክፍያ በማቅረብ ግንባር ቀደም ሃገር ሆና መገኘቷን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናትን ያደረገ አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ይፋ አድርጓል።
ይኸው የ120 ሃገራትን ታሪፍ በንጽጽር ያቀረበው ኑሚቢዬ የተሰኘው አካል በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ፍጥነት ባለው የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያው የማይቀመስ መሆኑንም አመልክቷል።
የኢትዮ-ቴለኮም ባለስልጣናት ይህንኑ አገልግሎት ጨምሮ በቫይበር የሚደረግ የስልክ ጥሪ ልውውጥ ላይ ክፍያን ተግባራዊ ለማድረግ ምክክርን በማካሄድ ላይ መሆኑን ባለው ሳምንት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በሃገሪቱ በብቸኝነት የስልክ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ኩባንያው በአገልግሎቱ ላይ አዳዲስ የቁጥጥር ስርዓቶችን ተግባራዊ ከማድረጉ ጎን ለጎን የተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችንም ለመመዝገብ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

በኢትዮጵያ 84ሺህ ብቻ የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን CNN ዘገበ

ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008)

በአፍሪካ ባሉት 97 ሚሊዮን ህዝብ ቁጥር በአህጉሪቱ ከናይጀሪያ ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ፣ 84ሺህ የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንዳሏት ተገለጠ።
በጉዳዩ ዙሪያ ልዩ ዘገባን ያቀረበው ሲኤንኤን (CNN) የቴለቪዥን ጣቢያ ሃገሪቱ ከውጭ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ 35 በመቶ ታክስን እንደምታስከፍልም አመልክቷል።
አብዛኞቹ ተሽከርካዎች ከውጭ ሃገር የገቡ መሆናቸውን ያወሳው የቴለቪዥን ጣቢያው በአሁኑ ወቅት 84ሺህ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን ባቀረበው ሪፖርት አስፍሯል።

Worsening defections in the Ethiopian army

ESAT News (April 12, 2016)
Defections by the army was top on the agenda at a recent high level military conference presided by the Minister of Defense, Sirage Fergessa and the Chief of Staff Samora Yenus.
The Minister told the mid-level officers that the study conducted on the root causes of defections by the army was not satisfactory. The participants agreed the study did not cover the real causes of defections but mainly focused on administrative problems in the army.
There have been reports of defections in the Ethiopian army in recent years, with most of the defectors joining armed resistance groups operating from the country’s northern border. Defectors say corruption, nepotism and ethnic favoritism were the reasons for their defections. Scores of air force pilots have defected just in the last couple of years accusing the regime of ethnic favoritism.
About 90% of Ethiopia’s generals and senior officers are from the Tigray ethnic group causing discontent and resentment on the part of the rank and file.
Army generals and high level officers are involved in unbridled high level corruption while the rank and file eke out an existence.

Ethiopia drafts law making it legal for the government to spy on personal computers

ESAT News (April 12, 2016)
The iron fist government in Addis Ababa has drafted a law that would allow authorities to spy on personal computers. The draft has reportedly been tabled to the rubber stamp Parliament for approval.
The law stipulates that investigators, cyber security professionals and other authorities could spy on personal computers with court warrant. Police could spy and search personal computers “if they find it necessary.” Police could detain suspects of “cyber criminals” for 4 months without arraigning the suspects to court.
The draft cites attack on personal computers and institutions as example of cybercrime. It also listed free use of some internet services which the government requires payment as a crime, validating recent reports that the government was planning to charge for the use of free call and text applications. Loss of revenue from long distance calls has seriously affected the single telecom service in the country which is owned by the government.

