ጥር 6 ቀን 2002 ዓም በተለምዶ ጉበት ከለር እየተባለ የሚጠራውን ቀለም የተቀባች ኮድ ሁለት የታርጋ ቁጥሯ 63795 የሆነች ‹‹ ወያኔ›› ዲኤክስ የቤት አውቶሞቢል ሾፌሩን ጨምሮ አራት ሰዎችን ይዛ ወደ ኢህአዴግ ፅ/ቤት እየከነፈች ነው ሾፌሯ የመኪናዋ ባለቤት ነው ፡፡ሶስት እንግዶችን ባስቸኳይ አቶ በረከት ቢሮ እንዲያደርስ ነው የታዘዘው ሁለት ወጣቶችንና አንድ ሰውነቷ ሞላ ያለች ሴትይዟል ፤የካቴድራል ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን በር ሊደርሱ ጥቂት ሲቀር የግንብ አጥሩ ከቤተክርስቲያኑ ግምብ ጋር የተያያዘው ግዙፉ የኢህአዴግ ፅ/ቤት በር ላይ ቆሙ እጆቻቸውን ከመሳሪያቸው ምላጭ ላይ ከማይነቅሉት ላብ አደር የመከላከያ ሠራዊት መካከል አንዱ ጠጋ አለና ‹‹አቤት ›› አለ ከሾፌሩ አጠገብ የተቀመጠችው ሴት ወ/ሮ ‹‹ አቶ በረከት ጋር ቀጠሮ አለን ›› አለችው ወታደሩም ‹‹ሁላችሁም›› አለ ‹‹ አዎ ›› አለች ራመድ አለና ከአንድ ሌላ የእሱ ቢጤ ጋር ተነጋግሮ በሩ ስር ካለች አነስተኛ ቤት ወረቀት ይዞ ወጣና አነበበ ወደ መኪናዋም ተጠጋና የአራቱንም መታወቂያ ጠየቀ ተሰጠው በስማቸው ትክክል ከመታወቂያቸው ላይ ካመሳከረ በኋላ በባለ ዘንግ ክብ መስተዋት የመኪናዋ ሆድ እቃ ሳይቀር ተፈትሽው ወደ ውስጥ እንዲገቡ ተፈቀደላቸው ወታደሩ ይዟት መጥቶ የነበረው ወረቀት ‹‹ ወ/ሮ ሙሉ ከነመኪናቸው ይግቡ›› የሚል ከበረከት ስምዖን ቢሮ የተላከች የመግቢያ ፈቃድ ነበረች ፡፡
አራቱም ሰዎች ከበረከት ፀሐፊ ከዓለም ጠረቤዛ ደረሱ በሃይላንድ ውሃ ጉዳይ ከህላዌ ዮሴፍ ጋር እየተጨቃጨቀች ነበር ቀልደኛውና ሲፈጥረው ባለስልጣን መሆን ያልነበረበት ህላዌ አይቷቸው የማያውቀውን አንግዶች ሲያይ ደንገጥ አለና ወደ ኋላው ሁለት ርምጃ ተሳበ አንግዶቹ አለምን እየጨበጡ መግባት ይችሉ እንደሆነ ጠየቁ በወቅቱ የስምዖን ልጅ በረከት ከአዲሱ ለገሰ ጋር ውይይት ላይ ስለነበር ‹‹ ቁጭ በሉ ከሰዓታችሁ 20 ደቂቃ ቀድማችኋል አለቻቸው›› ተቀመጡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ አዲሱ እየሳቀ ከበረከት ቢሮ ሲወጣ እሱም አንግዶቹን አየና አልፏቸው ሊሄድ ብሎ መለስ አለና እጁን ለሰላምታ ዘረጋላቸው በአክብሮት ጨበጡት ወ/ሮዋን ሲጨብጥ ጠበቅ አድርጎ ያዛትና ‹‹የት ነው የማውቅሽ ሦስተኛ ጉባኤ ላይ ነው አራተኛ ነው … እዚህ ቦታ እዚያ ቦታ ››እያለ ሲያስጨንቃት ወ/ሮዋ ፈገግ በማለት ብቻ ዝም አለችው አዲሱ ግን ተሸውዷል በወቅት ወ/ሮ ሙሉን የትም ቦታ አያውቃትም ነበር፡፡
