የኢህአዲግ መንግስት 11ኛው ሰዓት ላይ የደረሰ ይመስላል፡፡ ካድሬዎቹ በመላው ሀገሪቱ የሚይዙት የሚጨብጡትን አጥተው፤ደም እንዳሰከረው ሰው መቅበዝበዙን ተያይዘውታል፡፡ ገሚሶቹ ካድሬዎች ከስርአቱ ሸርተት ማለት ጀምረዋል፤በህዝብ ላይ ለሰሩት ግፍም ማጣፊያ ይሆናቸው ዘንድ የስርአቱን ብልት ደህና አርገው እየተለተሉት ነው፡፡ …..በዚህ ሰዓት ኢህአዲግ ወዴት እንደሚገባ፣ምን እንደሚያደርግ ሁሉ አያውቅም፡፡ በየአቅጣጫው የሚነሱ ተቃውሞዎችና ለውጥ ለውጥ የሚሉ ድምፆች ተበራክተውበታል፤እንቅልፍ ነስቶታል፡፡ ስለዚህ በደመነፍስ የሚያደርገው ድርጊት፤በህብረትካልመከትነውና ካላስቆምነው፤ ጥቂቶችን ተጎጂ ማድረጉ የማይቀር ነውና የአንዱ መነካት የሌላውም ነውና ሁላችንም በጋራ በመነሳት የስርአቱን ውድቀት በይፋ እናብስርለት፡፡
ዛሬ በደብረማርቆስና አካባቢዋ የሚገኙ ለውጥ የናፈቃቸው፤ስርአቱ ያንገፈገፋቸው፣……ለነፃነታቸው መከበር እራሳቸው ዘብ የቆሙ ትንታግ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ታሪክ የማይረሳው ገድል ፈፅመዋል፡፡ ስርአቱን በግልፅ አታስፈልገንም ብለውታል፡፡…ይህን ተከትሎም የሰው ደም ማፍሰስ ግብሩ የሆነው የኢህአዲግ አንባገነን መንግስት በተማሪዎቹ ላይ ቅልብ ውሾቹን አሰማርቶባቸዋል፡፡…..በዚህም በርካታ ተማሪዎች በመታሰርና በመደብደብ ላይ ናቸው፤……እነዚህ ወጣቶች ይህን መስዋት የሚከፍሉት ለሁላችንም ነፃነት መሆኑን ተረድተን በጋራ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል፡፡ …..ኢህአዲግን እስካሁን መረን እንዲለቅ ያደረገው፤ ‹‹ያንተ ቤት ሲንኳኳ፤ ይሰማል ከኔ ቤት›› ብለን፤ሌላው ወንድማችን በአንባገነኖቹ ሲታሰር፤ሲደበደብ፣ሲገደል፣ሲሰደት………በጋራ ልንቆምና ድምፃችንን ልናሰማ ባለመቻላችን ነው፡፡ ……ይህ ሁኔታ ግን ዋጋ እያስከፈለን መሆኑን መገመት አያዳግትም፡፡ …..ስለዚህ ይህን ከየአቅጣጫው እየተቀጣጠለ ያለውን የለውጥ ፈላጊዎች ችቦ ልንቀባበለው ግድ ነው፡፡ ….ይህን የንፁሀን ደም ያሰከረውን መንግስት እስኪረጋጋ የምንጠብቅበት አንዳችም ምክንያት የለንም፡፡ ሁሉም ሰው ለነፃነትና ክብሩ ይደራጅ፤ይነሳ!!!!!!! …… ኢትዮጵያ ልጆቿ እየነቁላት ነው!!! ….አምላክ ሀገራችንን ይጠብቃት!!!….ድል የህዝብ ነው!!!
No comments:
Post a Comment