Tuesday, April 12, 2016

መንግስት በኮምፒዩተሮች ላይ እንደፈለገ ስለላ የሚያካሂድበትን ህግ አረቀቀ

ሚያዚያ ፬( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት እንደፈለገ የግል የኮምፒውተር መረጃዎችን መጥለፍ፣ መበርበር፣ መሰለል፣ ኦን ላይን መፈለግ የሚያስችለውን ህግ አርቅቆ ለፓርላማ አቅርቦአል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ኮምፒውተር ወይንም የኮምፒወተር ስርዓት ምንነት ሲያብራራ በሶፍትዌር እና ማይክሮቺን ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ የዳታ ፕሮሰሲንግ፣ ክምችት፣ ትንተና፣ ስርጭት፣ ግንኙነት ወይንም ሌሎች ሂሳባዊ ወይንም አመክኖአዊ ተግባራትን የሚያከናውን ማንኛውም መሳሪያ ነው ይለዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የኮምፒውተር ወንጀል በፈቃድ እና ለፈቃድ እንደሚከናወን ይጠቅሳል፡፡ በዚሁ መሠረት በሳይበር ደህንነት ባለሙያዎችና መርማሪዎች ወይም ሌሎች በተፈቀደላቸው አካላት፣ በፍ/ቤት ትዕዛዝ የሚደረግ የኮምፒውተር ስርሰራ አያስቀጣም ይላል፡፡ ሌሎች ባልተፈቀደላቸው ወገኖች የይለፍ ቃልና ሌሎችን የደህንነት አጥሮችን ሰብሮ መግባትና ክፍያ የሚጠይቁ የኮምፒውተር አግልግሎቶችን ያለክፍያ መጠቀም እና የመሳሰሉ ድርጊቶች እንደሚያስጠይቁ አስቀምጦአል፡፡

በጅንካ የመከላከያ ሰራዊትና ልዩ ሃይል አባላት ከፍተኛ ቅኝት እያደረጉ ነው

ሚያዚያ ፬( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በደቡብ ኦሞ በጅንካ ከተማና አካባቢዋ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከልዩ ሃይል አባላት ጋር በመሆን፣ በተለይ ከምሽቱ 2 ሰአት ጀምሮ በመኪኖች ላይ መትረጊስና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችን ደግነው ቅኝት በማድግ ላይ ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ የወጣቶች ነጻ እንቅስቃሴ የተገደበ ሲሆን፣ ነዋሪዎችም ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል፡፡
ክትትሉ የተጀመረው በአካባቢው ከፍተኛ እውቅና ያላቸው የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ አቶ ዓለማዬሁ መኮንን፣ አቶ አብረሃም ብዙነህ እና አቶ ስለሺ ጌታቸው መጋቢት 17፣ 2008 ዓም መታሰራቸውን ተከትሎና ፓርቲያቸው መሪዎቹና አባሎቹ ካልተፈቱ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ መግለጫ ማውጣቱን ተከትሎ ነው፡፡

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በ1.1 ብር ሚሊዮን ብር የዋስትና መብት ተፈቀደላቸው

ሚያዚያ ፬( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአክሰስ ሪልስቴት መስራችና ባለቤት የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ዋስትና የቀረበባቸውን ክስ ውጪ ሆነው መከራከር እንደሚችሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብያኔወስኗል።

ባለሃብቱን በደረቅ ቼክና በሌሎች የሙስና ወንጀል ክስ ያቀረበባቸው አቃቤ ሕግ የዋስትና መብቱን እንዲነሳ ቢቃወምም ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን በመቀበል ውጪ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ሲል ብያኔውን ሰጥቷል።
አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የገዥው ፓርቲ አባላትን በማመን በአክሰስ ሪል ስቴት ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለማስተካከል ከሚኖሩበት ከአሜሪካ የተገባላቸውን ዋስትና በማመን መምጣታቸው ይታወሳል።

Ethiopian government stops fundraising campaign by UN agencies for famine to save image

ESAT News (April 11, 2016)
The Ethiopian government has stopped the fundraising campaign by UN agencies to help millions of Ethiopians facing famine, according to ESAT’s sources from Addis Ababa.
The sources said the Special Envoy for the Prime Minister of Ethiopia, Ambassador Berhane Gebrekiristos has asked the Addis Ababa representative of the United Nations Office for the Coordination of Humanitarian Affairs (UNOCHA) to stop the fundraising campaign that began on March 23, 2016. The ambassador reportedly told OCHA’s representative that the position of his government was firm on the matter and OCHA could close up shop and leave the country if it does not agree with the decision of the government.