በረከት ከመቀመጫው ተነስቶ ተቀበላቸው ትንሽ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ሾፌሩ ወደ ውጪ ወጣና ፀሐፊዋ ዓለም ጋር የመጣለትን ወፍራም ቡና እየጠጣ ከፊት ለፊቱ ‹‹ልማታዊውን ባለሀብት አትንኩት›› የሚል ትዕዛዝ ይሁን ልመና ፁሁፍ ያለበትን የሼክ አላሙዲንን ፎቶ እያየ በሀሳብ ሄዷል ሶስቱ ሰዎች ረዘም ላለ ሰዓት ቆዩ ድንገት ያልታሰበ ነገር ተከሰተ የታላቁ ባለስልጣን የአቶ በረከት ቢሮ በኃይል ተበረገደና ወ/ሮዋ ስትቀር ሁለቱ ወጣቶች በቁጣ መንፈስ ወጡ በዚህ ጊዜ ጸሀፊዋ ዓለም በፍጥነት ተነስታ የበረከትን ቢሮ እንደመዝጋት ደህንቱን እንደማረጋገጥም ወደ ውስጥ አየት አድረጋ መልሳ ዘጋችው ሁለቱ በፍጥነት ደረጃውን እየወረዱ ነበር ከጥቂት ቆይታ በኋላም ወ/ሮዋ ወጣች በር ላይ ቆሟ ግን አንዲት ቃል ወረወረች ‹‹በረከት ግን ጊዜ ወስደህ አስብበት ይህ ለሁላችንም (ለማንም) አይበጅም አለችው ተጨማሪ ንግግር ልታደረግ ያሰበች ትመስል ነበር ግን ከአፍንጫው ከፍ ብሎ ባለው ቦታ ላይ ንቅሳት ያለው የበረከት ስምዖን የግል ጠባቂ ከዚህ መጣ ሳይባል ድንገት ከተፍ ብሎ ወ/ሮዋን እንደ ማባበልም እንደ መግፋትም አድርጎ ቢሮውን ከጀርባው እየዘጋ ደጋግፎ ሸኛት ፡፡
በወቅቱ በረከት ቢሮ የመጡት እነዛ ሰዎች እነማን ናቸው ? የተነጋገሩትስ ሰለምንድን ነው? ያልተግባቡትስ በምንድን ነው ? ይህን ጉዳይ ከእኔ ከፀሐፊዋ ይልቅ የአንድነት ፓርቲ የአመራር አባል የነበረው ኢ/ር ዘለቀ ረዲ አሳምሮ ያውቀዋል:: ፁሁፌን ከማጠቃለሌ በፊት እነዛ አራት ሰዎች አሁን የት ናቸው? ለሚለው ጥያቄ መልስ ልስጥ የመኪናዋ ባለቤትና ሾፌር የነበረው በአሁን ወቅት ከኢ/ር ዘለቀ ረዲ ጋር በገጠር መንገድ ሥራና በታላላቅ የውሃ ቁፋሮ ሥራ ተሰማርቶ ሚሊየነር ሆኗል:: አንደኛው ገጣሚ ሙሉ ሰሎሞን ራት ጋብዛው ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ከካዛንቺስ ወደ መገናኛ መኪናውን እያሽከረከረ ሲሄድ በተሳሳተ መንገድ ከሌላ አቅጣጫ በሚመጣ መኪና ይገጭና ይቆማል:: ድንጋጤው አልፎለት ከመኪናው ሊወርድ ሲል በገጪው መኪና ውስጥ ከነበሩ ሰዎች በተተኮስ ሽጉጥ ተገደለ:: ሶስተኛው ሰው በአሁን ወቅት ወሊሶ ወህኒ ቤት የማያውቀው ወንጀል ተለጥፎለት የሰባት ዓመት ፍርደኛ ሆኖ ተኝቷል:: አራተኛዋና ወ/ሮ ሙሉ ኃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ በሚሊየን የሚቆጥር ገንዘብ አጭበርብራለች ተብላ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆነችና ነነዊት አፈወርቅ ከተባለች ልጇ ጋር 28 (ሃያ ስምንት) ዓመታት ተፈርዶባት ቃሊቲ ተጥላለች፡
እስኪ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ወ/ሮ ሙሉ ኃይለማርያም በምን እንደተሳረች የዘገቡትን አድምጡና ፍርድ ስጡ ምን ያህሉ ተዓማኒ ነበር ?እኚህ ስማቸውን መግለፅ አንፈልግም የተባሉና የተጠየቁትን ሚሊዮኖች እያወጡ የሚሰጡ ሰው ማናቸው? ሊንኩን ተጭነው ዜናውን ያድምጡ።
No comments:
Post a Comment