ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውስትራሊያ የሜልቦርን የአርበኞች ግንቦት7 ጽ/ቤት ” ሀገራችን ስላለችበት ሁኔታ እንምከርበት” በሚል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል ብሎአል።
የድርጅቱ የሜልቦርን ከተማ ተጠሪ አቶ ነብዩ መላኩ ፣ “የድርጅት አጥር ሳይከልለን ትግሉን እንርዳ” የሚል መልእክት ሲያስተላልፉ፣ ዶ/ር ታደሰ ብሩ በስካይፕ ባስተላለፉት መልእክት ደግሞ ” ትግሉ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን ገለጸው፣
“ትግላችን ወደ ጎን ሳይሆን ወደ ፊት ነው” በማለት፣ ህዝቡ በተለያዩ ሚዲያዎች በሚነዙ ወሬዎች እንዳይወናበድ እና ተአማኒነት ያላቸውን የመገናኛ ብዙሃን እንዲከታተል መክረዋል።
በአርበኞች ግንባር እና በከፋኝ ድርጅት ሲሳተፉ የነበሩ ታጋዮችም፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትግሉን ይደግፍ ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን የከተማው የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ አባል ወንድማገኝ ጌታሁን ገልጿል።

No comments:
Post a Comment