Britain is giving more than £1m to train security forces who kidnapped Ethiopia’s ‘Mandela’ – Daily Mail

ESAT News (April 11, 2016)
Britain is giving more than a million pounds to train Ethiopia’s security forces – even though the country’s repressive regime abducted a British citizen and holds him under sentence of death, the Daily Mail reported on Saturday.
Andargachew Tsege, a father of three from North London, was snatched almost two years ago while travelling through an airport in Yemen. After being forced on to a plane to Ethiopia, he was paraded on television and held for months in secret detention.

Monday, April 11, 2016

በቶሪኖ የተጠራው የመንግስት ስብሰባ በተቃውሞ ተበተነ

ሚያዚያ ፫( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እሁድ ሚያዚያ 3፣ 2008 ዓም በጣሊያኑዋ የቶሪኖ ከተማ መንግስት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ ለመጨጥ እንዲሁም አወዛጋቢ የሆነውን የኮንዶሚኒየም ሽያጭ ለማከናወን እና የውጭ ምንዛሬ ለመሰብሰብ የጠራው ስብሰባ በከተማዋ በሚገኙ ኢትጵያውያን ተቃውሞ እንዲሰረዝ ተደርጎአል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ ገና ከመነሻው ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ መሰረታዊ የሚባሉ የመብት፣ የእኩልነትና የኢኮኖሚ አስተዳደር ጥያቄዎችን አንስተው ተቃውአቸውን አሰምተዋል፡፡
አንድ አራተኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በተራበበት ሁኔታ፣ ቅድሚያ የሰዎችን ህይወት መታደግ ሲገባችሁ እናንተ ግን የት እንደምታደርሱት ለማይታቅ ገንዘብ ለመሰብሰብ አጀንዳ ከፈታችሁ፤ ይሄ ከአገርም በላይ ሰብአዊነትን የሚመለከት በመሆኑ ቅድሚያ ለሰው ልጅ ህይወት ስጡ ያሉት ዜጎች፣ ከ300 በላይ የኦሮሞ ወገኖች ባለቁበት ሰአት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ታስረው በሚሰቃዩበት በዚህ ወቅት፣ እንዲሁም በወልቃይት ጥያቄ ዙሪያ ዜጎች ስቃያቸውን እያዩ፣ እናንተ ምንም ሳይመስላችሁ፣ ስለ ውጭ ምንዛሬ ልትነግሩን አጀንዳ ከፈታችሁ፣ ይሄ ያሳፍራል ሲሉ በምሬት ትቃውአቸውን ገልጸዋል፡፡ በውጭ ለሚገኘው ዜጋ ቤት ከመጨነቃችሁ በፊት በቅድሚያ ቤት አጥቶ ለሚሰቃየው አገር ቤት ላለው ህዝብ ቤት ስሩለት በማለት፣ በአገር ቤት ህዝብ ቤት አጥቶ እየተሰቃዬ፣ በተሻለ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኘው በውጭ ለሚገኘው ዜጋ ቤት ለመስጠት የሚደረገውን ሩጫ በአስመሳይነት በመፈረጅ አውግዘዋል
ኢትዮጵያውያኑበአገሪቱ ውስጥ የአንድ ብሄር የበላይነት መኖሩን፣ እንዲሁም ከ20 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተርቦ እናንተ ኢሳትን ለማፈን ከፍተኛ ገንዘብ ታወጣላችሁ በማለት የሞራል ጥያቄ አንስተው ተቃውመዋል፡፡ አገሩን ለቀን ወጣንላቸው ፣ እዚህ ደግሞ ገንዘባችንን ፡፡ ሊወስዱ ይመጣሉ በማለት ተቃውሞአቸውን በማሰማት መንግስት ስብሰባውን ለመሰረዝ ተገዱዋል፡፡ በፊላደልፊያም ተመሳሳይ ተቃውሞ መደረጉ ታውቆአል፡፡

የወልቃይት ጠገዴና ፀለምት ተወላጆች በኒዉዚላንድ ኦክላንድ የጠሩት ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።


