በምህራብ ዞን የሚገኙ የእስታፍ ሰራተኞች ወታደራዊ ሚስጥር አባክነዋል በሚል ለ8 ቀናት በስብሰባ ላይ ተጠምደው መሰንበታቸው ታወቀ።በምእራብ እዝ፤ በባህርዳር መኮድ በተባለው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የስርዓቱ የሰራዊት አባላት ወታደራዊ ምስጢር አባክናችኋል በሚል ሰበብ ለ 8 ቀናት ስብሰባ ላይ መቀመጣቸው የገለጸው መረጃው ነገር ግን በተካሄደው ስብሰባ ምንም አይነት ፍንጭ እንዳልተገኘና አመራሮቹ በራሳቸው ጥርጣሬ ብቻ ለ6 ሰው በቁጥጥር ስር እውለው የት እንደወሰዷቸው እስካሁን ድረስ እንዳልታወቀ ተገለጸ።
መረጃው በማከል- ሓምሌ 17/2007 ዓ/ም ከሌሊቱ 7:30 ላይ በረጅም ርቀት መገናኛ የተላለፈ መልእክት ሲሆን ከሦስት ቀን በኋላ መልእክቱ ቀድሞ ሳይተገበር መጥተዋል በሚልና በአመራርና በአባላት መካከል ያለው ክፍተት በመባባሱ በውስጣችን ከጣላት ጋር የተያያዘ ነገር አለ በሚል ስብሰባው መካሄዱና አሁንም እየቀጠለ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment