Monday, November 30, 2015

በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ነው

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት የአዲስ አበባን አስተዳደር ለማስፋት ያዘጋጀው አዲሱ የመሬት ካርታ ወይም ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንደሚደረግ የመንግስት ባለስልጣናት የተለያዩ መግለጫዎችን መስጠታቸውን ተከትሎ፣ የክልሉ ተማሪዎች ተቃውሞአቸውን እየቀጠሉ ሲሆን፣ በአምቦ፣ ኤሉባቦር፣ በምእራብ ወለጋና በሌሎችም የተካሄዱት ተቃውሞዎች ወደ ሃሮማያ (አለማያ)ዩኒቨርስቲ ተዛምቶ፣ በተማሪዎችና በፖሊስ መካከል በተነሳው ግጭት፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል።

ተማሪዎቹ ተቃውሞአቸውን በሰላም በማሰማት ላይ እያሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ዩኒቨርስቲው ግቢ በመግባት ድብደባ በመጀመራቸው ከ30 ያላነሱ ተማሪዎች ተጎድተው ወደ ህክምና መወሰዳቸውን የአይን ምስክሮች ገልጸዋል። እስካሁን የሞቱ ተማሪዎችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ ባንችልም፣ የተወሱ ተማሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። አንድ የፌደራል ፖሊስም በድንጋይ መመታቱንና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ተቃውሞ መነሳቱን ተከትሎ የተወሰኑ ተማሪዎች ግቢው በመልቀቅ ወደ ሃረርና ድሬዳዋ ሄደዋል።
በሌላ በኩል ዬዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሳ ከዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ ከኦህዴድ አባላትና ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ፣ ተማሪዎች ለተቃውሞ ሰልፍ ሲወጡ መወሰድ ስለሚኖርበት እርምጃ ግልጽ የሆነ መመሪያና እቅድ ባለመተላለፉ ፣ መቸገራቸውን ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። የስብሰባው ተሳታፊ ነበሩ የኢሳት ምንጮች በድብቅ ቀርጸው በላኩት ድምጽ፣ የተለያዩ ተወካዮች፣ ፕ/ሩ ተቃውሞ እንደሚነሳ እያወቁ መረጃ አስቀድመው ባለማሳወቃቸው ወቀሳ አቅርበዋል። ይሁን እንጅ ፕ/ር ጨመዳ፣ ተቃውሞ መነሳቱን የሰሙት እሁድ ሌሊት መብራት ጠፍቶ በነበረበት ወቅት መሆኑን፣ ዛሬ ሁኔታው መባባሱን ገልጸዋል። ተቃውሞዎች ሲነሱ ፣ የፖለቲካ ስራ በመስራት እናሳምናለን ቢባልም፣ ተማሪዎች አናምንም ካሉ ስለሚወሰደው ቀጣይ እርምጃ ግልጽ የሆነ እቅድ ባለመኖሩ፣ ግራ መጋባታቸውን ተናግረዋል መንግስት የአዲስ አበባን አዲሱን ካርታ ወደ ተግባር ከመቀየር ወደ ሁዋላ እንደማይል አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን ተናግረዋል።

በሃረሪ ፖሊስና መከላከያ መካከል በተፈጠረው ግጭት ሃረር ሰላም አጥታ ሰነበተች

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከተማዋ ውጥረት ነግሶ መሰንበቱን የገለጸው ወኪላችን፣ መንስኤውም አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል ተደብድቦና በጥይት ተመትቶ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን ተከትሎ ነው።

ውጥረቱን ተከትሎ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ትራፊክ ዋና አዛዥ ኮማንደር አብዲ ኢብራሂም የተሰወሩ ሲሆን፣ በመከላከያ ሰራዊት አባላት በጥብቅ እየተፈለጉ ነው። ጉዳዩን ለማጣራት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር በከተማዋ የተገኙ ሲሆን፣ የክልሉ መንግስት መከላከያ ፈጸመብኝ ያለውን 18 ክሶች ሲያቀርብ መከላከያ በበኩሉ የክልሉ ፖሊስ ፈጸመብኝ ያለውን 12 ክሶች አቅርቧል።
ሁለቱ ባለስልጣናት የክልሉን መንግስት ጥፋተኛ ነው ብለው የደመደሙ ሲሆን፣ በዚህም የተነሳ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱል ፈታህ አብዱልቃድር ከስልጣናቸው እንዲነሱና ኮማንደር አብዲ ደግሞ ከስልጣናቸውና ከፖሊስ አባልነትም ጭምር እንዲባረሩ ከመደረጋቸውም በላይ ለወደፊቱም በየትኛውም የመንግስት ስራ እንዳይቀጠሩ ተወስኖባቸዋል።
መከላከያም አስፈላጊውን የሰው ሃይል በማሰማራት ኮማንደር አብዲን እንዲይዝ ትእዛዝ ተላልፎለታል። ጉዳት የደረሰበት መከላከያ ሰራዊት አባል በምስራቅ እዝ የመጀመሪያ ህክምና ከተደረገለት በሁዋላ ፣ ለከፍተኛ ህክምና ጦር ሃይሎች ተልኳል።
ክልሉ በተባረሩት ፖሊስ ኮሚሽነር ቦታ አቶ ነስሩ አሊ ተሹመዋል። በኮማንደር አብዲ ኢብራሂም ቦታ ደግሞ አቶ አብዱል ፈታህ ተሹመዋል።
ከሃረር ዜና ሳንወጣ፣ የመብራትና እና ውሃ ችግር የከተማውን ህዝብ አስመርሯል። የከተማው ነገዴዎች መንግስት ከፍተኛ ግብር እንደጣለባቸው፣ ይሁን እንጅ መብራት በወጉ እንኳ ባለማግኘታቸው ስራቸውን ለመስራት አለመቻላቸውን ገልጸዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች ህዝቡ ፊርማ አሰባብሶ ቢያስገባም መልስ አላገኘም።

በሰሜን ወሎ ጠረፋማ ቀበሌዎች የቁም እንስሳት እየሞቱ መሆኑ ተነገረ፡፡

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፋር አጎራባች በሆኑ 15 ቀበሌዎች የድረቁ ሁኔታ እየተባባሰ በመምጣቱ ከ500 በላይ የቁም እንስሳት መሞታቸውን የሐብሩ ወረዳ የግብርና ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡

ዝናቡ ለአንድ ወር በመዘግየቱ በሃምሌ ወር መጨረሻ መዝነቡ የሰብሉን እድገት ማስተጓጎሉን የሚናገሩት ባለሙያ፣ በወረዳው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው የከብት መኖ እጥረት ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች አሁንም ችግሩ ተባብሶ በመቀጠሉ በነዋሪው ላይ ከፍተኛ ስጋት ማሳደሩን ተናግረዋል፡፡
ባለሙያው አክለውም አሁን ባለው ድርቅ ሁኔታ 500 የቁም ከብቶች መሞታቸውን ቢናገሩም ነዋሪዎች ከዚህ በላይ እየሞተባቸው እንደሆነ መግለጻቸውን ተናግረዋል፡፡በተለይ በአሁኑ ወቅት ድርቁ ጉዳት እያደረሰ ያለው በጥጃዎችና ክበድ ላሞች ላይ የማስወረድና የሞት አደጋ በየጊዜው መከሰቱን ተናግረው፤ ይህን ተከትሎ የሚከሰቱ ተዛማች በሽታዎችም ለቁም እንስሳቱ ሞት መፋጠን በምክንያትነት እንደሚቆጠሩ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር በከፋ ሁኔታ ተባባሰ።

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ ባል ድፍን አዲስ አበባ ጭለማ ውጧታል። ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ የሃይል መቆራረጡ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን የመንግስት ሹማምንት አንዴ ችግሩ የመልካም አስተዳደር ብልሽት ውጤት ነው፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የመስመር እርጅና ነው እያሉ ፣ እርስበርሱ የተምታታ መግለጫ ከመስጠት ባለፈ ሁነኛ መፍትሄ ሳያበጁለት ቀርተዋል።

ችግሩ በተባባሰበት ባለፉት ሁለት ቀናት ዳቦ ቤቶች፣ የውበት ሳሎኖች፣ አነስተኛ ምግብ ቤቶች፣ካፌዎች፣ ክሊኒኮችና ጤና ጣቢያዎች፣ የባንክ ኤ ቲ ኤም ማሸኖች ከስራ ውጪ ለመሆን ተገደዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ህዝቡ በመብራት መቆራረጥ እየተሰቃየ ባለበት፣ ከችግሩጋር ተያይዞ ምርትና ምርታማነት ባሽቆለቆለበት በዚህ ወቅት መብራት ለጅቡቲ ፣ለኬንያ መሸጡ አይዘነጋም። መንግስት የመብራት ስርጭቱን በፈረቃ ለማድረግ ማቀዱን አስታውቋል። የመብራት መቋረጥ የተከሰተው በጣና በለስና በግልገል ጊቤ አንድ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ላይ የቴክኒክ ችግር በመፈጠሩ ነው ብሎአል።

223 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከማላዊ ወደ አገራቸው ተመለሱ

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ ማላዊ ላይ ተይዘው በእስር ቤት ውስጥ ሲንገላቱ የነበሩትን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በሰጡት 9 ሺ የአሜሪካ ዶላር ቁጥራቸው 223 የሚሆኑትን በቻርተር አውሮፕላን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።

እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከመስከረም ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ድርጅቱ ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ያደረገ ሲሆን እስካሁን ድረስ አጠቃላይ ድምራቸው 387 ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን መመለሱን ድርጅቱ አስታውቋል።
በማላዊ በተለያዩ እስርቤቶች ውስጥ የነበሩት ስደተኞች ከ2 እስከ 9 ወራት በተጨናነቀ ሁኔታ ታስረው የቆዩና የተለያዩ በደልና ሰቆቃዎች ሲፈጸምባቸው የነበሩ ሲሆን ከእስራቱ በተጨማሪም በሕገወጥ መንገድ አገር በመግባት ወንጀል ተከሰው በፍርድ ቤት 35 የአሜሪካ ዶላር መቀጮ ተበይኖባቸው እንዲከፍሉ ተደርገዋል።
ድርጅቱ ከአሜሪካም ወደ አገራቸው ለመመለስ ፍቃደኛ የሆኑ 164 ኢትዮጵያዊያንን መመለሱንና አሁንም ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ስራ ፍለጋ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት መፍለስ መቀጠላቸውንና አብዛሃኞቹ በታንዛኒያ፣ሞዛምቢክ፣ማላዊ እንግልትና ሰቆቃ እንደሚፈጸምባቸው ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOMን ጠቅሶ ኒውስ ሃወር ዘግቧል።

በሀረማያ ዩኒቨርስቲ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን የተቃወሙ ስልፈኞች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ።

Minilik Salsawi – በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዳይሆን የተቃውሞ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ከነበሩ የኦሮሚያ ተወላጅ ተማሪዎች መካከል የፊዴራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ወደ ዪኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በመግባት ሶስት ተማሪዎችን መግደላቸውንና ብዙዎችን ማቁሰላቸው እየተሰማ ነው ።




Friday, November 27, 2015

አንዳርጋቸው ጽጌና እስክንድር ነጋ ለምስክርነት ተጠርተዋል

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት እየታየ የሚገኙት አምስት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አቅርበው አሰምተዋል፡፡ በዚህ መዝገብ የተካተቱት ተከሳሾችም ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ዮናታን ወልዴ፣ ባህሩ ደጉ፣ ሰለሞን ግርማ እና ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው፡፡
ተከሳሾቹ ከሰኞ ህዳር 13/2008 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ለአራት ቀናት ምስክሮቻቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ ዘላለም ወርቃገኘሁ 11 ምስክሮች፣ ዮናታን ወልዴ 5፣ ሰለሞን ግርማ 3፣ እና ባህሩ ደጉ እና ተስፋዬ ተፈሪ እያንዳንዳቸው 8 ምስክሮችን ጠርተዋል፡፡ ከእነዚህ መካከልም በአንደኛ ተከሳሽ ለምስክርነት የተጠሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲቀርቡ አለመደረጋቸው ታውቋል፤ በተጨማሪም በእስር ቃሊቲ የሚገኙትና ለምስክርነት የተጠሩት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ እና ዳንኤል ሺበሽን ማረሚያ ቤቱ ለተከታታይ ቀናት ከፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ቢተላለፍለትም ሳያቀርባቸው ቀርቷል፡፡
በዋናነት ተከሳሾች በማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ በነበሩበት ወቅት የደረሰባቸውን አስከፊ የምርመራ ሁኔታና በዚሁ ምክንያት ተገድደው ስለሰጡት ቃል የሚመሰክሩ ምስክሮችን አሰምተዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ በምርመራ ወቅት አብረዋቸው ታስረው የነበሩና በኋላ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆነው ቀርበው የመሰከሩ ግለሰቦች እንዴት ተገድደው በሀሰት እንደመሰከሩባቸው ያስረዱልናል ያሏቸውን ምስክሮች አስደምጠዋል፡፡
ተከሳሾች የተከሳሽነት መከላከያ ቃላቸውን ለፍርድ ቤቱ የሰጡ ሲሆን፣ በተለይ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ህዳር 16/2008 ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ በሰጠው ቃል፣ የቀረበበት ክስ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው (politically motivated) እንደሆነና በምርመራ ወቅትም በፖሊስና ደህንነት ከተከሰሰበት ጋር በማይገናኝ መልኩ ‹‹ምርጫ 2007ን ለማደናቀፍ ቡድን አደራጅተሃል›› በሚል ሲመረመር እንደነበር አመልክቷል፡፡
ዘላለም በሰጠው ቃል የጸረ-ሽብር ህጉ አሸባሪዎችን ለመከላከልና ለመቅጣት ሳይሆን የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ ዜጎችን እና ጋዜጠኞችን ለማጥቃት እየዋለ እንደሆነም አስረድቷል፡፡ ‹‹በእኔ እምነት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውና ግንኙነት አለህ በሚል የተከሰስኩበት ድርጅት አሸባሪ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ሆኖም ግን እንደ እኔ አይነቶችን ለማጥቃት መጠቀሚያ እንዲሆን ሊፈረጅ ችሏል›› ሲል ቃሉን ሰጥቷል፡፡
ለተከታታይ 41 ቀናት ቀዝቃዛና ጨለማ ክፍል በማዕከላዊ እንዳሳለፈና ለአንድ ወር ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኝ እንደተደረገ የተናገረው ዘላለም፣ ‹‹ለለውጥ የሚታገሉ ወጣቶች ላይ ተጽዕኖ ላለማሳደር የደረሰብኝን በደል ሁሉ እዚህ መዘርዘር አልሻም›› ሲል ገልጹዋል፡፡ በተመሳሳይ ሌሎችም ተከሳሾች በሰጡት ቃል በማዕከላዊ አስከፊ ምርመራ እንደተደረገባቸው አስረድተዋል፡፡
በዚህ መዝገብ የተካተቱት አቶ ባህሩ ደጉ እስካሁን ምስክሮቻቸውን አቅርበው ያላሰሙ ሲሆን፣ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ እና 6ኛ ተከሳሽ ዮናታን ወልዴ ደግሞ ቀሪ ምስክሮቻቸውን የሚያሰሙ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ዛሬ ህዳር 17/2008 ዓ.ም ‹‹ዳኞች አልተሟሉም›› በሚል ቀሪ ምስክሮችን ማሰማት ባለመቻላቸው ለህዳር 24/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡
በዚሁ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የሆኑት አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ እና ዳንኤል ሺበሽ እንዲሁም መምህር አብርሃም ሰለሞን በዚሁ ችሎት ነጻ መሆናቸው ቢበየንም በአቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ተጠይቆባቸው ጉዳያቸውን በእስር ላይ ሆነው እየተከታተሉ እንዳሉ ይታወቃል፡፡

ወያኔ ሰራሽ የርስበርስ ግጭት ደግሶችን እናምክን!!!


የወያኔ ስርዓት ኢትዮጵያ የተዋቀረችው በህዝብ ታሪካዊ አብሮነትና ተዛምዶ ላይ ሳይሆን የብሔር ብሔረሰብ ልዩነቶችን በማጥበቅና ልዩነትንም የርስበርስ ጥርጣሬና ግጭት ምንጭ እንዲሆን በማለም ነው። ልዩነት የግጭትና የጠብ ምንጭ እንዲሆን ተደርጎ ነው የተዋቀረውና ብፖለቲካ ደረጃ የተገፋው። አንዱ ብሔረሰብ ሌላው ብሔረሰብ ክልል ውስጥ ሲሆን ባዕድነት እንዲሰማውና እንዲሰጋ አንዱ አንዱን በጥርጣሬ እንዲመለከተው ተደርጎ ነው ሀያ አራት አመት ሙሉ የተገፋውና እየተገፋ ያለው።
ይህም ሆኖ በዘመነ ወያኔ በየቦታው የተከሰቱ የብሔር ሌብሔርሰብ ግጭቶች በሙሉ የተቀሰቀሱት በራሱ በመንግስት ባለስልጣኖች እንጂ መቼም ህዝብ ለሕዝብ ሆኖ አያውቅም። በተለያዩ የደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች አማሮችን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ለማባረር የተወሰዱት ርምጃዎች ራሳቸው ሰለባዎቹ እንደሚናገሩት ለስቃይ የዳረጋቸው ነዋሪው ሕዝብ ሳይሆን ባለስልጣናቱ መሆናቸውን በግልጽ ሲናገሩ ሰምተናል።

ከአንድ ሺ ያላነሱ የአዲስ አበባ ፖሊሶች የሥራ መልቀቂያ አስገብተው በመጠባባቅ ላይ ናቸው

የፖሊስ ምንጮች እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ስራቸውን ለመልቀቅ ማመልከቻ ያስገቡ ፖሊሶች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።7 አመት ያላገለገሉ ፖሊሶች ያገለገሉበት ዘመን ታስቦ ገንዘብ ከፍለው የሚሰናበቱ ሲሆን፣ ይህንን ክፈተት በመጠቀም ብዙዎች ስራውን እየለቀቁ ሄደዋል። ከፖሊስ የሰው ሃይል ክፍል የደረሰን አስተማማኝ መረጃ እንደሚያሳያው መልቀቂያ አስገብተው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ፖሊሶች 1 ሺ ይደርሳሉ። ብዙዎች ለመልቀቃቸው የሚሰጡት ምክንያት ከስራ ጫና፣ ከአስተዳደር፣ ዘረኝነትና ከደሞዝ ጋር የተያያዘ ነው።

ለቃቂ ፖሊሶች ተቃዋሚዎችን ሊቀላቀሉ ይችላሉ የሚል ስጋት የገባው መንግስት ሰሞኑን ለአመታት ላገለገሉ ፖሊሶች የአግልግሎት ሰርተፊኬት በመስጠት ፍልሰቱን ለማስቆም እየተሯሯጠ ነው።
ሰሞኑን በተሰጠው የአግልገሎት የምስክር ወረቀት አንዳንድ ፖሊሶች ከ1 እስከ አራት ወራት ያሉ ደሞዛቸውን በስጦታ መልክ ተቀብለዋል። ይሁን እንጅ ሽልማቱ የመልቀቂያ ጥያቄ የሚያቀርቡ ፖሊሶችን ቁጥር ሊቀንሰው አልቻለም።
አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ፖሊስ ፣እሱ በሚሰራበት ወረዳ በርካታ ፖሊሶች በመልቀቃቸው የስራ ጫና መፈጠሩንና በአለቆች ላይ ግምገማ መጀመሩን ተናግሯል። አማራጭ ቢያገኝ ስራው ላይ የሚቆይ ሰው አይገኝም ሲልም በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ገልጿል።

የአዲስ አበባ የተለያዩ ወረዳዎች ተወካዮች የተባሉ መንግስት አይሰማንም አሉ

ኢሳት ዜና :-ሁለተኛውን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አስመልከቶ የህዝብ ተወካዮች ናቸው ከተባሉ ሰዎች ጋር የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በውይይቱ ተወካዮች በየአካባቢው የሚታዩ ችግሮችን ተናግረዋል። የህዝብ ተወካዮቹ ” ብንናገርም የሚሰማን መንግስት” የለንም ብለዋል።

ምንም እንኳ ብዙዎቹ ተወካዮች ለገዢው ፓርቲ ካላቸው ቀረቤታ እና በድርጅት አባልነት ተመርጠው የመጡ ቢሆንም ፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ በነበረው ስብሰባ፣ አንዳንድ ተወካዮች ወረዳቸው የገጠመውን ችግር በድፍረት አቅርበዋል።
አንድ የወረዳ 14 ተወካይ ፍትህ የሚጥስ አገዛዝ መኖሩንና ፣ የህዝቡን አቤቱታ የሚሰማ መሪ መጣታቱን ገልጸው፣ ወጣቱ መንግስትን እየጠላ ቢመጣ አይፈረድበትም ብለዋል
የወረዳ 3 ተወካይ በበኩላቸው በወረዳቸው የሚታዬው የውሃ ችግር አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው፣ “ህዝብ ሲቆጣ ውሃው ይለቀቃል፣ ህዝብ ዝም ሲል መልሶ ይጠፋል” በማለት ችግራቸውን አሰምተዋል።
የመሬትና ካርታ፣ ህገወጥ ግንባታ በሚል የሚፈርሱ ቤቶች ጉዳይ እና የጸጥታ ጉዳይ የህዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች መሆናቸውን ስብሰባውን የተከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግስታት የረድኤት ክፍል በኢትዮጵያ የሚታየውን ድርቅ የተመለከተ ፎቶግራፍ ይፋ አደረገ

ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ድርቁ እያስከተለ ያለውን ጉዳትና የደቀነውን ፈተና ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመዟዟር በፎቶ ግራፍ በማስደገፍ አቅርቧል።

በሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ የሚኖሩት አርሶአደርን፣ የስንዴ ማሳቸው በዝናብ እጥረት የተነሳ ደርቆባቸው ሃሳብ ገብቷቸው ይታያሉ
በጊዳን፣ ዳውንት፣ አበርጌሌ ወረዳዎች የጤፍ፣ የስንዴ፣ የዳጉሳና የማሽላ ማሳዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት ደርቀው መሬቱም ተሰነጣጥቆ ይታያል።

105 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ታንዛኒያ ውስጥ ተያዙ

 ኢሳት ዜና :-በሕገወጥ መንገድ ወደ ታንዛኒያ ግዛት ገብተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዋና ከተማዋ ዳሬሰላም ውስጥ መያዛቸውን የከተማዋ የፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ሱሌይማን ኮቫ ገልጸዋል።

አዛዡ ቁጥራቸው 105 የሚሆኑ ያሉዋቸውን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዳሬሰላም በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው መያቻውን ገልጸዋል። ስደተኞቹን ጨምሮ ሕገወጥ የሰው ዝውውር ሥራ ይሰራል የተባለው የ25 ዓመቱ ሩዋንዳዊ ዜጋም ተይዟል።
በስደተኞች ላይ የሚደረገው ምርመራ ሲጠናቀቅ፣ ስደተኞቹ በሕጋዊ መንገድ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ሲሉ አዛዡ አክለዋል።

ኢትዮጵያዊቷ ሯጭ ገንዘቤ ዲባባ በረዥምና መሃከለኛ ርቀት ሩጫ የዓመቱ ኮከብ ተብላ ተመረጠች

ኢሳት ዜና :-ዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማኅበር እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር የ2015 ዓ.ም የዓመቱ ኮከብ ሯጮች በማለት ኢትዮጵያዊቷ ትንሿ ልዕልት ገንዘቤ ዲባባ እና አሜሪካዊው አሽተን ኤተንን መርጧል።

የ24 ዓመቷ ወጣት የበቆጂ ፍሬ ገንዘቤ ዲባባ በዓመቱ ውስጥ በ1 ሽህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር በፈረንሳይ ሞናኮ እርቀቱን በ3 ደቂቃ 50.07 ሰከንድ ክብረወሰን ከመስበሯም በተጨማሪ በቻይና ቤጅንግ የአለም አትሌቲክስ ውድድር ላይ በ1ሽህ 500 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤትና በ5 ሽህ ሜትር ርቀት ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የነሃስ ሜዳሊያ ባለቤት መሆኗ አይዘነጋም።የ27 ዓመቱ ወጣት አሜሪካዊው አሽተን ኤተን በበኩሉ የዓለም ዴክታትሎንና ሄፕታትሎን ክብረወሰን ባለቤት ነው።
ዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማኅበር እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ለአትሌቶቹ በሞናኮ የሽልማት ስነስርዓት አላደረገም የዚህም ዋናው ምክንያት ማኅበሩ በሙስና ቅሌት በመዘፈቁ እንደሆነ ተገልጿል።

Hailemariam Desalegn said redrawing the borders between Sudan and Ethiopia will begin next month according to a previous agreement with Sudan’s President Omer al-Bashir.

Hailemariam Desalegn said redrawing the borders between Sudan and Ethiopia will begin next month according to a previous agreement with Sudan’s President Omer al-Bashir.


Sudan’s state minister for foreign affairs Kamal al-Din Ismail told the official news agency (SUNA) that Desalegn told 2nd vice-president Hassabo Mohamed Abdel-Rahman on Monday that the demarcation will be resumed next month.

According to Ismail, Abdel-Rahman, who is currently visiting Addis Ababa, discussed with Desalegn the border and economic issues between the two countries.

‎በጎንደር‬ ከተማ ቀበሌ 17 ሁለት ሰላማዊ ወጣቶች በህወሃት ልዩ ኃይል ጦር በጥይ ተደብድበው ተገደሉ፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
‪#‎በጎንደር‬ ከተማ ቀበሌ 17 ሁለት ሰላማዊ ወጣቶች በህወሃት ልዩ ኃይል ጦር በጥይ ተደብድበው ተገደሉ፡፡
‪#‎አንድ‬ የጠገዴ ታጣቂ ሁለት የህወሓት ፖሊሶችን ገድሎ በረሃ መውጣቱ ተዘገበ፡፡




በጎንደር ከተማ ቀበሌ 17 ሁለት ሰላማዊ ወጣቶች በህወሃት ልዩ ኃይል ጦር በጥይ ተደብድበው ተገደሉ፡፡
ህዳር12 2008 ዓ.ም በጣት የሚቆጠሩ የቀበሌ 17 ወጣቶች መጥምቁ ዮሃንስ አካባቢ በቀሃ ወንዝ ዳር አቅራቢያ ተሰባስበው ህዳር ሚካኤልን በጋራ በማክበር ላይ እያሉ የህወሓት ልዩ ኃይል አባላት ደርሰው ወጣቶቹን ለመበተን ድንገት በከፈቱት ተኩስ ነው ሁለቱ ወጣቶች በግፍ የተገደሉት፡፡
በጥይት ከተደበደቡት ሁለቱ ወጣቶች መካከል አንደኛው ቶሎ ነብሱ ባለመውጣቱ ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ለህክምና ተወስዶ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ህይወቱ ሲያልፍ የአካባቢው ነዋሪዎች ወጥተው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል አጥር ዙሪያ በጥበቃ ላይ በነበሩት ጥቂት የህወሓት ልዩ ኃይል ጦር አባላት ላይ ድብደባ በመፈፀም ቁጣቸውን የገለፁ ሲሆን የልዩ ሃይል ጦር አባላቱ ሮጠው ለጥቂት ከሞት አምልጠዋል፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግቢና አካባቢው ሌሊቱን ከፍተኛ ግርግር ተነስቶ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንዳደረ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
አንድ የጠገዴ ታጣቂ ሁለት የህወሓት ፖሊሶችን ገድሎ በረሃ መውጣቱ ተዘገበ፡፡
ህዳር 14 2008 ዓ.ም ክምሽቱ 2፡30 ላይ ሁለት ፖሊሶችን ተኩሶ በመግደል እንደታጠቀ አምልጦ ጫካ የገባው ታጣቂ ስሙ ሀጎስ ይሰኛል፡፡ 
በታጣቂው ሀጎስ እርምጃ የተወሰደባቸው የአገዛዙ ፖሊሶች ደግሞ ኮንስታብል አስቻልና ኮንስታብል አታለለ ይሰኛሉ፡፡

አንተም ደመቀ መኮንን! (ከአንተነህ መርዕድ)

ከአንተነህ መርዕድ
Demeke Mekonnen Hassen Deputy Prime Minister of Ethiopia
መጥኔ በሁለመናው ለተራብነው!!
ይድረስ ለማውቅህና ለማታውቀኝ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
የኢትዮጵያ ህዝብ እስከአሁን መሪዎቹን መርጦ አያውቅም። ሁሉም በጉልበት ትክሻው ላይ ተፈራርቀው ወጥተውበታል፤ እየተካኩም አሁን ላለበት ከዓለም የመጨረሻነትና የርሃብ ተምሳሌትነት አድርሰውታል፤ አድርሳችሁታል። ያለፈ ታሪክ እየቆፈርን ማን ምን ሠራ እያሉ ለመዘባነን በአሁኑ ወቅት ህሊና ላለው አንገብጋቢ ጥያቄ አይመስለኝም። በእጃችን ላይ ያለውን ዐይኑን አፍጥጦ የመጣውንና የብዙ ሺዎችን ህይወት ለመቅጠፍ “ሀ’’ ብሎ የጀመረውን ርሃብ ለመግታት ደመኛ ጠላቶችም ቢሆኑ የሚተባበሩበት ወቅት ነውና። ከየትም ወገን ይምጣ ርሃብን ለፖለቲካ ፍጆታ የመጠቀምን ያህል ጭካኔ ከቶ የለም።

Thursday, November 26, 2015

የህንዱ ካራቱሪ ኩባንያ ንብረት ጨረታ ወጣበት

 ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጋምቤላ ብሔራዊ ክልል በኑኤር ዞን ጂካዎ እና ኢታንግ ወረዳ የሚገኘውን የህንዱ ካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ኃ/ተ/የግ/ማ ንብረት የሆነውን 100ሺህ ሄክታር የእርሻ መሬት ጨምሮ ሌሎች ንብረቶች ላይ የሐራጅ ጨረታ አውጥቷል።

ባንኩ ህዳር 7ቀን 2008 በመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ባወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ መሠረት ተጨራቾች እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ መጫረት እንደሚችሉ የገለጸ ሰሆን፣ በዚህ ጨረታ ለሽያጭ የቀረበው የካራቱሪ በሊዝ የተረከበው መሬት 100 ሺ ሔክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 7ሺ 645 ሄክታር መሬት የለማ መሆኑን ገልጾአል፡፡ ኩባንያው ከመንግስት ለእርሻ ኢንቨስትመንት ከተረከበው መሬት በተጨማሪም መጋዘን፣ የሠራተኞች መኝታ ቤቶችንና ተገጣጣሚ ቤቶችን ባንኩ እንደሚሸጥ አስታውቆአል፡፡ ባንኩ ያስቀመጠው የጨረታ መነሻ ዋጋ 55 ሚሊየን 886 ሺህ

የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ገቢ በ2008 ዓ.ም መጀመሪያው ሩብ ዓመት እንደአለፉት ዓመታት ሁሉ ማሽቆልቆል ታየበት፡፡

 ኢሳት ዜና :-ከሐምሌ 2007 እስከ ጥቅምት 30 /2008 ባሉት ጊዜያት ብቻ 222 ሚሊየን ዶላር ከወጭ ንግድ ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ማሳካት የተቻለው 177 ሚሊየን ዶላር ያህሉን ብቻ ነው፡፡

ሀገሪቱ ወደውጭ ከምትልካቸው የግብርና ምርቶች መካከል የቅባት እህሎች ጥራጥሬ፣ ቅመማቅመም፣ ቡና፣ ጫት የሚገኙበት ሲሆን በተለይ የቅባትና የጥራጥሬ እህሎት የዓለም ገበያ ዋጋ መውደቅ ጋር ተያይዞ ገቢው ሊያሽቆለቁል እንደቻለ ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ አመልክቶአል፡፡

ለብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል 200 ሚሊዮን ብር ተመደበ

 ኢሳት ዜና :-ህገመንግስቱ የጸደቀበት በተለምዶ የብሄር ብሄረሰቦች በአል ህዳር 29 ቀን በጋምቤላ ክልል የሚከበር ሲሆን ፣ ለበአሉ ድምቀት በጋምቤላ ስታዲየም ተገንብቷል። ከ5 ሺ በላይ እንግዶችን ለማስተናገድ የማሰልጠኛ ተቁዋማት የመማሪያ ክፍሎችን ጭምር ወደ ምኝታ ክፍሎች ለመቀየር ታስቦአል።

በፈዴሬሽን ም/ቤት በኩል በየአመቱ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚወጣበት ይህ በአል ፣ዘንድሮ ከ15 ሚሊየን በላይ ወገኖች በድርቅ ችግር ውስጥ በሚማቅቁበት ወቅት ይከበራል።

አንድ የደህንነት አባል ገንዘብ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተያዘ

 ኢሳት ዜና :-ሳሙኤል ጋዲሳ ገለታ የተባለው የደህንነት አባል ጥቅምት 03/2008 ዓ.ም ፣ በመኪና አከራይነት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙትን አቶ ተክሉ ቀጄላን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባል እንደሆንክ ደርሸብሃለሁ በማለት አስፈራርተው 30 ሺ ብር ጽዮን ሆቴል ውስጥ ሲቀበሉ፣ ግለሰቡ አስቀድመው ለፖሊስ አመልክተው ስለነበር፣ የደህንነት አባሉ ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል። ፖሊስ በገንዘቡ ላይ ማህተም በማሰራፉ የደህንነት አባሉ ድርጊቱን ሊክድ አልቻለም።

የደህንነት አባሉን መያዝ ተከትሎ የኦሮምያ ክልል መስተዳደር ባለስልጣናት ድርጊቱ ገጽታችንን ያበላሻል በሚል ፣ ባለፈው ሳምንት በፖሊስ ፕሮግራም ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት እንዳይቀርብ አስደርገዋል። የፖሊስ ምንጮች እንደሚሉት የደህንነት አባሉ በቁጥጥር ስር እንዲውል የጠቆሙ ሰዎች፣ በደህንነቶች እየተጠሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ምንም እንኳ የደህንነት ሰራተኛው አሁንም ድረስ ማእከላዊ ታስሮ ቢገኝም፣ክስ እንዳይመሰረትበት ለማድረግ ባለስልጣናት በመሯሯጥ ላይ ናቸው።

የአፍሪካ የሰላምና የደህንነት ጉባኤ በድርቅ የተጎዱ አገሮች እንዲረዱ ጠየቀ

 ኢሳት ዜና :-በደቡብ የአፍሪካ አገራት በቦትስዋና፣ ሌሶቶ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ፣ ደቡብ አፍሪካና ዝምባብዌ ከምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ሶማሊያን እንዲሁም በምዕራብ አፍሪካ አገራት የአየር መዛባቱ በሚፈጥረው ድርቅ ሳቢያ የምግብ እጥረትና የሰብዓዊ ቀውስና ግጭቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ምክር ቤቱ ጠቅሷል። ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እነዚህ አገራት አስከፊ ቀውስ ውስጥ ከመግባታቸው አስቀድሞ አፋጣኝ የሆነ የሰብዓዊ እርዳታውን መለገስ እንዳለበት በአጽኖት አሳስቧዋል።

በተጨማሪም የዓለም የምግብ ድርጅት FAO ድርቁን ተከትሎ የምግብ ዋጋ መናር እንደሚከሰት፣ በተለይ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በድርቁ ተጠቂ ከሆኑት አገራት ቀዳሚዋ በመሆኑዋ እርዳታ እንደሚያሻት ገልጿል።

“ረሃቡና ኢህአዴጋዊ እውነታዎች!”

ኤርሚያስ ለገሰህወሃት መራሹ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ረሃብ በተከሰተ ቁጥር የረሃቡን ዋነኛ ምንጭ “የአየር ንብረት መዛባት” በሚል ውጫዊ ምክንያት ማላከኩ የተለመደ ሆኗል። ለአብነት ያህል የዛሬ ዘጠኝ አመት በኢትዮጵያ ረሃብ በተነሳ ወቅት “የሰሞኑ የረሃብ ፖለቲካ” በሚል ረዕስ የውስጥ ድርጀት ሰነድ ተዘጋጅቶ ነበር ደራሲው ጓድ መለስ ዜናዊ ነበሩ። በማስከተልም የፓርቲው ከፍተኛ ካድሬዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት ውይይት እንዲያደርጉበት ተደረገ። በዚህ ሰነድ ገፅ 6 ላይ የረሃቡን ዋነኛ ምንጭ እንደሚከተለው

Wednesday, November 25, 2015

በኦሮምያ አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም ተቃውሞ ተነሳ

 ኢሳት ዜና :-አወዛጋቢው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም ከአመት በፊት አደባባይ የወጡ የኦሮምያ ክልል ወጣቶችና ተማሪዎች ህይወታቸው በመንግስት ታጣቂዎች ከተቀጠፈ በሁዋላ፣ ኢህአዴግ እቅዱን በድጋሜ ተግባራዊ ለማድረግ መንቀሳቀሱን ተከትሎ በአምቦ፣ በማንዲና በዙሪያ ከተሞችና ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።

በአዲስ አበባ ህዝቡ የመሬት ፖሊሲውን ሲቃወም የጸጥታ ጉዳይም አሳሳቢ እየሆነ መሆኑን ገለጸ

 ኢሳት ዜና :-መንግስት ሁለተኛውን የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ከህዝብ ጋር ለመወያየት የጠራው ስብሰባ ህዝቡ ብሶቱን አሰምቶ በተቃውሞና ባለመግባባት ተጠናቋል።

የካራ ቆሬ ነዋሪዎች በመጀመሪያ የተደረገላቸውን ጥሪ ባለመቀበል በስብሰባው ባለመገኘታቸው፣ በድጋሜ 50 ብር እንደሚሰጥ ከተገለጸ በሁዋላ በ አዳራሹ ተገኝተዋል። ይሁን እንጅ ውይይቱ በእቅዱ ላይ መሆኑ ቀርቶ ህዝቡ ብሶቱን ሲያሰማ ውሎአል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ አንድ የመንግስት ወኪል መገደሉን ተከትሎ 4 ሰዎች በተገኙበት እንዲገደሉ ተወሰነባቸው

 ኢሳት ዜና :-በፎገራ ወረዳ፣ ወረታ ከተማ በቁሃር ሚካኤል ቀበሌ ነዋሪ የሆነው መንግስቴ ቢምር የተባለ የአካባቢ ሹም የህብረተሰቡን መሳሪያ በማስፈታት ከኢህአዴግ ጋር ሲሰራ ነበር በሚል መገደሉን ተከትሎ፣ እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋሉት ገዳዮች በተገኙበት እንዲገደሉ መወሰኑን ምንጮች ገልጸዋል።

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ በአርሲ ዞኖች የተረጂዎች ቁጥር አሻቀበ

ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ አድማሱን እያሰፋ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብና ምስራቅ ሃረርጌ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ አፋጣኝ የምግብ ዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት 50 በመቶ በላይ ማሻቀቡን የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሃረን አልዪ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

እስካሁን ድረስ ከ549 ሽህ ተረጂዎች ተለይተው ዕርዳታ ሲሰጣቸው የቆየ ቢሆንም ድርቁ አሁንም ለውጥ ሳያሳይ በመቀጠሉ የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ብቻ ከ320 ሺሕ በላይ ተጨማሪ ተረጂዎች የመንግሥትን ዕርዳታ የሚሹ በመሆናቸው፣ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የተረጂዎች ቁጥር ከ900 ሺሕ በላይ ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል፡፡

በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ አደባባይ የወጣ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲሰማ ዋለ * ህዝቡ ጎማ እያቃጠለ ነበር

(ዘ-ሐበሻ) በምእራብ እና በመካከለኛው የኦሮሚያ ክልሎች ዛሬ ሙሉ ቀን ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ሲያሰማ መዋሉ ተዘገበ:: የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች እንደዘገቡት በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ በተደረገው ከፍተኛ ተቃውሞ ሕዝቡ በአደባባይ ጎማዎችን ጭምር በማቀጥል መሪር ተቃውሞውን አሰምቷል:: 

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፊታችን ማክሰኞ በአውሮፓ ፓርላማ ንግግር ያደርጋሉ ተባለ

(ዘ-ሐበሻ) የትጥቅ ትግሉን መንገድ መርጠው ታግዬ አታግላለው ብለው አስመራ የወረዱት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፊታችን ማክሰኞ ዲሴምበር 2 በአውሮፓ ፓርላማ ንግግር እንዲያደርጉ መጋበዛቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ::
ከአስመራ ወደ ብራሰልስ እንደበረሩ የሚነገርላቸው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለሕዝብ ክፍት በሆነው በዚሁ የአውሮፓ ፓርላማ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት በወ/ሮ አና ጎሜዝ ነው ተብሏል:: በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ መገኘት ለሚፈልጉ – የአውሮፓ ነዋሪዎች በምርጫ 97 ወቅት የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ለነበሩት ወ/ሮ አና ጎሜዝ ደብዳቤ
ፕሮግራሙ ለሕዝብ ክፍትና ነፃ በመሆኑ አስቀድማችሁ:-
  • ስማችሁን
  • የተወለዳችሁበትን ቀን/ ወር/ ዓ.ም
  • ዜግነታችሁን
  • እና የፓስፓርት ቁጥራችሁን በ Anamaria.gomes@europarl.europa.eu በመላክ መመዝገብ እንደሚቻል የደረሰን መረጃ ጠቁሟል::

ገሃዱ አሰቃቂ ረሃብ እና የማወናበጃው «የልማት ዕድገት» በኢትዮጵያ | ሞረሽ ወገኔ

በያዝነው ዓመት በአገራችን በኢትዮጵያ አስከፊ የርሃብ አደጋ እንደተስፋፋ ከተለያዩ የዜና አውታሮች ይደመጣል። በተቃራኒው ደግሞ የትግሬ-ወያኔ የሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ብዙሃን በአገዛዙ ጥረት ስለተገኘው የልማት ትሩፋት ይለፍፋሉ። በአንድ አገር በአንድ ጊዜ ሁለት እጅግ ተቃራኒ ሁኔታን የሚያንጸባርቁ ዜናዎች ሲደመጡ እውነቱን አንጥሮ ማሣዬት ተገቢ ነው። ስለሆነም በዚህ መግለጫ ዕውነቱ የትኛው እንደሆነ ብቻ ሣይሆን የመፍትሔ ኃሣቦችንም ለማመልከት ተሞክሯል።  በአገራችን በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ጊዜያት ከፍተኛ የርሃብ አደጋዎች ተከስተዋል። በዚሁ ሳቢያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን አልቀዋል፤ አሁንም እያለቁ ነው። ለአብነት ያህል በንጉሡ ዘመን በ1958ዓ.ም. እና በ1965-66 ዓ.ም. እንዲሁም በደርግ ጊዜ በ1977 ዓ.ም. የተከሰቱት የርሃብ አደጋዎች በአስከፊነታቸው እና በሕዝብ ጨራሽነታቸው የሚጠቀሱ ናቸው። በትግሬ-ወያኔ የአገዛዝ ዘመን ርሃብ አልፎ አልፎ የሚመጣ ሣይሆን በየዓመቱ ከ7 እስከ 25 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንን ለችጋር ማጋለጡ እና የሰው እጅ ተመልካች እንዳደረጋቸው ይታወቃል። ይህም ሆኖ እንደ ዘንድሮው እጅግ የከፋ አልነበረም። በመሆኑም በዚህ ዘመን ርሃብ በኢትዮጵያውያን ላይ ቤቱን ሠርቷል ለማለት ያስደፍራል። ስለሆነም ሦሥቱም ተከታታይ አገዛዞች አንዱ ካለፈው ገዢ

Ethiopia’s Zone 9 Bloggers Honored with International Press Freedom Awards

Tadias Magazine
By Tadias Staff
New York (TADIAS) — Ethiopia’s Zone 9 bloggers were honored with the 2015 International Press Freedom Awards on Tuesday in New York City.
The Ethiopian blogging collective shared the prestigious CPJ award with other journalists from Malaysia, Paraguay and Syria.

ዜጎች እርዳታ እንዲደረግላቸው እየጠየቁ ቢሆንም እስካሁን በቂ ምላሽ ሊሰጣቸው አልቻለም

 ኢሳት ዜና :-ከተለያዩ ክልሎች ለኢሳት የሚላኩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እርዳታ የሚጠይቁ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ በቂ የሆነ እርዳታ እየተከፋፈለ አይደለም።

በአማራ፣ በትግራይ ፣ በሶማሊ፣ በደቡብና በአፋር የእለት ደራሽ ምግብ የሚጠይቁ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ህጻናት በአልሚ ምግብ እጥረት የተነሳ ለበሽታ እየተዳረጉ በመሞት ላይ ናቸው፡፡የረሃቡ ሁኔታ አስከፊ እየሆነ ቢመጣም በመንግስት ባለስልጣናት በኩል የሚሰጠው መግለጫ እርስ በርስ የሚጣረስ በመሆኑ፣ በተረጅዎች ህይወት ላይ ተጽኖ እያሳረፈ ነው።

በደቡብ ክልል በርካታ ከተሞች አርበኞች ግንቦት7 የድጋፍ ወረቀቶች ተበተኑ

ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው ወጣቶች እንደገለጹት፣ በወላይታ ሶዶ ከ1 ሺ የማያንሱ በራሪ ወረቀቶች ተበትነዋል። ራሳቸውን ያደራጁት ወጣቶች በፖሊስ፣ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የገበያ ማእከላት የአርበኞች ግንቦት7 ሊ/መንበር የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ን ፎቶ እንዲሁም የቅስቀሳ መልእክቶችን የያዙ ወረቀቶችን በግድግዳዎች ላይ ለጥፈዋል። ፖሊሶች ወረቀቶችን በመቅደድ ተጠምደው ማርፈዳቸውን፣ በከተማው ውስጥ ትልቅ የመነጋገሪያ ርእስ መፍጠሩንም ወጣቶች ለኢሳት ገልጸዋል።

የመንግስት ደህንነቶች የኢሳትን ዌብሳይት ሰብረው ለመግባት ያደረጉት ሙከራ ከሸፈ

ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመረጃ ደህንነት ባለሙያዎች በማስረጃ አስደግፈው እንደገለጹት የኢህአዴግ የመረጃ ደህንነት ሰራተኞች መብራቱ በሚል ስም ኢሳት በኢንተርኔት የሚያሰራጨውን ዌብሳይት ሰብረው በመግባት፣ ጉዳት ለማድረስ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል።

የኮምፒዩት መለያ ቁጥሩ 197. 156. 86. 162 የሆነ አዲስ አበባ የሚገኝ ኮምፒዩተር መብራቱ በሚል የመግቢያ ስም ወደ ወደ ኢሳት ዌብሳይት ለመግባት ቢሞክርም አልተሳካለትም።
መንግስት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማውጣት የስለላ ሶፍትዌሮችን ለመጠቀም ሲሞክር መጋለጡ የአለም መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የኢሳትን የቴሌቪዥን ስርጭት ለማፈን ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አድርጓል። ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በሁዋላ አሁን ደግሞ ተመሳሳይ ስም በመጠቀም የኢሳትን ዌብሳይት ሰብሮ መረጃዎችን ለመጥፋት ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱ ገዢው ፓርቲ ከኢሳት ጋር የገጠመውን ትንቅንቅ የሚያሳይ ነው።

በቴፒ ከተማ ውጥረት ነግሷል

በደቡብ ምዕራብ ቴፒ ከተማ የተቀሰቀሰውን አስተዳደራዊ አለመግባባት ተከትሎ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአካባቢው መስፈሩ ተገለጠ።

በከተማዋ ላይ የተነሳው የይገባኛል አስተዳደራዊ ጥያቄ ስምምነት ባለማግኘቱ በርካታ ሰዎች በተቃውሞ ጫካ መግባታቸውንና ድርጊቱ በከተማዋ ውጥረት ማንገሱን በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

Tuesday, November 24, 2015

በወላይታ ሶዶ ህዝቡን ለትግል የሚያነሳሱ መፈክሮችና ምስሎች በብዛት ተለጠፉ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮበወላይታ ሶዶ በሦስቱም ክፍለ ከተሞች አርበኞች ግንቦት 7 እያፋፋመው የሚገኘውን የነፃነት አርበኝነት የሚደግፉና ህዝቡን ለትግል የሚያነሳሱ መፈክሮችና ምስሎች በብዛት ተለጠፉ፡፡
ህዝቡ በአርበኞች ግንቦት 7 ሁለገብ የትግል ማዕቀፍ ውስጥ ተሰባስቦ ሁሉም በአንድት ተነስቶ ለተጀመረው ፀረ-ወያኔ፣ ፀረ-አምባገነናዊ የህወሓት አገዛዝ ፍልሚያ

" የየጁ ደብተራ…" በኤርሚያስ ለገሰ ከቅርብ አመታት ወዲህ በአከባበር እየተለወጠ የመጣውን የህውሀት እና ልጆቹን ልደት አጨንቁሮ ለተመለከተ ብዙ ነገሮችን መናገር ይችላል።

 በልሙጡ ለሚያይ ሰው የብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴግ የልደት በአላት " መወድሰ ህወሀት" እየሆኑ መሔዳቸውን በቀላሉ መታዘብ ይችላል። ህውሀቶች የየካቲት 11 እና እሱን ተከትሎ የነበሩት ሳምንታት አልበቃቸው ብሎ ህዳር 11 ( የኦህዴድ እና የሐይለማርያምን ልደት ቀን ረሳሁት) በቤቢ ሻወርነት እየተጠቀሙበት ነው። ርግጥ ነው ህውሀቶች ወገባቸውን ይዘው " እኛ በልጆቻችን ውስጥ አድረን ቡራኬያችንን ብንወስድ እናንተን ለምን አሳከካችሁ?" እንደሚሉን ይገባኛል። ባያሳክከን ጥሩ ነበር። ፈር የሳተው ቡራኬ በኢትዬጲያ ህዝብ ላይ እያሳረፈ ያለው ጫና በአይናችን ላይ እየሔደ አላሳከከንም ማለት እንደ ብአዴን አባላት ቧልት ስለሚሆንብን ነው። እናም ቢያንስ የብአዴን አባላትን የውስጥ ጩኸት እኛ ብንጮኸው ምስጋናቸው ዘግይቶም ይደርሰን ይሆናል።

Sunday, November 22, 2015

ወያኔ ክብሩ አሰፋን ረሸነው!