ሚያዚያ ፫( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኒዉዚላንድ ኦክላንድ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያዉያኖች አጋርነታቸዉንና ወልቃይት አማራ እንጂ ትግሬ አይደለም በሚለዉ የማንነት ጥያቄ ከወልቃይት ጠገዴና ፀለምት ሕዝብ ጋር መሆናቸዉንና ድጋፋቸዉን ለመስጠት ያላቸዉን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
ስብሰባዉንም በእንኳን ደህና መጣችሁ የከፈቱት አቶ አረፈዐይኔ መኮንን በአገር ዉስጥ የወልቃይት ጠገዴና ፀለምት የማንነት ሕዝብ ጥያቄ ሕገመንግስቱ በሚፈቅደዉ መሰረት የማንነታቸዉን ጥያቄ 50 ሺ የሚሆኑ አባወራ አስፈርመዉ ሕጋዊ በሆነ መንገድ አቅርበዉ የተመለሰላቸዉ መልስ ግን እስራት ግርፋት ስደት እንግልት ከዚያም ሲያልፍ ግድያ መሆኑን ነዉ። አሁንም ወጣቱ የሚደርስበት ችግር እቤቱ ለማደር በመቸገሩ ዱር ቤቴ ያለበት መሆኑንም አያይዘዉም ገልፀዋል።
ይህም በመሆኑ እኛ ኢትዮጵያዉያኖች ዛሬ አማራዉ ላይ እየደረሰዉ ያለዉ ጥቃት ከኢትዮጵያ የነፃነት ጥያቄ የተለየ ባለመሆኑ እኛም ይህን የነፃነት ጥያቄ አብረን ከጎን በመቆም ማድረግ የምንችለዉን ሁሉ ማድረግ ይገባናል በማለት ለተሰብሳቢዉ ገለፃ አድረገዋል።
በዚህ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ በተጠራዉ ስብሰባ አቶ ገ/መድህን አርአያ በስካይፕ በመገኘት በቦታዉ ለተገኘዉ ሕዝብ የወያኔን አስከፊ የሆነ አገር የማጥፋት አጀንዳዉን ገና ጫካ እያለ ሲመሰረት ጀምሮ ይዞት የተነሳ መሆኑን ለተሰብሳቢዉ ገልፀዋል።
በቀጣይም የወልቃይት ተወላጅ የሆኑትም አቶ አበራ በራሳቸዉ እና በቤተሰቦቻቸዉ ሕይወት ወያኔ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ በ1972 ዓ.ም ወልቃይት የትግራይ መሬት ነዉ እናንተም ትግሬዎች ናችሁ በማለት ጦርነት በማወጅ በርካታ ያካባቢዉን ሰዎች ገለዉ በተወለዱበት አገር ቤተክርስቲያን እንኳን እንዳይቀበሩ ያደረጉበት እና የነበረዉን ንብረታቸዉን ዘርፈዉ መሔዳቸዉን ተናግረዋል፡፡ አያይዘዉም ከ1976 ዓ.ም እስከ 1978 ድረስ ሽሬ አዉራጃ ዉስጥ በምትገኝ ልዩ ስሟ ዶጋ ዲት በምትባል ትንሽ መንደር ዉስጥ ከ3ሺ በላይ እስረኛ በነበረበት ከመሬት በታች ባለ እስር ቤት ዉስጥ መከራ መቀበላቸዉንም ተናግረዋል።
በዚህ የሁለት አመት የእስር ቆይታቸዉ ከጓደኞቻቸዉ ጋር በሰንሰለት ታስረዉ ከጎናቸዉ አብረዋቸዉ የታሰሩት ሰዎች ሲሞቱ ከ3 እስከ 4 ቀን ድረስ ሬሳዉን ለማዉጣት ባለመፈለግ እና ሆን ብለዉ ከሬሳዉ ጋር ለ3 እና ለ4 ቀናት አብረዉ ታስረዉ እንዲቆዩ እንዳደረጉዋቸው ተናግረዋል።በዚህ ሁሉ የስቃይ ሕይወት ዉስጥ እሳቸዉም እንደ ጓዶቻቸዉም እግዚአብሔር ሞታቸዉን እንዲያቀርብላቸዉ ይለምኑ እነደነበርም ገልፀዋል።
በማያያዝም በእስር ቤት ዉስጥ የደረሰባቸዉን ግፍና በደል ለተሰብሳቢዉ እጅግ ልብ በሚነካ ሁኔታ የገለፁት አቶ አበራ፣ በእስር ቤት ለምርመራ በቀረቡበት ጊዜ በወያኔ ተጋዳይ በሳንጃ ደረታቸዉን ተወግተዉ ላንድ አመት ያህል ያለ ሕክምና መሰቃየታቸዉን እና በእግዚአብሔር ፈቃድ ከዛ መከራ የወጡበት ሁኔታ እንደገጠማቸዉና ወደ ሱዳን እንደተሰደዱ አስረድተዋል፡፡
በዚህ በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ በአዉስትራሊያ ሜልቦርን እና ፐርዝ እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያዉያኖች በተገኙበት የተሳካ ዉይይት እንደተካሔደ አንዱአለም ሀይለማርያም ከኒዉዚላንድ ኦክላንድ ዘግቦአል።

