መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በንግድ ስራ የምትደዳረዋ ካሚል ሙሃመድ ታውኒ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላት በሚል በኬንያ ልዩ ፖሊስ ተይዛ ለሶማሊና ለኢትዮጵያ መንግስታት ተላልፋ መሰጠቷን ተከትሎ ሰቆቃ እንደተፈጸመባት ተናግራለች።
ቃሏን ለፍርድ ቤት ስታሰማ እንባዋ ያቋርጣት እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል። ወ/ት ትዌኒ የህክምናዋን ወጪ ለመሸፈን የኬንያ መንግስት የገንዘብ ካሳ እንዲሰጣት ፍርድ ቤትን ጠይቃለች። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ከሰማ በሁዋላ ከአንድ ወር በላይ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የኬንያ ፖሊስ ድርጊቱን አለመፈጸሙንና በዚህ ስም የታሰረ ስለመኖሩ እንደማያውቅ ገልጿል፤፡
የኬንያ ፖሊስ ድርጊቱን አለመፈጸሙንና በዚህ ስም የታሰረ ስለመኖሩ እንደማያውቅ ገልጿል፤፡
No comments:
Post a Comment