Saturday, January 24, 2015

የሕወሓት አስተዳደር 4 የአንድነት አመራሮችን አሰረ * አንድነት ጥር 17 የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ስርዓቱን እንቅልፍ ነስቶታል

(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት አስተዳደር ጉዳይ አስፈጻሚ መስሪያ ቤት እንደሆነ ላለፉት 23 ዓመታት ሲነገርለት የቆየው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲን ለማፍረስ የሚያደርገው ሴራ ከተጋለጠ በኋላ; አሁን ደግሞ ሌላኛው የሕወሓት አስተዳደር ጉዳይ ፈጻሚ የሆነው ፖሊስ 4 የአንድነት አመራሮችን ማሰሩን ከአዲስ አበባ የመጡ መረጃዎች አመለከቱ::
ከሚሊዮኖች ድምጽ ባገኘነው መረጃ መሰረት የታሰሩት 4 የአንድነት ፓርቲ አመራሮች:
1. አቶ አስራት አብርሃ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ
2. አቶ ሰለሞን ስዩም የፍኒትና ሚሊዮኖች ድምጽ ኤዲቶሪያል ሃላፊ
3. አቶ ስንታዩ ቸኮል የአዲስ አበባ ምክር ቤት የወጣቶች ክፍል ሃላፊ
4. አቶ ንዋይ ገበየሁ የህዝብ ግንኙነት ረዳት ሃላፊ እንዲሁም ሌሎችም ወደ አልታወቀ ቦታ በፖሊስ ተይዘው ተወሰደዋል።

እንደ ሚሊዮኖች ድምጽ ዘገባ ከሆነ ወያኔ/ኢሕአዴግ የኃይል የአዲስ አበባ ሰልፍ ከመደረጉ አንድ ቀን በፊት የኃይል እርምጃ መዉሰድ ጀምሯል። የአንድነት አመራሮች ፖሊስ እየጎተተ በማሳሰር እየሰራ ያለው፣ ከአቶ ትግስቱ አወል ጋር ከምርጫ ቦርድ ጋር አብሮ እየሰራ ያለው የማነ አሰፋ እንደሆነ ታወቋል።

በዚህ ሰዓት ትግሉ ወደ አንድ ምዕራፍ ተሸጋግሯል አስራት፤ ነዋይ ፤ስንታየሁና ሰለሞን ቢታሰሩም እንኳ የሶሻል ሚዲያውን ከሀገር ውጪ ያሉ የአንድነት ምዕራፍ 2 ሶሻል ሚዲያ ቡድን አባላት እየመሩት ነው ምዕራፍ 3 እና 4 ከሰዓታት በኋላ የተጀመረው ትግል ግቡን እስኪመታ እረፍት አይኖራቸውም፡፡

አንድነት ጥር 17 በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የጠራው ተቃውሞ ሰልፍ ስር ዓቱን እንቅልፍ እንደነሳው ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ::


No comments:

Post a Comment