ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርበኞች ግንቦት ሰባት የጀመረውን የነፃነት ትግል በገንዘብ ለማጠናከር በላስቬጋስ ከተማ የተጠራው የሀገር አድን ጥሪ በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎና በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን በእለቱ በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ከፍተኛ ገንዘብ መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል፡
በዚህ ለሰማእታት በተደረገ የህሊና ጸሎት የተጀመረ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ አቶ ሙሉነህ እዩኤልና አቶ ጋሻው ገብሬ የንቅናቄው አመራር አባላት በአዳራሽ ተገኝተው አስፈላጊውን ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይ የታደመው የላስቬጋስ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በንቅናቄው መሪዎች ወደ ትግሉ ሜዳ መውረድ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ወያኔን አስወግዶ በምትኩ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት ንቅናቄው የጀመረውን ትግል እስከመጨረሻው ድረስ ከንቅናቄው ጎን በመሰለፍ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡
ንቅናቄውን በገንዘብ ለማጠናከር በጎልድ ኮስት ሆቴል በተጠራው በዚህ ስብሰባ ልይ ከፍተኛ የህዝብ መነቃቃት የታየበት ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ገንዘብ መሰብሰቡንም ለማወቅ ተችላል፡፡
ንቅናቄውን በገንዘብ ለማጠናከር በጎልድ ኮስት ሆቴል በተጠራው በዚህ ስብሰባ ልይ ከፍተኛ የህዝብ መነቃቃት የታየበት ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ገንዘብ መሰብሰቡንም ለማወቅ ተችላል፡፡
No comments:
Post a Comment