Thursday, July 2, 2015

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ባለአክሲዮን የሆኑበት ኮሌጅ የህግ ትምህርት መስጠቱን ቀጥሎአል

የኢህአዴግ መንግስት ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም መልኩ የህግ ትምህርት በግል ተቋማት እንዳይሰጥ የከለከለ ሲሆን፣ የአቶ ደመቀ ከፊል ንብረት የሆነው ሚሸከን ኮሌጅ ግን ተማሪዎችን እያሰተማረ እንደሚገኝ መረጃዎች አመልክተዋል። ተመሳሳይ ድርጊት የፈፀሙ ኮሌጆች ቢዘጉም፣ ለሚሽከን ኮሌጅ ግን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጀንሲ ከማሰጠንቀቂያ ያለፈ ውሳኔ አልሰጠውም። የሚሽከን ኮሌጅ መስራች በአዊ ብሄረሰብ አሰተዳደር ዞን የዚገም ወረዳ አሰተዳዳሪ የነበሩት አቶ ቢምረው ዋሴ ሲሆኑ፣ እሳቸውም ከወረዳው ሶስት ሚልዮን ብር ዘርፈዋል በሚል ለፀረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ በደረሰበት ወቅት፣ ም/ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንንን ተጋሪ አድርገው ከምርመራ መዳናቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ሚሽከን ኮሌጅ በ21 ከተሞች ከ43 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡ በርካታ ባለስልጣናትን ከጀርባቸው አዝለው የሚሄዱት የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የህግ ጥሰት ሲፈጽሙ ከማስታወቂያ ያለፈ እርምጃ እንደማይወሰድባቸው መረጃውን ያጠናከረችው የክልሉ ዘጋቢ ገልጻለች። በጉዳዩ ዙሪያ የኮሌጁን ስራ አስኪያጅና የትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44740#sthash.QbbuLWrq.dpuf


No comments:

Post a Comment