‹‹ሞላ (አስገዶም) ግን ምን አይነት ሰው ነው? ንግግር አይችልም፡፡ ሚዲያ ላይ ሲቀረብ፣ ምን እንደሚነገርና ምን እንደማይነገር እንኳን ለይቶ አያውቅም፡፡ ‹‹መግለጫው››ን በአጋጣሚ አይቼ በመገረም ‹‹አጃኢብ›› ስል ነበር፡፡ [ፈገግታ ያጀበው ሳቅ] …ኢህአዴግም ሞላን ከሚያስከዳ ይልቅ ሌላ ሰው ቢሞክር ይሻለው ነበር፡፡ የሞላ ትርጉሙ አልታየኝም፡፡ የብርሃኑ (ነጋ/ፕሮፌሰር) ኤርትራ መምጣት ሞላን አነስተኛ (Insignificant) አድርጎታል፡፡ ሰውየው ለዓመታት እንዲሁ ተቀምጦ የነበረ ይመስለኛል፡፡
እውነት ነው፣ ፖለቲካ ዕውቀት እና ብስለት ይጠይቃል፡፡ አንዳንዱ ፖለቲከኛ ከበላዩ ሰው ሲመጣበት አይወድም፤ አይመቸውም፡፡ መለስ ዜናዊ (የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር) ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው፤ የሚበልጠውን ሰው አይፈልግም ነበር፡፡ ሞላም እውነተኛ ታጋይ ቢሆን ኖሮና ኤርትራ ካሉት ጋር ቢጣላ እንኳን፤ ወደዚህ መምጣት ሳይሆን፣ ከትግሉ ርቆ አርፎ መቀመጥ ነበረበት – ከመርህ አኳያ! ታዲያ ምን እቀይራለሁ ብሎ ነበር በረሃ የገባው? ብቻ፣ የኑሮ ሰቀቀን ያለበት ይመስላል፡፡ …ኤልያስ፣ በፖለቲካ ዓለም ውስጥ፣ ዋናው ግቡ የግል የኢኮኖሚ ጥቅሙን ማግኘት ያደረገ ሰው ካለ ያን ጥቅም ያገኘ ቀን ትግሉን ያቆማል …››
/ ተማም አባቡልጉ (ጠበቃ) ጋር፣ ትናንት ተገናኝተን ሥለሀገራዊ ጉዳይ ኢ-መደበኛ ጨዋታ እና የሀሳብ ልውውጥ ስናደርግ ከተናገረው የተወሰደ፡፡
No comments:
Post a Comment