አርበኛ አታለል አሰፋ በደሙ ከፃፋቸው አስደማሚ የአርበኝነት ታሪኮ፣ አስደናቂ ጀግንነቱና አንፀባራቂ ጀብዱው መካከል 150 አርበኞችን እየመራ ተከዜን ተሻግሮ ሚያዚያ 16 1998 ዓ.ም አርማጭሆ ጎደቤ ላይ ሰፍሮ ይገኝ በነበረው የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍቶ ጠንካራ ምት በማሳረፍ የጦር ሰፈሩን ሙሉ በሙሉ ደምስሶ በርካታ ቁጥር ያለው ወታደርና ዲሽቃ መማረኩ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡

Friday, November 20, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) በጎንደር ወገራ ወረዳ ንዑስ ወረዳ ገደብዬ በረሃቡ ለተጎዱ ህፃናት ከለጋሾች የተሰጠው አልሚ ምግብ በአግባቡ እየተከፋፈለ እንዳልሆነ በዛሬው ዕለት ከቦታው የደረሰን መረጃ አጋልጧል፡፡

ከለጋሾች የተቸረው የህፃናት አልሚ ምግብ ከቦታው መድረሱን ያረጋገጡት የሰባት ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጎስቋላ ገበሬ እናቶች ልጆቻቸውን አንዱን በጀርባቸው አዝለው ሌላኛውን በደረታቸው ታቅፈው በዛሬው ዕለት ከየቀዬዎቻቸው ወደ ገደብዬ ከተማ ሲጎርፉ የዋሉ ሲሆን በጣት ከሚቆጠሩት እጅግ በጣም ጥቂት እድለኞች በስተቀር ሁሉም ለማለት በሚቻል ሁኔታ አልሚ ምግቡ ሳይሰጣቸው ከረሃብና ከችጋራቸው በላይ መንገድ ብቻ ተመትተው ተመልሰዋል፡፡
አልሚ ምግቡ

የጉጂ ማህበረሰብ አባላት ህዝባዊ እምቢተኝነት ለመጀመር እየተዘጋጀን ነው አሉ

ኀዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በጉጂ ዞን የሚኖሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች በአንድ ላይ በመሆን ያቀረብነው የመልካም አስተዳደር እና የፍትህ ጥያቄ ካልተመለሰ የህዝባዊ እምቢተኝነት ተቃውሞአቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። 

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች ዜጎች በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ነው

ኀዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአለማቀፍ ድርጅቶች ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን እየገለጹ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ችግሩ አስከፊ ሆኖ ቀጥሎአል።

ብአዴን የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰልፍ እንዲወጡ ሲያሳድድ እንደነበር ተገለጸ

ኀዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህዳር 9፣ 2008 ዓም ብአዴን በሰልፉ ለመሳተፍ የሚፈልገውን አሽከርካሪ ማግኘት ባለመቻሉ የባጃጅ ማህበር አመራሮችን በመንገድ ትራንስፖርት አማካኝነት በመጥራት በሰልፉ ባይሳተፉ የአምስት መቶ ብር ቅጣት እንደሚፈጽም በማስፈራራት ከቀኑ 10፡30 እስከ 11፡30 መንገዶችን በመዘጋጋት ህብረተሰቡን ሲያስጨንቅና ባጃጆችን ተሰለፉ በማለት ሲያሳድድ እንደነበር ዘጋቢያችን ገልጻለች።

ህዝባዊ ተቀባይነቱን ያጣው ወያኔ በሽፍትነት ዘመኑ ትግራይ ውስጥ ሲያደርግ እንደረነበረው ሁሉ፣ መንግስታዊ ስልጣኑን ከያዘም በሁዋላ መሰልጠን አቅቶትና እንደመንግስት ማሰብ ተስኖት፣ አገዛዜን ይቃወማሉ ብሎ የሚጠረጥራቸውን ዜጎች የቅርብ ቤተሰቦችና የሩቅ ዘመዶች ሳይቀር ማሰቃየት መጀመሩን ከአራቱም የአገራችን ማዕዘናት በየቀኑ የሚደርሱን ሪፖርቶች ያመለክታሉ።

Thursday, November 19, 2015

ወንጌል እና ሰይጣን፣ ትግሬ እና ብርቱካን ( ሄኖክ የሺጥላ )

ወንጌል እና ሰይጣን፣ ትግሬ እና ብርቱካን ( ሄኖክ የሺጥላ )

የብርቱካን አሊ ልጅ አብዱ በራ’ብ እንዳልሞተ ወያኔ ነገረን ። በዛ ላይ ቢቢሲ ደሞ እንደ ኢሳት እንደዋሸ ተነገረን ። ይሁን !
እንበልና የብርቱካን ልጅ በራብ አልሞተም ፣ ቀጥሎም የብርቱካን ልጅ በቁንጣን ነው የሞተው እንበል ፣ እንደውም እንደ ወያኔ ባለ ስልጣን ልጆች ሰክሮ መንገድ ላይ ውስኪ እየደፋ ሲሄድ የደፋው ውስኪ አዳልጦት ነው የሞተው እንበል ፣ ከፍ ሲል ለቢቢሲ ጋዜጠኛ ያሳየችው ቅጠል የተሸፈነ የልጇ የአብዱ መቃብር ሳይሆን የእህል ማስቀመጫ ጎተራ ነው እንበል ፣ እነዚህ ሁሉ እውነት ሆኑ እንበል ፣ ከዚያስ ?

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ ማጎሪያ ቤት ውስጥ በጣም ታሞል።


ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ተሜ) በዝዋይ ማጎሪያ ቤት ውስጥ በጣም መታመሙን ወንድሙ


fa99e-temesgendesalegn
ተመስገን እጅጉን በጣም ታሞል። ለተመስገን በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ህክምና የለም።
ከ24 ቀናት በኃላ በዐይናችን እንድናይው “ሲፈርዱ” ሲፈልጋቸው ከልክለው ሲያሰኛቸው ስለሚፈቅዱ ፈቀዱ ከማለት ፈረዱ ማለት ይሻላል ብዬ ነው። ዛሬ ህዳር 8/2008ዓ.ም ዝዋይ እስር ቤት ተመስገንን ዐይቼዋለሁ። “እጅጉን በጣም ታሟል” ከወገቡ ህመም በሻገር “የግራው ጆሮ መድማት” ጀምሮል። የሚደማውን ጆሮ ቶሎ ቶሎ እየጠረገ በመከራ ነው የሚያናግረኝ። ሊያናግረኝ አፉን ማንቀሳቀስ ሲጀምር የጆሮው ህመም ንግግሩን ያቆርጠዋል። እኔ ህመሙን ላለማየት አይኔን የማሳርፈበት ቦታ አጣለሁ። ከበውን የቆሙት ወታደሮች እና ሀላፊዎች ህመሙን አይተዋል። በተመስገን ላይ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ሌላ እስር ቤት ሰርተውለታል ከስረኞች የሚገለልበት፣ ምንም አይነት ህክምና የማያገኝበት እስር ቤት።

አሁንም እስረኞች ነን - ከዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የተሰጠ መግለጫ


ከሚያዝያ 17 2006 ጀምሮ በፓሊስ ቁጥጥር ስርውለን የነበርነው 3 ጋዜጠኞችና እና 6 የዞን9 ጦማርያን ከአንድአመት ከሁለት ወር እና ከአንድ አመት ከ5 ወር የእስር ቆይታ በኋላ ሁላችንም ከእስር አንደተፈታን ይታወሳል፡፡ በሃምሌ ወር መጀመሪያሶስት ጋዜጠኞች እና ሁለት ጦማርያን አቃቤ ህግ ክስ አቋርጦ፣ በማስከተል አራት ጦማርያን ደግሞ ነጻ ተብለው ከእስር መለቀቃችንየሚታወስ ሲሆን ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በዋስትና ላይ ሆኖ የቀረበበትን “አመጽ የማነሳሳት ክስ” እንዲከላከል መባሉም ይታወቃል፡፡

የወልቃይት ህዝብ የወያኔ ስርሃትን ለመታግል በአንድነት መነሳቱ ታወቀ

የወልቃይት ህዝብ ህወሓት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ ተደጋጋሚ ግፍና በደል ያደረሰበት በመሆኑ መቸም የማይፈታ ቂም አለው፡፡ ህወሓት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ደግሞ ሳይፈልግ ከጎንደር እንዲገነጠል ተደርጎ ወደ ትግራይ ክልል በመጠቃለሉ ሲያነሳው የቆየው ያልተመለሰ ጥያቄ አለው፡፡

