ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ለሁለት ቀናት በመዲናዋ አዲስ አበባ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን በድጋሜ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ ለቀጣዩ ሦስት ዓመታት ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡ ሲሆን፣ አምስት የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላትም በጉባኤው ተመርጠዋል፡፡ ጉባኤው የፓርቲውን የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም መርጧል፡፡
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲን ለቀጣይ ሦስት ዓመታት እንዲመሩ 136 ድምጽ ሲያገኙ ተፎካካሪያቸው አቶ ዮናታን ተስፋዬ 60 ድምጽ አግኝተዋል።
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲ በሁለቱ ቀናት ጉባኤው ያነሳቸውን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰሩ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲን ለቀጣይ ሦስት ዓመታት እንዲመሩ 136 ድምጽ ሲያገኙ ተፎካካሪያቸው አቶ ዮናታን ተስፋዬ 60 ድምጽ አግኝተዋል።
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲ በሁለቱ ቀናት ጉባኤው ያነሳቸውን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰሩ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
No comments:
Post a Comment