የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ በጋራ ባወጡት መግለጫ ”ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ ደርሰናል” ብለዋል። ድርጅቶቹ አያይዘውም ”አገራችንና ሕዝባችንን ከአዘቅት ለማውጣት በመጣመር ብቻ ሳይሆን በውህደት አንድ ሆነን አገራችንንና ሕዝባችንን አንድ በማድረጉ ረገድ አስፈላጊው መስዋዕትነት በመክፈል የትግል እድሜ እናሳጥር በሚል ለውህደት የሚያደርሰንን ውይይት ለመጀመር የሚያስችል ሂደቶችን አጠናቀን ወሳኝ ወደሆነው ሂደት ውስጥ መግባታችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ወዳጆች ማብሰር እንፈልጋለን።” ብለዋል።
ሶስቱ ድርጅቶች የወያኔን መንግስት በሃይል ለመጣል ከሚንቀሳቀሱት ንቅናቄዎች ዋናዎቹ ሲሆኑ፤ በአሁኑ ሰአት ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል። በተለይም የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ በወያኔ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ የትግል አቅጣጫው የተቀየረ እና የኢትዮጵያ ህዝብና ለነጻነት እንታገላለን የሚሉ ድርጅቶች ወደ አንድ ጎዳና እየመጡ መሆናቸው በርካታዎችን ያስደሰተ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰአት ማህበረሰቡ ጠንካራ የሆነ እንቅስቃሳሴ ማየት እንደሚሻ በተደጋጋሚ እየጠየቀ ሲሆን፤ አሁን የጀመረው የስምምነት መስመር ምናልባትም የነጻነት ሃይሎች በከፍተኛ ደረጃ ትግሉን ግብ ለማድረስ የተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያሳይ ምልክት ነው ሲሉ አንዳንድ ከዜናው በሆላ ያነጋገርናቸው ሰዎች ይገልጻሉ።
No comments:
Post a Comment