የብአዴን ታጋዮች የሞትንለት እና የደማንለት ድርጅት አክስሮናል አሉ፡፡

ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብአዴን ህዳር 11 በባህርዳር በሚያከብረው በአል ላይ ለነባር ታጋዮች ልዩ የሽልማት ስነስርዓት ያዘጋጀ ሲሆን፣ ለሽልማቱ የታጩት አመራሮች በድርጅት ነባር አባላት አስተያየት እንዲሰጥባቸው ማድረጉን ተከትሎ፣ ነባር ታጋዮቹ በብአዴን አመራሮች ላይ የሰላ ትችት አቅርበዋል፡፡ ታጋዩች ከድል በሁዋላ እስከ ሜጀር ጀኔራልነት የሚደርስ ማዕረግ ቢሰጠንም ከመዝገብ ቤት ያለፈ የውሳኔ ሰጭነት ስልጣን የለንም ብለዋል፡፡

በኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ውስጥ ፍርሃት ነግሷል

ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በነሃሴ ወር ባካሄደው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የመልካም አስተዳዳር ችግሮችን ለመፍታት ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ እርምጃ እንደሚወድድ ውሳኔ ቢያሳልፍም አብዛኛው አመራር የችግሩ ሰለባ በመሆኑ በግንባሩ እርስበእርስ ከፍተኛ መፈራራትና መጠባበቅ መከሰቱ ታውቋል፡፡

በሰሜን ሸዋ 23 እስረኞች አመለጡ

ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ማክሰኞ ሸዋ ሮቢት በቀወት ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ እስረኞች በሙሉ ያመለጡ ሲሆን፣ እስረኞቹ እስካሁን አልተያዙም። አብዛኞቹ እስረኞች በህገወጥ መንገድ ትነግዳላችሁ ተብለው የተያዙ ነበሩ። እስረኞቹ ሌሊት ላይ የጭቃ ቤቱን ግድግዳ በውሃ አርሰው ከቀደዱት በሁዋላ ሁሉም በአንድ ላይ አምልጠዋል።

ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ እስረኞችን ለመያዝ ፍተሻ በመካሄድ ነው። የወረዳው ነዋሪዎች እስረኞችን አምጡ በማለት እየተሰቃዩ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ሰላምታየን አቀርባለሁ! ናትናኤል ያለምዘውድ (ከሸዋሮቢት እስር ቤት)

ይቺን ፅሁፍ የምጽፈው ዛፍ ጥላ ስር ተወሽቄ ሙቀቱን ለመከላከል ከታጠቅኋት ቁምጣ ሱሪ ላይ ደብተሬን አስደግፌ፣ ሀሳቤን ለመሰብሰብ ስሞክር አንዱ ተፈንክቶ ደም እያዘራ ሲያልፍ፣ ሌላው ስምንት ቁጥር ታስሮ አሰቃቂ የዱላ መዓት ሲወርድበት፣ ጨለማ ቤት የታሰሩት የጣዕር ድምፅና፣ በሚዝገመገመው የድርቀት ወላፈን ክፉኛ ከሀሳቤ እያናጠበኝ የምቸገር፣ ሁለት ፍራሽ ላይ ለሰባት ተጠቅጥቄ የምተኛ፣ ለጊዜው የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች የሚደርሱብኝ......ሸዋ ሮቢት ‹‹ልማታዊ›› ማረሚያ ቤት ላይ በአስቸጋሪው ሁኔታ ደረቴን ነፍቼ የምታሰር የሰማያዊ ፓርቲ አባል ነኝ፡፡ 

Wednesday, November 18, 2015

በቤንሻንጉል ጉሙዝ 12 የአማራ ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተገኙ

ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጊቱ የተፈጸመው ባለፈው መስከረም ወር ሲሆን የቀብሩ ስነስርዓት የተፈጸመው ግን ባሳለፍነው ሳንምት ነው። በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ 12 የአማራ ተወላጆች ለቀን ስራ ተብለው ከተወሰዱ በሁዋላ በወረዳው አስተዳደሪ ትእዛዝ ኮከል ቀበሌ ላይ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተረሽነዋል።አስከሬናቸው ተቆራርጦ በጆንያ ተጠቅሎ መገኘቱንና የቀብር ስነስርዓታቸውም መፈጸሙን ምንጮች ገልጸዋል።

በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ 2 መምህራን ታሰሩ

ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህር ወንድማገኝ አንጆሎ እና መምህር መስፍን በላይ የታሰሩት ባለፈው ሳምንት ሲሆን፣ ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ እስር ቤት ተወስደዋል። ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር በተያያዘ መታሰራቸውን ምንቾች ገልጸዋል። መምህራሩ ከሰው ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

መምህር ወንድማገኝ ከመታሰራቸው በፊት ዩኒቨርስቲው የስራ እና የእግድ ደብዳቤ ጽፎላቸው ነበር። በመምህር ወንድማገኝ ላይ የቀረበውን ክስ መነሻ፣ የየኑቨርስቲ ባለስልጣናት የጻፉዋቸውን ደብዳቤዎች በመጨረሻም ግንቦት7 ተብለው ታፍነው ለምን እንደተወሰነባቸው ነገ በልዩ ዝግጅት አጭር ዘገባ እናቀርባለን።

አለማቀፍ የአፋር ዲያስፖራ በአፋሮች ላይ የሚደረሰውን ጥቃት በተመለከተ ለጅቡቲው ፕሬዚዳንት ደብዳቤ ጻፈ

ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእንግሊዝኛ አጭር አጠራሩ ፊዳ የተባለው የአፋር ድርጅት ለጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ በጻፈው ደብዳቤ በአፋር ህዝብ ላይ የዘር ማጽዳት በመፈጸም፣ የራስዎን ዘሮች በቦታው ላይ እያስቀመጡ ነው ሲል ከሷል።

የወልቃይት ህዝብ ለነፃነቱ ሊታገል ከመቸውም ጊዜ በላይ ቆርጦ በአንድነት መነሳቱ ታወቀ

የወልቃይት ህዝብ ህወሓት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ ተደጋጋሚ ግፍና በደል ያደረሰበት በመሆኑ መቸም የማይፈታ ቂም አለው፡፡ ህወሓት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ደግሞ ሳይፈልግ ከጎንደር እንዲገነጠል ተደርጎ ወደ ትግራይ ክልል በመጠቃለሉ ሲያነሳው የቆየው ያልተመለሰ ጥያቄ አለው፡፡
ህወሓት የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የጀመረውን የነፃነት ትግል እንቅስቃሴ ጦር ኃይሉን ተጠቅሞ ለመደፍጠጥ ወደ አካባቢው ያለማቋረጥ ሰራዊት እያዘመተ አሰቃቂ የህዝብ ጭፍጨፋ በማድረግ ዘር ማጥፋት ፈፅሟል፡፡

“15 ሚሊዮን ህዝብ መደበቅ ሰማይን በመዳፍ ለመሸሸግ እንደ መሞከር ይቆጠራል” (በውቀቱ ስዩም)

በውቀቱ ስዩም

ባገራችን ኣብዛኛው ዜጋ ለቀን ጉርስና ላመት ልብስ ሲታገል የሚኖር ነው፡፡ ጌቶች ደግሞ ኣማርጠው ይበላሉ፡፡ ኣማርጠው ይለብሳሉ፤በለስ ሲቀናቸው ደግሞ የሃያ ኣምስት ሚሊዮን ብር ቪላ ይቀልሳሉ፡፡ እንዲያም ሆኖ ደግሞ መከበርና መደነቅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰው ምንም በስጋው ቢመቸው በሌላው ተመዝኖ እንደቀለለ ሲሰማው ደስተኛ ኣይሆንም፡፡ ስለዚህ ጌቶች ያስንቀናል ብለው የሚያስቡትን ነገር በሙሉ ጠምድው ይይዙታል፡፡ ይዋጉታል፡፡ ኢትዮጵያ- ጌቶች ለኩራታቸው፤ ዜጎች ለራታቸው የሚታገሉባት መድረክ ናት፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ያቀደውን ህዝባዊ ስብሰባ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀየር መገደዱን ገለፀ

• ‹‹ከደህንነትና ፖሊሶች ጋር ካልተነጋገርኩ አልፈቅድም›› አስተዳደሩ
• ‹‹ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት እነሱን መለማመጥ አያስፈልግም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ጋር ለመነጋገር ህዳር 18/2008 ዓ.ም ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ አቅዶ የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ አስተዳደር በፈጠረበት መሰናክል ምክንያት ያቀደውን ህዝባዊ ስብሰባ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀየር መገደዱን ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

ትግርኛ ተናጋሪው VOA ጋዜጠኛ ወሎ ድረስ ምን ኣስኬደው?~~

ግርማይ ገብሩ ወይዘሮ ብርቱካን ለBBC የሰጡትን ቃለመጠይቅ ውሸት መሆኑን ለማረጋገጥ በፌደራል ህግ መሰረት ትግራይ ክልልን ተሻግሮ ኣማራ ክልል ድረስ ዘልቆ ወይዘሮ ብርቱካን ኣነጋግረዋል። ኣማራ ክልል ውስጥ ለምን ሄደ ?ማንስ ላከው? ትግራይ ክልል ውስጥ የሚጣራ ነገር ጠፍቶ ነው? ወይስ ሌላ ኣጀንዳ ኣለው? የሚለውን ማይቱ ሳይሻል ኣይቀርም፣

Tuesday, November 17, 2015

ብአዴን ህዝቡን በግዳጅ ሰልፍ እያስወጣ በአሉን እያከበረ ነው

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-35ኛ አመት በአሉን በማክበር ላይ ያለው ብአዴን ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች፣ ነጋዴዎችና በተለያዩ ሙያ የተሰመራዩት ሁሉ ስራቸውን አቁመውና ድርጅታቸውን ዘግተው በአሉን እንዲያከብሩ ተገደዋል። በበአሉ ላይ ባልተገኙት ላይ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው ቀጣቶች እንደሚተላለፍባቸው የድርጅቱ ካድሬዎች ሲቀሰቅሱ መሰንበታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በኮምቦልቻ፣ ደሴ ጎንደርና ሌሎችም ቦታዎች ህዝቡ ለብአዴን ሰልፍ እንዲወጡ ተገደዋል። በተለይ ተማሪዎች በበአሉ ላይ ካልተገኙ በትምህርታቸው ውጤት ላይ አደጋ እንደሚገጥማቸው ተነግሯቸዋል።

