ሐምሌ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው በሚገኙ በኢህአዴግ ድርጅት ኃላፊዎች የተመራውና በተያዘው በጀት ዓመት ከተማዋን ይመራሉ ተብለው የሚሾሙ የድርጅት ካድሬዎችን የሚለይበት የከተማና የክ/ከተማ ከፍተኛ የግምገማ መድረክ አጋማሹን ካድሬ አስደስቶ አጋማሹን ደግሞ አሳዝኖና አበሳጭቶ ተጠናቋል፡፡
በሃምሌ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ የተጀመረው ይህ ግምገማ በልዩ ትኩረት አጀንዳ ተቀርፆለት በተቀመጠለት መርሃ ግብር መሰረት በአጠቃላይ 20 ቀን የፈጀ ሲሆን ፣ ባለፈው ዓርብ ሃምሌ 24 ቀን 2007 ዓ.ም በከተማ ደረጃ የሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮችን መድረኩ ከገመገመ በኋላ ለከፊሎቹ አዛዛኝ ጊዜ ሆኖ ተጠናቋል፡፡
ይህ ተከታታይ ግምገማ በከተማና በክ/ከተማ የሚገኙ የኢህአዴግ አመራሮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በየደረጃው የስራ ባህሪያቸው የሚመሳሰሉትን አመራሮች አካቶ በዞን ተካፋፍሎ ተገምግሟል።
በተለያዩ መድረኮች ማለትም የአዲስ አበባ ም/ቤትን ጨምሮ የከተማው ቁልፍ ካድሬዎች የመሩት ግምገማ ሲሆን፣ በግምገማው በከተማው ቀጣይ አመራር ሆኖ የሚቀጥልና የማይቀጥል በሚል የሚለዩበት ሆኖ ተጠናቋል፡፡
ግምገማው ከፍተኛ ጭቅጭቅ የተነሳበት፤በአመራሮች መካከል ስድብ ቀረሽ ዘለፋ የተካሄደበት፤ አንዱ ሌላውን ለመጣል ጓደኛ እና ጓደኛ የተጣላበት፤ በስራ እና በአመራር ቆይታ ወቅት በነበሩ የስራ አፈፃፀም ወቅት የነበራቸውን ጥንካሬና ድክመት ሳይገለጹ የቀሩበትና ዕርስ በዕርስ የተካካዱበት ግምገማ ሆኖ ተጠናቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የግምገማው ውጤት በአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት ደረጃ በቅርቡ ባሉበት ሹመት ደረጃ የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ እንዲሁም ከአመራር የሚባረሩ በሚል የመጨረሻ የውጤት ደረጃ እስከሚገለጽ ድረስ እየተጠበቀ ነው።
ከወዲሁ የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ ካድሬዎችን ለመለየት በሚያስችል ደረጃ በግምገማው ላይ የተለየ ሲሆን፣ ከማይቀጥሉ ወገን ያሉት አመራሮች ብስጭታቸውን ለማስታገስ የህመም ፈቃድና ማህበራዊ ጉዳዮችን ሰበብ በማድረግ ፈቃድ እየጠየቁ ነው።
በወረዳ ደረጃ ያለው ግምገማ ደግሞ ሃምሌ 17 ቀን 2007 ዓ.ም ተጀምሯል።

No comments:
Post a Comment