ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ብአዴን በባህርዳር ባካሄደው 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ክልሉን የገጠሙትን ፈተናዎች አቅርቧል። ጉባኤው በዝግ የተካሄደ ሲሆን፣ አንዳንድ የጉባኤው ተሳታፊዎች ድርጅቱ የገጠመውን ፈተና በዝርዝር አቅርበዋል።
ዝምታን የመረጠው ህዝብ በስርዓቱ ደስተኛ እንዳልሆነ በርካታ አመላካች ነገሮች መኖራቸው የተብራራ ሲሆን፣ “ህዝብ አኩርፏል፣ ምን እናድርግለት ?” የሚል ጥያቄም ተነስቷል።
በእየአመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ስራአጥ ወጣቶች መምጣታቸው በመንግስት ላይ የህልውና ስጋት መፍጠሩ በጉባኤው ላይ ተወስቷል። በጥቃቅንና አነስተና ስራዎች የሚመረቁ ወጣቶች ፣ ተመርቀው እሴት የሚጨምር ፈጠራ ለማሳየት ባለመቻላቸው ፕሮግራሙን ዋጋ አልባ አድርጎታል። የመንግስት ፖሊሲ ከዶር እርባታ፣ ከብት ማድለብ እና የስሚንቶ ምርት የተሻለ ማየት ባለመቻሉ፣ እያደገ የመጣውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ አላስቻለውም ተብሎአል።

No comments:
Post a Comment