Monday, August 10, 2015

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) አመራሮች ም/ል ፕሬዝደንቱ የፍርድ ቤት ውሎ

የፍርድ ቤት ውሎ (ለገሰ ወ/ሃና )
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) አመራሮች ም/ል ፕሬዝደንቱ
1 ዘመነ ምህረት
2 ጌትነት ደርሶ አባል
3 መለሠ መንገሻ የወጣቶች ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ
ዛሬ ነሐሴ 4/2007 ዓም 4:20 ሰአት አካባቢ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ተከሳሾች እና ከሳሽ ያቀረቡትን መቃወሚያ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ነበር
በዚህ መሠረት
1ኛ ተከሳሽ ዘመነ ምህረት ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ሙሉበሉ ውድቅ ተደርጏል በተለይ የተከሰሰበት አንቀፅ እንዲሻሻል ያቀረበው መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ አንቀፁ መሻሻል የለበትም ብሏል ዘመነ የተከሰሰበት አንቀጽ ከ15 አመት እስከሞት የሚያስቀጣ መሆኑ የታወቃል
3ኛ ተከሳሽ መለሠ መንገሻ ያቀረበው መቃወሚያ በከፊል ተቀባይነት አግኝቷል በዋናነት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ ) አባል መሆን ከአመራሮቹ ጋር በስልክ -------መገናኘት ወዘተ የሚለው የአቃቤ ህግ ክስ
መለሠ መንገሻ ያቀረበው መቃወሚያ የኢትዮጵያ ህዝብ አረበኞች ግንባር( ኢህአግ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ያልተፈረጀ ስለሆነ አሸባሪ ተብየ ልከሰስ አይገባኝም ያለውን ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል
ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የቀረበው የሽብር ክስ ተሻሽሎ በህገመንግስቱ መሠረት በወንጀል ይከሰስ ሲል አቃቤ ህግ ተቃውሟል ተከሳሽ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው መቃወሚያ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ( ኢህአግ ) በፓርላማ በአሸባሪነት አልተፈረጀም ያለው እውነት ቢሆንም
በአሸባሪነት ከተፈረጀው ከግንቦት 7 ጋር ተዋህዷል በአሸባሪነት ነው መከሰስ ያለበት ብሏል
ፍርድ ቤቱ ግን አልተቀበለውም የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ከተከበረ በህገመንግስቱ መሠረት ክሱ ተሻሽሎ ለነሐሴ 13/2007 ዓም በተመሳሳይ ሰአት እንዲቀርብ ታዟል
ሁለተኛ ተከሳሽ ጌትነት ደርሶ ምንም አይነት ሀሳብ አልሰጠም ምክንያቱ ደግሞ ቀደም ሲል ጠበቃ አልፈልግም ክርክር አላደርግም ከዚህ ፍርድ ቤት ፍትህ ስለማላገኝ ስላለ በዛው ቀጥሏል
ዛሬስ ተከሳሾች ምን አሉ ?
ቀድሞ የመናገር እድል ያገኘው መለሰ መንገሻ ነበር
፠ በአሸባሪነት በመከሰሴ ህክምና ተከልክያለሁ


፠ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት ደርሶብኛል( አማራ በመሆኔ)
፠ ለመከላከያ ምስክርነት ወደ አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስወሰድ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞብኛል
፠ አጄኝ አጥብቀው በካቴና አስረው አመመኝ እጄ ሊቆረጥ ነው ስላቸው ለእጅህ ይገርምሃል እንዴ ገና አንገትህን እንቆርጠዋለን ተብያለሁ ብሎ ለችሎት አቤቱታ ቢያቀርብም ዳኞች ከተመካከሩ በኇላ " እኛ የተቀመጥነው የቀረበልንን መዝገብ መርምሮ ውሳኔ መስጠት ብቻ ነው " የሚል መልስ ሰጥተውታል::
ዘመነ ምህረት
፠ዘመነ ፊቱን ወደ ጏደኛው መለሰ ፊቱን አዙሮ ከዚህ ፍርድ ቤት ፍትህ አንጠብቅም ለምን ትደክማለህ
፠የህግ የበላይነት በሌለበት አቤቱታ ማቅረብ ተገቢ አይደለም
፠ ወደ ዳኛ ፊቱን አዙሮ ዛሬ ወደዚህ ስመጣ በእጁ ፓሊሱን እያመለከተ ደብድቦኛል ሲል አብረውት የመጡት ታሣሪዎች ሁሉም ባንድነት አዎ መቶታል አሉ ዘመነ መታኝ ያለው ፓሊስ ይሰቅ ነበር ለመለሠ እንዳደረጉት ዳኞቹ ተማከሩ የመለሱት መልስ በጣም ያስቃል የመለሱት የመጀመሪያውን ነው " እኛ የቀረበልንን መዝገብ መርምረን ውሳኔ መስጠት ብቻ ነው የኛ ተግባር " አሉ
፠ ከናንተ ፍትህ አንጠብቅም እኛ ፍርድ የምንጠብቀው ከእግዚአብሔር ነው ሁላችንም በእምነታችን ወደ ፈጣሪ መጮህ አለብን በተለይ የኦርቶዶክስ አማኞች አሁን ወቅቱ የጾም ነው በርትተን መፀለይ አለብን እውነተኛ ዳኝነት የሚገኘው ከፈጣሪ ብቻ ነው በማት ሀሳቡን አጠቃሏል::
ከነ ዘመነ ምህረት በመቀጠል ቁጥራቸው 10 አካባቢ እድሜያቸው 17 እስከ 20 የሚሆን ትንንሽ ልጆች ናቸው ለአቅመ እስራት ያልደረሱ ናቸው ችሎት የቀረቡት የመጡት ከጎንደር እና ከጎጃም አካባቢ ነው ስማቸው ሲጠራ አይሰማም ነበር በዚህ ምክንያት ስማቸውን አልያዝኩም
ስለተከሰሱበት የሸብር ክስ ምንም ያልገባቸው ናቸው ከአርበኞች ግንቦት ሰባት እና ከሌሎች አሸባሪ ድርጅቶች ጋር ሽብር ለመፍጠር ስትንቀሳቀሱ ነበር የሚለውን ክስ ሲሰሙ እኛ የምትሏቸውን ስሞች እየሠማን ያለነው ከናንተ ነው እኛ አናውቃቸውም እተደበደበን ያለነው አማራ በመሆናች ነው መርማሪዎች የጠሉት አማራነታችንን ነው ብለዋል ::

No comments:

Post a Comment