6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ህጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል


ሚያዚያ ፫( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ረሃብ አለማቀፍ ትኩረት እያገኘ ነው፡፡ ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የተመለከተ ዘገባ አቅርበዋል፡፡ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች፣ መንግስትን ላለማስከፋት ፈራ ተባ እያሉም ቢሆን ሁኔታው አስፈሪ መሆኑን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ አሁን ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን ሲመለከቱ፣ ስጋታቸውን በአደባባይ መግለጽ ጀምረዋል፡፡ 6 ሚሊዮን ህጻናት ለከፋ ረሃብ መዳረጋቸውን የአለማቀፉ የህጻነት አድን ድርጅት አስታውቆአል፡፡ በአጠቃላይ ድርቅ ያጠቃው አካባቢ 30 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ መያዙን አልጀዚራ በሰራው ሪፖርት አመልክቶአል፡፡
የዚህን ዜና ሀተታ ከዜናው በሁዋላ እናቀርባለን፡፡

ትግሉ ሰፊ የምሁራን ተሳትፎ ይሻል! (አርበኞች ግንቦት 7)

ኢትዮጵያ በበብዛትም ይሁን በጥራት በውጭው አለምም ይሁን በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ምሁራን ያፈራች ሀገር ነች። በጅጉ የሚያሳዝነው ግን በሀገሪቱና በሕዝቧ ችግር ላይ ሀሳብ ሲሰጡ ፣ ባደባባይ ሲከራከሩና ሲታገሉ የሚታዩት በጅጉ ጥቂቶች ናቸው። ርግጥ ነው ተከታታይ መንግስታት በምሁራን ላይ ያደረሱት ጥቃትና ማግለል ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።

Friday, April 8, 2016

የእንግሊዝ የፓርላማ አባላት የአንዳርጋቸውን ጉዳይ ሊ

የእንግሊዝ ፓርላማ የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ በውጪ አገራት በእስር ላይ የሚገኙ እንግሊዛዊ ዜግነት ያላቸውን (በኢትዮጵያ የሚገኙትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ) እስረኞች ጉዳይ በማጥናት መንግስት በውጪ አገራት በሚገኙ እንግሊዛዊያን ላይ የሚፈጸምን የሰብዓዊ መብት ረገጣን  ለማስቀረት የሚያሳየውን ቁርጠኝነት እመዝናለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡


