Saturday, September 19, 2015

ወደ ኢትዮጵያ የሸሹት የትሂዴን አባላት ከ70 የማይበልጡ መሆናቸው ታወቀ


mola Asgidom
ኢሳት ዜና (መስከረም 7, 2008)
ባለፈው ሳምንት ትግል በቃኝ በሚል ታጣቂዎችን አስከትለው እጃቸውን ለኢትዮጵያ መንግስት የሰጡት አቶ ሞላ አስገዶም ይዘውት የሄዱት ታጣቂ ብዛት 70 ብቻ መሆኑን እንዲሁም ከድርጅቱ 25 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከአቶ ሞላ በቀር እጃቸውን የሰጠ ኣንደሌለ ተገለጠ።
አርብ ጻጉሜ 6 ቀን 2007 አም በኢትዮጵያ አዲስ አመት ዋዜማ ከኤርትራ ወደሱዳን የተሻገሩትና ከዚያም ለኢትዮጵያ መንግስት እጃቸውን የሰጡት አቶ ሞላ አስገዶም፣ ለዘመቻ በሚል ከንቀሳቀሷቸው 115 ወታደሮች 45ቱን መመለስ እንደተቻለ ተመልክቷል። 
የትሕዴን ም/ሊቀመንበር የነበሩትና አሁን በተጠባባቂነት የድርጅቱን የመሪነት ስፍራ የጨበጡት አቶ መኮንን ተስፋዬ እንደተናገሩት ከአቶ ሞላ በስተቀር አንድም የትሕዴን አመራር ለኢትዮጵያ መንግስት እጁን አልሰጠም።

ከድርጅቱ 25 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ወደ ኢትዮጵያ የተሻገሩትና እጃቸውን የሰጡት አቶ ሞላ አስገዶም ብቻ መሆናቸውን አቶ መኮንን ተስፋዬ ገልጸዋል። ተገደው የሚሄዱትን ወታደሮች ለመመለስ በተደረገው እንቅስቃሴ ግጭት መከፈቱን በማውሳትም፣ በመሰደድ ላይ ከነበሩት 115 ታጣቂዎች 45ቱን መመለስ መቻላቸውን አስረድተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የትሒዴን ሃይል ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያ መግባቱን የገለጸው መንግስት በገዢው ፓርቲ ይፋዊ ያልሆኑ ልሳናት በኩል ተጨማሪ ታጣቂዎች ኤርትራ ቀርተዋል ሲል የቀደመውን መግለጫ የሚያስተባብል መረጃ አስራጭቷል። ከበሽተኞቹ በቀር ሁሉም ሃይል ወጥቷል ሲል መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግስት 200 ተጨማሪ ታጣቂዎች ቀርተዋል ሲል ትናንት ሃሙስ ይፋ አድርጓል።
በድንበር አካባቢ ግጭት መኖሩን ይህም ትጥቅ እንዲፈቱ በተጠየቁ ሁለት መቶ የደምሄት (ትሂዴን) ሰራዊትና በኤርትራ ወታደሮች መካከል ነው ሲልም አክሏል። በአካባቢው ግጭት ስለመኖሩ ከገለልተኛ ምንጭ ማግኘት አልተቻለም።

No comments:

Post a Comment