ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከ9 ሺ በላይ አባወራ አርሶ አደሮች የሚኖሩባቸው 8 የቀበሌ ገበሬ ማህበራትን ወደ ከተማ ለማካለል የከተማው ማዘጋጃ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በርካታ አርሶ አደሮች ለችግር ተጋልጠዋል።
ሁን ቦላሬ፣ ኦፋጋን ደባ እና ኦፋሴሬ የሚባሉ ቀ/ገ/ ማህበራት በሚዋሰኑባት አንዲት ጎጥ ብቻ 380 ቤቶች መፍረሳቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች በጠቅላላ በከተማው ዙሪያ ባሉት አርሶአደር መንደሮች የፈረሱት ቤቶች ቁጥር ከ2 ሺ 500 በልጧል ይላሉ።
እርምጃውን ተከትሎ አራስ ሴትና ህጻናት ሳይቀር ጎዳና ላይ የወደቁ ሲሆን፣ ታምራት ታንቱ ባጫ የተባለ ወጣት፣ ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ በመንግስት አፍራሽ ግብረሃይሎች መፍረሱን ተከትሎ፣ ራሱን አጥፍቷል።
አርሶ አደሮቹ ከ12 ሺ እስከ 80 ሺ ብር የሚደርስ ገንዘብ አውጥተው ቤታቸውን መስራታቸውን ይናገራሉ።
እርምጃውን ተከትሎ አራስ ሴትና ህጻናት ሳይቀር ጎዳና ላይ የወደቁ ሲሆን፣ ታምራት ታንቱ ባጫ የተባለ ወጣት፣ ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ በመንግስት አፍራሽ ግብረሃይሎች መፍረሱን ተከትሎ፣ ራሱን አጥፍቷል።
አርሶ አደሮቹ ከ12 ሺ እስከ 80 ሺ ብር የሚደርስ ገንዘብ አውጥተው ቤታቸውን መስራታቸውን ይናገራሉ።
No comments:
Post a Comment