ትናንት ይፋ የተደረገው ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነም ብዛት ያላቸው እንግሊዛዊያን በውጪ አገራት ታስረው የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ሲፈጸምባቸው መንግስት የሚጠበቅበትን ጫና በማሳረፍ ዜጎቹን ከሚደርስባቸው ጥቃት መከላከል አልቻለም፡፡ባለፈው ዓመት የነሐሴ ወር የወጣን ሪፖርት ኮሚቴው መመልከቱ የተገለጸ ሲሆን በሪፖርቱ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚፈጽሙ አገራት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ለሰብዓዊ መብት መከበር ግድ የማይሰጠው መሆኑን ታዝበዋል ተብሏል፡፡
በፓርላማው የተዋቀረው የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ በመንግስት የሰብዓዊ መብት አከባበር ስራ ዙሪያ ጥልቅ ምርመራ እንደሚያደርግ በመግለጽ በውጪ አገራት የሚገኙ እንግሊዛዊያን እየደረሰባቸው የሚገኝን የመብት ጥሰት በዝርዝርና በጥልቀት በመመልከት የሰብዓዊ መብትን ለማስከበር መንግስት የተጓዘውን ርቀት እንደሚቃኝ አውስቷል፡፡
በለንደን የአንዳርጋቸውን ቤተሰቦች በመርዳት ላይ የሚገኘው ሪፕራይቭ የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀው ከሆነም የፓርላማ ቡድኑ በዋናነት የአቶ አንዳጋቸውን ጉዳይ መመርመር ይጀምራል፡፡
አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጪ መያዛቸውን በመቃወም የተባበሩት መንግስታትና የአውሮፓ ፓርላማ አንዳርጋቸውን ኢትዮጵያ በነጻ እንድትለቅ ሲጠይቁ የእንግሊዝ መንግስት ተመሳሳይ ጥያቄ ሳያቀርብ በመቆየቱ ትችት ሲሰነዘርበት ቆይቷል፡፡ሪፕራይቭ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም የዴቪድ ካሜሮን መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ዋነኛው ደጋፍ አድራጊ መሆኑን ማጋለጡ አይዘነጋም፡፡
ምንጭ ሪፕራይቭ

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችና ደህንነቶች በዋልድባ ቁጥጥር ሲያደርጉ መሰንበታቸው ታወቀ

መጋቢት ፴( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የገዳሙ አባቶች እንደገለጹት መጋቢት 27 የተከበረውን የመድሃኒአለም በአል ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችና ደህንነቶች በገዳሙ በመግባት ቁጥጥርና ክትትል ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡ ሁሉም ደህንነቶች ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ የህወሃት ደህንነቶች መሆናቸውን የሚናገሩት አባቶች፣ ከወልቃይትና ከጎንደር ወደ ገዳሙ የሄዱ ምእመናን ከቤተሚናስ መነኮሳት ጋር ምን አይነት ግንኙነት አላችሁ በማለት ሲያዋክቡዋቸው እና ሲከታሉዋቸው ሰንብተዋል፡፡ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ያሰጋቸው የህወሃት ደህንነቶች፣ ገዳሙን በተለዬ ሁኔታ ቁጥጥር እያደረጉበት ነው፡፡

ከወልቃይት ፣ ከጠገዴ ፣ ከዳንሻ፣ ሁመራ፣ አርማጭና ቆላ ወገራ በወልቃይት መዘጋ አድርገው ወደ ገዳሙ የሚሄዱ ቤተክርስያን ሳሚዎችን፣ ዛሬማ ወንዝ ላይ በማስቆም ከፍተኛ ፍተሻ ሲያደርባቸው ሰንብቶአል፡፡

በአፋር መጪው ጊዜ እጅግ አስፈሪ ነው ተባለ

መጋቢት ፴( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ20 ሚሊዮን ያላነሱ ዜጎችን ለረሃብ አደጋ ያጋለጠው ድርቅ፣ በአፋር ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍቶአል፡፡ እናቶች በየሳምንቱ በሞትና በህይወት መካከል ያሉ ህጻናትን ይዘው ረጅም ርቅት ተጉዘው ህክምና ለማግኘት ይጥራሉ፡፡ ረሃቡ የከፋ መሆኑንና አለማቀፉ ማህበረሰብ ባይደርስ ኖሮ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል የአይ ቲ ቪ ኒውስ ጋዜጠኛ ቦታው ድረስ በመሄድ ዘግቦአል፡፡

በአንድ የህክምና ማእከል ውስጥ የሚሰራ ዶ/ር እንዳለው፣ ህጻናቱ ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ በተለያዩ በሽታዎች ተጠቅተዋል፡፡ ከ400 ሺ በላይ ህጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ዘጋባው አመልክቶአል፡፡