የህወሃት ድጋፍ ያለው ቡድን በአፋር ስልጣኑን ተቆጣጠረ

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል ራሳቸውን ከህወሃት ተጽኖ ለማላቀቅ በሚፈልጉ የአቶ ጣሃ አህመድ ቡድኖችና ህወሃት ከጀርባ ሆኖ በሚመራቸው በአቶ ስዩም አወል መካከል ሲካሄድ የነበረው የስልጣን ሽኩቻ ፣ በህወሃት የሚደገፉት አቶ ስዩም የአፋር ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው በመመረጥ አሸንፈዋል።

የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የቅርብ ቤተሰብ በበርካታ ዜጎች ላይ የፈጸሙት ማጭበርበር ተጋለጠ

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለቤት አባት የሆኑት አቶ አሰፋ ሩዎ ሂወራ በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ነዋሪዎችን የቤት ካርታ በመቀበል በአመት ከ25 ሺ እስከ 30 ሺ ብር እንደሚከፍሉ አስታውቀው የባንክ ብድር ከወሰዱ በሁዋላ፣ ብድሩን ለመመለስ ሳይችሉ በመቅረታቸው የቤታቸውን ካርታ ያስያዙ ሰዎች ቤታቸው በሃራጅ ሊሸጥባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የጤና ቀውሶች ተጋላጭ ትሆናለች በማለት አስጠነቀቀ

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓለም ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠነ ሰፊ የሆኑ የጤና ችግሮች እንደሚከሰቱ የዓለም የጤና ድርጅት የአየር ንብረትና የጤና እክሎችን በሚተነትነው ሪፖርቱ አስጠንቅቋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ለሶማሊያ ከወታደራዊ ይልቅ ፖለቲካዊ መፍትሔ ያስፈልጋታል አሉ

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ማህሙድ በአገራቸው ላለፉት አስር ዓመታት ለተንሰራፋው የአልቃይዳና የአልሸባብ ጥቃቶች እልባት ሊገኝለት የሚችለው ፖለቲካዊ መግባባቶችን በመፍጠር ካልሆነ በስተቀር በወታደራዊ የኃይል ጥቃቶች ብቻ ዘላቂና አስተማማኝ የሆነ ሰላም ማስፈን እንደማይቻል አበክረው ተናግረዋል።

በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ ፣በበርሜል እየሞላን ጥይቶችን እና መሳሪያዎችን ስላዘነብን ብቻ አልሸባብን አናጠፋውም።የእርቅና የምህረት መንገዱን ሁሌም መፈለግ ያሻናል።አሁንም በሽምግልና መንገድ መፍትሔ መፈለጉን እየቀጠልንበት ነው ብለዋል ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ማህሙድ።
እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ከአስር አገሮች የተውጣጡ የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ጦር ወታደሮች በሶማሊያ ቢሰፍሩም ፣ በአገሪቱ ዘላቂ የሆነ ሰላም ማስፈን ግን አልቻሉም። በቅርቡ ከዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ወጣ ብሎ በደቡባዊ ሶሊያ ጃናሌ ግዛት 80 የሚሆኑ የሰላም አስከባሪ ጦር አባላት መገደላቸውን ብሉንበርግ ዘግቧል

የህወሓት አገዛዝ ወጣቶችን ለውትድርና አስገድዶ ማፈስ ጀመረ፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
የህወሓት አገዛዝ ወጣቶችን ለውትድርና አስገድዶ ማፈስ ጀመረ፡፡
በጎንደር ወገራ ወረዳ ንዑስ ወረዳ ገደብዬ የቀበሌ አስተዳዳሪዎችና የማዘጋጃ ቤት ሹሞች አስረኛ ክፍል ጨርሰው ስራ ፈትተው የተቀመጡትን ወጣቶች እንዲሁም ዘጠነኛ ክፍልን በመማር ላይ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶችን ጭምር "በ5000 ብር ደመወዝ ስራ እንቀጥራችኋለን" በሚል ማማለያ አሽበልብለው በስልጠና ስም ባንድ አዳራሽ ውስጥ አጉረው በፖሊስ በማገት በመጨረሻም ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ጭነዋቸዋል፡፡

ለውትድርና በግዳጅ የታፈሱት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ዕድሜያቸው ከ15-18 ዓመት የሚደርስ ሲሆን አብዛኞቹ የጎንደር ወገራ ወረዳ ጉንትር፣ ጭልፎ ወንዝና ሚጧ ቧግሽ የሚሰኙ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ናቸው፡፡
እንዲሁም በተጨማሪ የህወሓት አገዛዝ በአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ወጣቶች በአንድ ሰፊ ግቢ ውስጥ አሽጎ አግቷቸው ይገኛል፡፡ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከሎችም በቅርቡ ሊጭናቸው እየተዘጋጀ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

Monday, November 16, 2015

መንግስት ረሀቡ የደቀነውን አደጋ ለማቃለል እየሞከረ ነው

ኀዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት በአንድ በኩል የውጭ እርዳታ እየጠየቀ በሌላ በኩል ረሃቡን ብቻውን እንደሚቋቋመው መግለጹ ግራ እያጋባ ነው።

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ችግሩ ከመንግስት አቅም በላይ

በመራዊ የፌደራል ፖሊሶች ወጣቶችን አፍነው ወሰዱ

ኀዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊስ እና የደህንነት ሃይሎች ከባህርዳር ከተማ በስተደቡብ በ35 ኪሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ መራዊ ከተማ በመገኘት የከተማዋን ወጣቶችንና ነዋሪዎችን ከሌሊቱ አስራ አንድ ሰአት ላይ እየደበደቡ አፍነው ወስደዋቸዋል።

እነ አቶ ሀብታሙ አያሌው አቃቤ ህግ የጠየቀው ይግባኝ ተቀባይነት አገኘ

ኀዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ተበይኖላቸው የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የጠየቀው ይግባኝ ያስቀርባል በመባሉ ክሱ እንደገና ሊታይ መሆኑን ነገረ ኢትዮጵአ ዘግቧል።

የብአዴን ንብረት የሆነው አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ፍትሃዊ ያልሆነ ከፍተኛ ወለድ በማስከፈል ህብረተሰቡን እየበዘበዘ ነው ተባለ

ኀዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በስፋት በመሰማራት የአነስተኛ ነዋሪውን ህይወት ለመቀየር ትልቅ መፍትሔ አለው በማለት የገዢው መንግስት በስፋት እየሰራበት ያለው የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም፣ ከሌሎች የባንክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተለየ ከፍተኛ ወለድ በማስከፈል ህብረተሰቡን እየበዘበዘ መሆኑን ደንበኞች በተለይ ለኢሳት ተናግረዋል፡፡

ሱዳናዊያን በኢትዮጵያ ታጣቂዎች ጥቃት እየደረሰብን ነው አሉ

ኀዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የጸጥታው ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱንና በሱዳናዊያን በግፍ ለተገደሉት ኢትዮያዊያን አፋጣኝ አጸፋዊ ምላሽ የሰጡት የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ታጣቂዎች ሃምሳ መንደሮችን በቁጥጥራቸው ስር ማድረጋቸውንና ሃያ ለሚሆኑ ያገቷቸውን ሱዳናዊንን 360ሺህ የሱዳን ዲናር ማለትም 59 ሽህ ዶላር አስከፍለው መልቀቃቸው ተዘግቧል።

የጎንደር-ደልጊ ነዋሪዎች የሆኑ ከ10 በላይ ሰላማዊ ሰዎች "ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ" በሚል ከጥርጣሬ ያላለፈ ሰበብ ብቻ በህወሓት አገዛዝ ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች ታፍነው ተወሰዱ፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

የጎንደር-ደልጊ ነዋሪዎች የሆኑ ከ10 በላይ ሰላማዊ ሰዎች "ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ" በሚል ከጥርጣሬ ያላለፈ ሰበብ ብቻ በህወሓት አገዛዝ ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች ታፍነው ተወሰዱ፡፡

በህወሓት አገዛዝ ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች ቅዳሜ ዕለት ከየመኖሪያ ቤታቸው እየታፈኑ ከተወሰዱት ከ10 በላይ የሚሆኑ የደልጊ ሰላማዊ ነዋሪዎች መካከል፦
•አቶ አሰፋ ገዳሙ
•ወጣት አዲሱ አያሌው
•አቹ ወርቁ
•ሙሉጌታ ክፍሌ 
•ያሃቤ... የተባሉት ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም "ልጅህ ወደ ኤርትራ በመሄድ አርበኞች ግንቦት ሰባትን በአካል ተቀላቅሏል" በሚል ምክንያት አቶ ሙሌ አላምረው የተባሉትን የህወሓት ሰዎች በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው ሲሞክሩ አምልጠው ለመሰወር እንደቻሉ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

Sunday, November 15, 2015

ረሃብና ፖለቲካ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)


አገራችን ኢትዮጵያ ምንም እንኳን ዛሬ በምጣኔ ሀብቷ፣ በፖለቲካዊና ማህበራዊ እድገቷ ከዓለም አገሮች በጠቅላላ ወደ ኋላ የቀረች ብትሆንም ቅሉ ጀማሪና ልዩ የሚያደርጓት ብዙ ታሪካዊ እሴቶችና የተፈጥሮ ችሮታዎች አሏት፡፡ የሰው ዘር መገኛና ነፃነቷን ጠብቃ የቆየች መሆኗ ልዩ ከሚያደርጓት ታሪካዊ እሴቶቿ መካከል ጎልተው የሚጠቀሱና ዓለም ሁሉ የሚያውቃቸው ናቸው፡፡ ቀደምት ህዝቧ ትቶት ያለፈው የኪነ-ህንፃ ረቂቅ ጥበብ እትም አሻራም ስሟን በውዳሴ እያስጠራ ዘመናትን አሻግሯታል፡፡