Thursday, April 7, 2016

በአማራው ክልል ፕሬዚዳንት ላይ ያነጣጠረ ግምገማ እየተካሄደ ነው

መጋቢት ፳፱( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በአማራ ክልል ተነስተው የነበሩትንና እስካሁንም መቁዋጫ ያልተገኘላቸውን የቅማንትና የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄን ተከትሎ ለደረሰው ደም መፋሰስ የክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳጋቸውን ተጠያቂ በማድግ የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በመሩዋሩዋጥ ላይ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል፡፡ የወልቃይት ጥያቄ የአቶ ገዱ የአመራር ችግር እንጅ የአማራ ህዝብ ጥያቄ አይደለም በሚል፣ ፕሬዚዳንቱን ከብአዴን አባላት እና ከህዝቡ ጋር በማጋጨት፣ ጥያቄው ተዳፍኖ እንዲቀር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን እነዚህ ወገኖች ይገልጻሉ፡፡

ከመጋቢት 23 ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በሁሉም ዞኖች ሲካሄድ በሰነበተው የብአዴን የህዋስ ግምገማ ፣ ሁለት አላማዎችን ለማሳካት መታቀዱን የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ አንደኛው፣ የአማራ መብት አልተጠበቀም፣ አማራ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገባውን ቦታ አላገኘም፣ የወልቃይት ጠገዴ፣ የሱዳን መሬትና ሌሎችም ተያያዝ ጥያቄ ያነሱ የድርጅቱን አባላት፣ በጠባነትና በተቃዋሚ አጀንዳ አራማጅነት በመክሰስ ነጥሎ ለመምታ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ የወልቃይት ጠገዴን ጥያቄ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የግል አጀንዳ በተለይም ከትግራይ ክልል መሪ ከአቶ አባይ ወልዱ ጋር ባላቸው ቅራኔ የተነሳ የተፈጠረ ነው በሚል፣ጥያቄዉን ግልሰባዊ ይዘት በመስጠት፣ ህዝባዊነቱን መንጠቅ የሚል ነው፡፡ በዚህም መሰረት፣ በግምገማው ወቅት፣ የህዝብ ጥያቄዎች ናቸው በሚል የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያነሱ በነበሩ የብአዴን አባላት ላይ በየመድረኩ የማሸማቀቅና የማስፈራራት ስራ በመስራት አንገታቸውን እንዲደፉ ተደርጎአል፡፡ በእነዚህ አባላት ላይ በሂደት እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችልም ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡

የቤት ለቤት ፍተሻ የመርካቶ ነጋዴዎችን አበሳጭቶአል

መጋቢት ፳፱( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በፖሊስ ሀይል እየታገዘ መደብሮቻችንን መፈተሽ መጀመሩ ህገወጥ እርምጃ ነው በሚል የመርካቶ ነጋዴዎችተቃውመዋል።

አንዳንድ ነጋዴዎች ለአዲስ አበባው ሪፖርተራችን እንደነገሩት ፖሊሶች በድንገት ሱቆቻችንን በመውረር ፍተሻ እናደርጋለን በሚል ለእያንዳንዱ እቃ በህጋዊ መንገድ የገባበትን ማስረጃ ካላቀረባችሁ ብለው እንደሚያዋክቡ፣
አንዳንዶች ማስረጃዎችን እስከሚያሰባስቡ እድል እንኩዋን ሳይሰጡዋቸው እቃዎቻቸውን ኮንትሮባንድ ናቸው በሚል ጭነው እየወሰዱ መሆኑ አሳዛኝ ነው ሲሉ በምሬት ገልጸዋል።
ነጋዴዎቹ አያይዘውም በተለይ ሞባይሎች፣ ፍሪጆች፣ ቴሌቪዥኖችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መንግስት በላካቸው ሀይሎች እየተዘረፉ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ በበኩሉ ኮንትሮባድን ለመቆጣጠር በመርካቶ አካባቢ በተመረጡ 7 ሱቆች ላይ ሰሞኑን ድንገተኛ ፍተሻ በማካሄድ ግምታቸው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሆነ የኤሌክትሮኒክስ የኮንትሮባንድ እቃዎች ይዣለሁ ብሎአል።
ባለፉት ወራት በተመሳሳይ ሁኔታ በ29 ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱንና በድርጊቱ የተጠረጠሩ ነጋዴዎችን እንደሚከስ አስታውቆአል። በዚህ ምክንያት በመርካቶ በተለይ አንዋር መስጊድ አካባቢ በርካታ ሱቆች አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ለመገንዘብ ተችሎአል።

በአበረታች መድሃኒት ምክንያት የኢትዮጵያ አትሌቶችና አትሌቲክስ ማኅበር ቅጣት ይጠብቃቸዋል

መጋቢት ፳፱( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ ተደርጎ የማያውቅ ድርጊቶች በቅርቡ ከዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማኅበርና ከመገናኛ ብዙሃን በኩል መደመጥ ተጀምርዋል። ውጤታማው የኢትዮጵያ የመሃከለኛና የረዥም ሩጫ ተወዳዳሪዎች አበረታች መድሃኒት መጠቀማቸውን የፀረ አደንዛዥ እጽ ተቆጣጣሪ ድርጅት በምህጻረ ቃሉ ዋዳ /WADA/ አስታውቋል።

ዓለምአቀፉ አትሌቲክ ማኅበር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ማኅበር የሯጮችን የደም ምርመራ ናሙና ውጤት ካላቀረበ በኢትዮጵያ ላይ ቅጣት እንደሚጥል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ማኅበር የሕክምና ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አያሌው ጥላሁን እንዳሉት ”ከ150 አስከ 200 በሚሆኑ ሯጮች ላይ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ምርመራ እንደሚጀምር ገልጸዋል።
ዶክተር አያሌው አክለውም ”እኛ ምርመራውን ካላደረግን በቅርቡ ከማንኛውም ውድድሮች የሚያግድ ቅጣት እንደሚጣልብን ዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማኅበር አሳውቆናል” በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት ተናግረዋል።
የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማኅበር ፕሬዝዳንት ሰር ሰባስቲያን ኮባሳለፍነው ወር ላይ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከዋነኞቹ ተጠርጣሪዎቹ አምስቱ አገራት ሩሲያ፣ ኬንያ ፣ ሞሮኮ፣ ቤላሩስና ዩክሬን ተርታ መመደቧን አሳውቀዋል።
ኢትዮጵያና ኬንያ እያንዳንዳቸው ሶስት ሯጮች ላይ እገዳ መጣላቸውን አስታውቀዋል። ዘጠኝ የኢትዮጵያ ሯጮች አበረታች መድሃኒት ሳይጠቀሙ እንዳልቀሩ ጥርጣሬ መኖሩንና ማጣራቱንም እንደሚቀጥል ማኅበሩ አስታውቋል።
የአበረታች መድሃኒት ቁጥጥሯ ደካማ የተባለችው ሩሲያ ከማንኛውም ውድድሮች የታገደች ሲሆን ኬኒያና ኢትዮጵያም አስቀድመው ካላሳወቁ እገዳውን ሊጥል እንደሚችል ዓለምአቀፉ አትሌቲክ ማኅበር ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አሾሸትድ ፕሬስ ዘግቧል።

በዱባይ የታሰሩት ኢትዮጵያዊያን ሥጋ ላኪዎችን እስካሁን አልተለቀቁም

መጋቢት ፳፱( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ በዱባይ በተካሄደው ዓለምአቀፍ የምግብ ኤግዚብሽን ላይ ለመካፈል በተጓዙበት የተበላሸ ሥጋን አቅርበዋል በሚል ውንጀላ በተባበሩት አረብ ኤሜሬት ፓሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት የስድስቱን ኢትዮጵያዊያን ሥጋ ላኪዎችን ለማስለቀቅ እንዳልተቻለ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤትና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እስረኞቹን ማስፈታት እንዳልቻሉ የተገለፀ ሲሆን የሥጋ ላኪዎች ማኅበር በበኩሉ ለተደጋጋሚ ጊዜያት ተማጽኖውን ቢያቀርብም ችግሩ ከአቅም በላይ መሆኑን አስረድተዋል።
ከአንድ ወር በላይ ሳይፈረድባቸው በእስር የሚማቅቁትን ዜጎች ማስፈታት የተሳናቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለዱባይ አንባሰደር ደብዳቤ መፃፋቸው ታውቋል።
ከወራት በላይ ካለ ፍርድ በእስር የተንገላቱት ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ሲታይ የኢትዮጵያ ኤንባሲና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ለዜጎች ከለላ የመስጠት አቅማቸው መዳከሙን ያመላክታል ሲሉ ታዛቢዎች ይገልጻሉ።